2016-11-19 11:05:00

ቅዱስነታቸው ከአሦር ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ጌዋርጌስ 3ኛ ጋር በቫቲካን ተገናኙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትነው እለት ማለትም በኅዳር 7/2009 ዓ.ም ከአሦር ምስራቃዊት ሁሉን አቀፍ (Catholicos) ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚ መሪ ከሆኑ ብጹዕ ፓትሪያርክ   ጌዋርጊስ ሦስተኛ ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው የታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸው በግንኙነቱ ወቅት ያደረጉትን ንግግር እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

ቅዱስነቶ እና የተከበሩ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!

በእዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ መካነ መቃብር በሚገኝበት ሥፍራ ከእናንተ ጋር መገናኘቴ ፀጋን የሚያጎናጽፍ እድል በመክፈቱ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል። በታላቅ ፍቅር እንኳን ደህና መጣችሁ ስል በእናነት የቀረበልኝ መልካም ንግግርን በማመስገን ጭምር ነው። በአሦር ለሚገኙ የምስራቃዊ አብያተ ክርስቲያን ጳጳሳት፣ ካህናት እንዲሁም ምዕመናን ሰላምታዬ በእናንተ በኩል ይደርሳቸው ዘንድ አቀርባለሁ። በእዚህ ከተማ ደሙን ለጌታ ባፈሰሰው ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ቃል ላይ ተመስርቼ “ከአባታችን ከእግዚኣብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን” (ሮም 1.7) ለማለት እፈልጋለሁ።

በእዚህ ግንኙነታችንና ዛሬ ከተወሰነ ጊዜ ቡኋላ በጋር በምናሳርገው ጸሎት ጌታችን የሰላምን ፀጋ ይሰጠን ዘንድ እንማጸናለን። በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም ደግሞ በኢራቅ እና በሶሪያ እየታየ በሚገኘው ነገር ተደናግጠናል። በእዚያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሚስኪን ሕጻናት፣ ሴቶችና ወንዶች በምንም ዓይነት መልኩ ተገቢ ባልሆነ ጦርነት እይተከሰተ ባለው አሰቃቂ ግጭት የተነሳ ደማቸውን በከንቱ እያፈሰሱ ይገኛሉ። በእዚያ የሚገኙ ክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም በቁጥር አናሳ የሆኑ የሌላ እምነት ተከታይና ለየት ያለ የዘር ግንድ ያለቸው ሰዎችም ሳይቀሩ ያለመታደል ሆኑ በእየቀኑ የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ስቃይና ፈተና ተለማምደውታል።

በየቀኑ እነዚህ ክርስቲያኖች በእዚህ ሐዘን ውስጥ ሆነው በየዋህነት የኢየሱስን ፈለግ በመከተልና ከእርሱ ጋር አንድነትን በመፍጠር  በመስቀሉ እርቅን ያመጣልንን እርሱን “በውስጣቸው ያለውን የጠላትነት ስሜትን በማስወገድ” የመስቀል መንግድ እየተጓዙ ይገኛሉ። እነዚህ ወንድሞች እና እህቶች በማንኛውም ዓይነት ችግሮች ውስጥ ብሆኑም እንኳን ከጌታ ጋር በታማኝነት ጸንተን በመኖር በችግራችን ወቅት ሁሉ መስቀሉን በመሳለም፣ እንዲሁም በእርሱ ፍቅር ተማምነን  መኖር እንደሚገባን በማሳየት አብነት ሆነውና። የእምነታችን መዐከል የሆነው ኢየሱስ በመከራችን ወቅት እንደሚጠራንና ሳንሰለች በእርሱ ፍቅር ታቅፈን መኖር እንዳለብንና በምሕረትና በይቅርታ መኖር እንዳለብንም አሳይተውናል። ይህንንም ዛሬም ቢሆን በመከራቸው ወቅት ሁሉ ለጌታ ታማኝ በመሆን ሕይወታቸውን ሳይቀር መስዋዕት በማድረግ መልካምን ነገር በመፈጸም ክፉን ነገር ማሸንፍ እንደ ሚቻል አስተምረውናል (ሮም 12,21)። እነዚ ወድሞቻችን እና እህቶቻችን የኢየሱስን መንገድ በመከተል ጥላቻን ማስወገድ እንዳለብን ስለገፋፉን ምስጋናችንን እናቀርብላቸዋለን። ኢየሱስ ደሙን ስለ ፍቅር ብሎ በማፍሰስ ሁሉንም በማስታረቅ አንድ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን እንድትበቅል እንዳደርገ ሁሉ እነደዚሁም የእነዚህ ሰማዕታት ደም የክርስቲያኖችን ሕብረት የሚፈጥር ዘር ነው። እነርሱም በወንድማማችነት ፍቅር ራሳችንን እብረት ለምፍጠር እንድናውል ይጋብዙናል።

በመካከላችን በነበረውና እየተጠናከረ በመምጣት ላይ ባለው ግንኙነታችንና ለእዚህ እርሶ ላደረጉት ጉብኝት እግዚኣብሔርን እያመስገንኩኝ ግንኙነታችን ከዚህ የበለጠ ይጠናከር ዘንድ ምኞተ መሆኑን እገልጻለሁ።

ከእዚህም ቡኋላ እርስ በእርሳችን በበለጠ ሁኔታ በመተዋወቅ በጋራ ወንጌልን የመመስከር ተልዕኮኋችንን በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል እድሉ ተፈጥሩዋል። ቅርበታችን  ሕብረት ወደ መፍጠር ደረጃ ተሻግሩዋል። በየትኛውም ቦታ ቢሆን በጋራና በፍቅር፣ ፍቅር ወደ ሚያመልክተን የሕብረት መንገድን መያዝ የጠበቅብናል። በጥምቀታችን ምክንያት በመካከላችን የጠለቀ ትስስር እንዳለም በድጋሚ ለመረዳት ችለናል። ካቶሊኮች እና አሦራዊያን “ሁላችንም ቢሆን በአንዱ በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቃችን” (1ቆሮ 12,13) የአንዱ የክርስቶስ አካል በመሆናችን ወንድማማቾች ነን። በእዚህ እርግጠኛ በመሆንና በመተማመን፣ በጸሎትም እምነታችንን በማጠንከር በተለይም ደግሞ በመንበረታቦት ዙሪያ “ሁሉንም ፋጹም በሆነ መልኩ አንድ ባደረገው” ፍቅር ልንታገዝ ያስፈልጋል። መለኮታዊ ሃኪም የሆነውን ጌታን የባለፍው ጊዜ ቁስሎቻችንን በእርሱ የምሕረት ቅባት ይፈወሱልን ዘንድ ሳንታክት ልንለምነው ያስፈልጋል።

ቅዱስነቶ እንዲሁም የተከበራችሁ ወንድሞቼ!

በታላቅ ደስታና ፍቅር እኛን ለመጎብኘት በመምጣታችሁና ዛሬ በጋራ አንዳችን ለንዳችን ለመጸለይ፣ የጌታ ጥበቃ የበዛልን ዘንድ በጋር መማጸን በመቻላችን፣ ምሕረቱን በሙልኋት ለመቀበልና በጋራ መመስከር እንድያስችለን ለመማጸን በመብቃታችን ያለኝን አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.