2016-11-14 14:29:00

ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ምሕረት በየቀኑ ያድነናል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 4/2009 በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት ድኾችን መረዳት እንዳለባቸው እንደ ወንድምና እህት ከመቁጠር ይልቅ እንደ ሸክም ከሚመለከት የደነዘዘ ሕልና ምዕመናን መራቅ እንዳለባቸው ማሳሰባቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚላካ ባሳረጉት ማስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ከ6ሺ በላይ ድኾችና የመኖሪያ ቤት የሌላቸው ሰዎች የታደሙ ሲሆን “በአከባቢያችን በመሰቃየት ላይ ያሉትን ወንድም እና እህቶችን ማየት ካልቻልን ወይም ደግሞ በዓለማችን የሚታየውን ከባድ ችግር መገንዘብ ካልቻልን ሕሊናችን ደንዝዙኋል ማለት ስለሆነ ጉዳዩ ልያስጨንቀን ይገባል” ማለትቻውም ታውቁኋል።

ድኾች ተጨባጭና ውድ የሆኑ ሰዎች ናቸው እንጂ ጥቅም መስጠት እንዳቆመ ያረጀ ቁስ አይደሉም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የማያልፉትን እግዚኣብሔርና ባልንጀሮቻችን በሕይወታችን ከፍተኛ ዋጋ ልንሰጣቸው ይገባል ካሉ ቡኋላ በእለቱ ወንጌል ላይ እንደተጠቀሰው ይህ አሁን ያለንበት ባዚሊካ እንኳን ሳይቀር ሃላፊ ነገር ነው ብለዋል።

ዛሬ በዓለማችን በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ የሚገኘውን ብክነት በተመለከተ ቅዱስነታቸው እንደገለጹት “ሊወደዱ የሚገባቸው የሰው ልጆችን ችላ በማለት ቁሳቁሶችን ለማምረት ብቻ ከፍተኛ ትኩረት ለመስጠት የሚደረገው ተግባር መንፈሳዊነትን ለመቀየር የሚደረግ ክፍተኛ ጥረት ምልክት ነው” ካሉ ቡኋላ እድገትና ልማት በሚታይባት ዓለማችን የሰው ላጆች የሚያገኙት ጥቅም ቀስ በቀስ እየቀነሰ መምጣቱ ይህም ጉዳይ አሁን በእኛ ዘመን የሚታይ አሳሳቢና እርስ በእርሱ የሚጋጭ አስገራሚ ነገር ነው ብለዋል።

“በእያንዳንዱ ቤት ፍትህ የሌለ ከሆነ በባለጸጎች ቤት ሰላም ሊኖር አይችልም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከልብ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ያለፍርሃት መመልከት እንድንችልና ልባችንን እውነተኛ ወደ ሆነው እሴት መመለስ እንድንችል ይረዳን ዘንድ እግዚኣብሔር ፀጋውን እንዲሰጠን መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዛሬ በመላው ዓለም የሚገኙ ካቴድራሎች እና መንፈሳዊ የንግደት ሥፍራዎች ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት እየተጠናቀቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት የምሕረት በሮቻቸውን እየዘጉ ይገኛሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቻው ዐይኖቻችንን የእኛን እርዳታ ለሚፈልጉ ጎሬቤቶቻችን እንዳይዘጋ ፀጋውን ይሰጠን ዘንድ እግዚኣብሔርን መማጸን ይገባል ካሉ ቡኋላ ልቦናችንን በማታለል፣ በፍርሃት፣ በስልጣን ጥማትና በቅንጦት እንዲሁም የሰው ልጆችን ኩራትና ፍርሃትን መተንበይ ከምያስችለን የአምልኮ መንፈስ በማንጻት ዐይኖቻችንን ለእግዚኣብሔር በመክፈት ይገባናል ብለዋል።

የምሕረት አምላክ የሆነውን በእምነትና በእርግጠኛነት በመመልከት “ፍቅር መቼም ቢሆን የሚያልቅ ነገር አለመሆኑን” መማር ያስፈልጋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ተስፋችንን በማደስ ለተጠራንበት ትክክለኛ ዓላማ መቆማችንን በማረጋገጥ ለማያልፈው ሕይወትና ከእግዚኣብሔርና ከሌሎች ጋር በሕብረት በመቆም ማለቅያ የሌለውን ደስታ ለመቋደስ መራመድ ያስፈልጋል ብለዋል።

ለየት ባለ ሁኔታ ለተረሱና ለተገለሉ “እንደ አልዐዛር” በየቤቶቻችን ደጃፍ ላይ ለሚገኙ ወንድም እና እህቶቻችን ዐይኖቻችንን መክፈት ይኖርብናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያናችንም እንድንተገብረው የምትጠይቀን ነገር ይህንኑ ነው ብለው ወደ ራሳችን መመለስ እንችል ዘንድ እንዲረዳን እግዚኣብሔርን መለመን አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው ይህንን እንዳንፈጽም ከሚያግዱን ነገሮች፣ ከራስ ወዳድነት፣ ከስልጣን ጥማት፣ በዓለም መንፈስ እንድንታለል ከሚያደርገን ወጥመድ መላቀቅ እንድንችል ይረዳን ዘንድ እግዚኣብሔርን መማጸን ያስፈልጋል በማለት ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.