2016-11-14 16:36:00

ማርቲነዝ፥ የምሕረት ዓመት በመላ ዓለም የወንድማማችነትን መንፈስ ያነቃቃል


የዛሬ አንድ ዓመት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ባንጉይ በሚገኘው ካቴድራል ቅዱስን በር በይፋ በመክፈት ያስጀመሩት የምሕረት ዓመት የመዝጊያ ቀን በተቃረበበት በዚሁ በአሁኑ ወቅት  በትክክል በበዓለ ኢየሱስ ንጉሥ በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚከበርበት ቀን የሚጠናቀቅ ሲሆን። ስለዚሁ የምሕረት ዓመት ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ራዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት ካቶሊካዊ የተሃድሶ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለኢጣሊያ ቅንርጫፍ ሊቀ መንበር ሳልቫቶረ ማርቲነዝ፥ ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ከውጫዊ የከተሞቻችንና የህልውና ክልል ከሆነው ሰውና የዓለም ክልል የሚጀምር ትሕትና ኵላዊ ቅድስና መሆኑ የመሰከረችበት የሁሉም የምሕረት ዓመት ቅድስተ ቅዱሳን ሊባል የሚችል ቅዱስ ዓመት ነው። በሁሉም የዓለማችን ክልሎች በሚገኙት አቢያተ ክርስቲያንና ካቴድራሎች ሁሉ ቅዱስ በር የተከፈተበት ሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት ይኸንን ገቢራዊ በማድረግ በተለይ ደግሞ ስቃይ መከራ በሚታይበት ክልል በወህኒ ቤቶች በማከሚያ ቤቶች በማገገሚያ በግብረ ሠናይ ማእከሎች ሁሉ ቅዱስ በር በቅዱስ አባታችን ጥሪ መሠረት እንያዲከፍቱ ያደረገና ከፍ ብሎ ለመገኘት ዝቅ ብሎ መገኘትን ያለው አስፈላጊነት ዳግም እንዲስተዋል ያደረገ ቅዱስ ዓመት ነው ብለዋል።

በእውነቱ የምሕረት ዓመት እወጃቸው የግኑኝነት ባህል እንጂ ለያይ ግንብ እንዳይገነባ፡ ድኮችን ስደተኞች እንዲስተናገዱ፡ ድኻው ወደ ጌታ የሚያስገባ ቅዱስ በር መሆኑ ሰውን ማእከል የሚያደርግ ባህል እንዲገነባ ጌታ ለምሕረት የፈጠነ ለፍርድ የዘገየ ነው የሚለው የእምነታችን ትምህርት የጎላበትና ይኸንን መንፈስ በጥልቀት እንዲኖር ያበረታታና በዚህ የምሕረት ዓመት ወቅት ለማድረ ተረዛ ቅድስና ማወጅ የምሕረት ዓመት በባንጉይ ቅዱስ በር በመክፈት ማስጀመራቸውና ባንጉይ የዓለም መፍሳዊ ማእከል በማድረጋቸው ሁሉ በእውነቱ ምሕረትና መሐሪነት ተያይዘው የሚሄዱና መሆናቸው እንዲስተዋል አድርጓል።

ቅዱስ ዓመት የቅድስና ጸጋ የሚታደልበት ዓመት ነው። ይኽ ደግሞ በሰማይ እንዳላው ቅዱስ እንደ ሆነው አባታችሁ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ የሚለው ኩላዊ ጥሪ የሚስተጋባበት ወቅት ነው፡ ኢየሱስን ለማየት እንፈልጋለን የሚለውን ግሪካዊ ጥያቄ ከሁሉም የሚቀርብ ጥያቄ ነው። ሆኖም የእርሱ መገለጥ ልብ የማይል ጥያቄ ከሆነ መቼም ቢሆን ኢየሱስን ማየት እይቻልም። እየሱስን ማየትን በእግዚአብሔር የመገለጥ እቅድ መለኪያ ዘንድ መካተት ይኖርበታል። ዓለም ኢየሱስን ከትስብእት ውጭ ስለ ፈለገው መልስ ሳያገኝ ቅርቷል። ቅዱስ አባታችን ይኸንን በትስብእቱ የተሰጠው መልስ የምሕረት ዓመት ማእከል በማድረግ ኢየሱስን ለማየት ምን ማለት መሆኑና መልሱ የት እንዳለ በቃልና ብሕይወት እየገለጡት ነው።

ምሕረት የፍቅር ሕያውነት ነው፡ ስለዚህ ምሕረትን የማያወቅ ምሕረት ክርስቲያናዊ ፍቅር አይደለም፡ ምሕረት የፍቅር ሕያውነት ባይሆን ኖሮ እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚለው የእግዚአብሔር መለያ ባልታደልን ነበር። ጌታ ፍቅር ነው ምክንያቱም ምሕረት ነውና። መሓሪነት ወንድማማችነትን የሚያስፋፋ ጸጋ ነው፡  ይኽ የምሕረት ዓመት ወንድማማችነት መኖርን ለምንኖርበት ዓለም አቢይ ተጋርጦ ሆኖ ባለበት በአሁኑ ወቅት መኖር ያለበት እሴት መሆኑና ወንድማማችነትን መኖር የሚችል ዓለም ብቻ ነው የበለጠ ዓለምን የሚሆነው ይኽ ደግሞ በምሕረት ዓመት ተበክሯል። የምሕረት ዓመት የምሕረት መመዘኛው የእግዚአብሔር መሐሪነት እንጂ ርእሰ ብቃት ወይንም ርእሰ ቅድስና አለ መሆኑ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር ሁሉም ለብቻው ብቃት የለውም የሚል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.