2016-11-14 16:32:00

36ኛው የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ መጠናቀቅ


ሮማ በሚገኘው በኢየሱሳውያን ቅዱስ ኢግናዚዩስ ዘ ሎዮላ ቤተ ክርስቲያን የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ ሆነው በተመረጡት አባ ኣርቱሮ ሶዛ 36ኛው ጠቅላይ ምሉእ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. መጠናቀቁ ከማኅበሩ የተሰራጨው ዜና አስታወቀ፡

ኣባ ሶዛ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የቅዱስ ኢግናዚዩስ ዘ ሎዮላ የመንፈሳዊ ሱባኤ አስተንትኖ የተሰኘው ድርሰቱ መሰረት ፍቅር ነው። ይኽ ፍቅር ደግሞ የሚሰዋ የሚሰጥ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን በመላክ የገለጠው እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚለውን እግዚአብሔርነትን በሙላት የሚገልጥ ነው። ስለዚህ ይኽ ፍቅር በቃል ሳይሆን በተግባር የሚኖርና የሚገለጥ ነው፡ ፍቅር እያንዳንዱ ያለውን ሁሉና ገዛ እራሱን የሚሰጥበት ተግባር ነው።

ጦርነት በሚካሂድበት ክልል ምስክርነት የሚሰጡት ወንድሞች

ሕይወትን የሚጠይቅ ምስክርነት የሚሰጡት ጦርነትና ግጭት ባለበት ክልል የሚኖሩ የወንድሞቻችን ካህናት ምስክርነት የሚደንቅ ነው። አስደናቂነቱን ገዛ እራስ አሳልፎ መስጠትን የሚያመለክት በመሆኑ ነው፡ ጦርነት በሚያስከተው ችግር ምክንያት የሰው ልጅ ለስደት ለመፈናቀል አደጋ ይጋለጣል። የእኩልነት የፍትህ የሰላም አለ መኖር በሕዝቦች መካከል እኩልነት አለ መኖሩ ሰብአዊነታቸው አስገድዷቸው የሚሰደዱት ዜጎች ይመሰክሩታል። ስለዚህ ፖለቲካ የአስተዳደር ጥበብ የእኩልነትና የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚመራ ጥበብ ነው፡ ከዚህ ውጭ ሲሆን ፖለቲካ ትርጉም የለሽ ሆኖ ይቀራል።

ዓለማችንን በድኻው ዓይነት መታዘብ ውይንም መመልከት

የኢየሱሳውያን ማኅበር የማመዛዘን ብቃት ዓለም በድኻው ዓይነት መመልከት ከሚለው መርህ የሚመነጭ ነው፡ ስለዚህ ይኽ ደግሞ ወደ እውነተኛው ሕይወት የሚመራ መንገድ ነው። በመሆኑም ወደ ውጫዊ የከተሞቻችንና የሕልውና ክልል እንድንል የሚገፋፋን ውጫዊው ክልል የሚኖረው ችግር ስቃይና መከራ መፍትሔ እንዲያገኝ የሚያነቃቃ ነው። የኢየሱሳውያን ማሕበር ህዳሴ ከዚህ የሚጀምር ነው። ኢየሱሳዊ ሁሉን ነገር ትቶ አለ ርእዮተ ዓለምና አለ የማስመሰል ሕይወት በእግዚአብሔር ፍቅር እየተጽናና ወንጌል ለማበሰር የተጠራ ነው እንዳሉ ከማኅበሩ  የተሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.