2016-11-11 13:10:00

ቅዱስነታቸው ክርስቲያኖች እምነታቸውን ልክ እንደ ርችት ለጊዜው ቦግ ብሎ እንደ ሚጠፋ አድርጎ መቁጠር የለባቸውም አሉ


በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 1/2009 ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ክርስቲያኖች እምነታቸውን ልክ እንደ ርችት ለጊዜው ቦግ ብሎ እንደ ሚጠፋ አድርጎ በመቁጠር ለታይታ ወይም ያለማቋረጥ አዲስ ግልጸት በእምነታቸው ውስጥ ይከስታል ብሎ እንዲያስቡ ከሚያደርግ ፈታና መቆጠብ ይኖርባቸዋል በማለት በአጽኖት መግለጻቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸው መሠረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ቃል ላይ በማድረግ ፈሪሳዊያን ኢየሱስን “የእግዚኣብሔር መንግሥት መቼ ነው የሚመጣው?” ብለው በጠየቁት ጊዜ ኢየሱስም የኢግዚኣብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ትገኛለች ብሎ እንደ መለሰና ልክ እንደ አንድ የተዘራች ትንሽ ዘር ብቻውን ጊዜውን ጠብቆ ያድጋል በሚለው የወንጌል ቃል ላይ መሠረቱን አድርጎ የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸው በዚሁ ጭብጥ ላይ ተመሥርተው እንደ ገለጹት የታይታን መንፈስ በማስወገድ ዘሩ እንዲያድግ የሚያደርገው እግዚኣብሔር  ነው ብለዋል።

“የእግዚአብሔር መንግሥት ሁል ጊዜ አዲስ ነገር፣ አዲስ ግልጸት፣ አዲስ መልዕክት የምንፈልግበት፣ የታይታ ሐይማኖት አይደልም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እግዚኣብሔር በኢየሱስ አማካይነት  የተናገረው ቃል የመጨረሻው ቃል” መሆኑን ገልጸው ከእዚያ ባሻገር ያለው ነገር ሁሉ ግን የማያድግ፣ ዘላቂ የሆነ ብርሃን የሌለው፣ ወዲያው ታይቶ ወዲያው እንደ ሚጠፋ እንደ ርችት ለጥቂት ጊዜ ብርሃን ሰጥቶ ወዲያው እንደ ሚጠፋ ዓይነት ነው ብለዋል።

ብዙን ጊዜ እኛ አስገራሚ የሆኑ ግለጸቶችን በመሻት የእዚህ ዓይነቱ የታይታ እምነት ውስጥ እንዘፈቃለን በማለት ስብከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር መንግሥት ግን በታላቅ ትህትና በመኋከላችን ሆና እያደገች ትገኛለች በለዋል። የኛ ተስፋ ልክ አንድ ሰው ዘር ዘርቶ ምርት እንደ ሚጠብቅና  ዳቦ የምትጋግር አንዲት ሴት ልጡን በእርሾ ለውሳ መቡካቱን በተስፋ እንደ ምትጠባቅ ሁሉ የኛም ተስፋ የመዳን ተስፋ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ተስፋ የሚያድግ ተስፋ ነው ብለዋል።

የእግዚኣብሔር መንግሥት በሙልኋት እስኪ ገለጽ ድረስ በትዕግስት መጠባበቅ ይጠበቅብናል” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በመኋከላችን የሚገኘውን የእግዚኣብሔር መንግሥት በተግባራችን፣ በስቃያችንም ወቅት ሁሉ መንከባከብ ይጠበቅብናል ካሉ ቡኋላ እንክብካቤያችንም አንድ ሰው የዘራውን ዘር እስኪያድግ እንደ ሚንከባከብና መልካሙ ችግኝ በተደላደለ ሁኔታ ያድግ ዘንድ አረሙንም ከመልካሙ ችግኝ በእንደ ሚያጠራው ሁሉ እኛም ተስፋችንን በእዚህ ዓይነት መልኩ መንከባከብ ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው እለት ለእናንተ ማቅረብ የምፈልገው ጥያቄ “የእግዚኣብሔር መንግሥት በመኋከላችን የሚገኝ ከሆነና ሁላችንም ይህ ዘር በውስጣችን ካለ መንፈስ ቅዱስ በእዛ ውስጥ አለ ማለት ነው፣ ታዲያ እንዴት ነው ይህንን መንከባከብ የምንችለው? እንዴትስ ነው መወሰን የምችለው?፣ እንዴትስ ነው መልካሙን ተክል ከአረሙ መለየት የምችለው? የእግዚኣብሔር መንግሥት እንዲያድግ እኛ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? ብለው ጥያቄን አቅርበው ይህንን ማድረግ የምንችለው በውስጣችን ያለውን መልካም ዘር በመንከባከብ ሊሆን እንደ ሚገባውም ጨምረው ገልጸው በተስፋ ማደግ፣ ያንን ተፋም መንከባከብ ይጠበቅብናል ምክንያቱም እኛ የዳነው በተስፋ ነው ተስፋ የደኅንነታችን ገመድ ነው ተስፋ እግዚኣብሒርን በእርግጠኝነት እንድንገናኝ የሚያደርገን ነገር ነው በማለት ገልጸኋል።

“የእግዚኣብሔር መንግሥት በተስፋ ሲታጀብ ጠንካራ ይሆናል” በማለት ስከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ተስፋችን በውስጣችን እየበቀለ ከሚገኘው ዘር ጋር ማቆራኘት ይጠበቅብናል ብለው በመኋከላችን የሚገኘውን የእግዚኣብሔር መንግሥት በተግባራችን፣ በውሳኔያችን በተስፋ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ይህንን የእግዚኣብሔር መንግሥት እድያድግ ማድረግ ይጠበቅብናል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁት ስብከት ተጠናቁኋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.