2016-11-07 16:15:00

በአልባኒያ ለ38 የእምነት ሰማዕታት ብፅዕና መታወጅ ትልቅ የደስታ ምክንያት


እ.ኤ.አ. ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ከ 1945 እስከ 1974 ዓ.ም. አልባኒያ በኮሙኒዝም ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓተ መንግሥት ሥር በነበረችበት ዘመን የደም ሰማዕትነት የከፈሉት የእምነት ጀግኖች ሁለት ብፁዓን ጳጳሳት፡ 21 የሰበካ ካህናት፡ 7 የፍራንቸካውያን ማኅበር አባል ካህናት፡ 3 የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት ካህናት፡ አንድ የኢየሱሳውያን ማኅበር ዘርአ ክህነት ተማሪ፡ አራት ዓለማውያን ምእመናን በጠቅላላ 38 የቤተ ክርስቲያን ልጆች ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ቅዱስ አባታችንን በመወከል ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ብፅዕና አውጃለች።

ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ከአልባኒያና ከአልባኒያ ውጭ የመጡ በጠቅላላ ከአስር ሺሕ በላይ የሚገመቱ ምእመናን የአልባኒያ ርእሰ ብሔር ቡጃር ኒካኒ የአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር፡ የተለያዩ የአገሪቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትና የተለያዩ ሃማኖት የወከሉ የበላይ መፍሳዊ መሪዎች መሳተፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ገለጡ።

አልባኒያ 50 ዓመት በዚያ ጨካኝ ጸረ ሃይማኖታዊ ከአገሪቱ ማንኛውም እምነት ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደ ሕዝብ አለ ምንም ዓይነት መፍሳዊ ዋቢነት እንዲኖር በውስጥ ያለው ወደ ላይ ያቀናውን መፍሳዊህነት ባህርዩን ለመሰረዝ የሞከረ አልባኒያ ኢእግዚኣብሔርነት እምነት ተከታይ በማድረግ እምነትን አልክድም የሚሉትን አግሞ በማጥፋ በመግደል፡ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ያወረደው መዓትና ስደት ከባድ የቅርብ ታሪክ ትውስት መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ መሥዋዕተ ቅዳሴውን መርተው ባስደመጡት ስብከት እንዳሰመሩበት የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አያይዘው ብፅዕ አቡነ አማቶ እነዚያ ጸረ እግዚአብሔር ርእዮተ ዓለም ያነቃቃና አማኞችን ለሞት ይዳርግ የነበረው ሥርዓት የት ነው፡ መንግሥታት ያልፋሉ ሥርዓቶች ርእዮተ ዓለም ሁሉ ያልፋል የማያልፈው ግን እግዚአብሔር እርሱ በሰው ልብ ውስጥ ያሳደረው ተስፋ እምነት ፍቅር መሆኑ በቃልና በሕይወት የሰበኩት ስለ ወንጌል ስለ እምነት መሥዋዕት የሆኑት ይኸው ሕያዋን ናቸው። ሰብአዊነታቸው በሰማያዊ ቤት ቦግ ብሏል እንዳሉም አስታውቋል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት እውነት መንገድና ብርሃን የሆነውን በሕይወታቸው የመሰከሩ ምሕረት ወንድማማችነት ያስተጋቡ አሳዳጆችን ይቅር ያሉት በተለይ ደግሞ የኩታሪ ሰበካ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ግጂኒ ጸረ የአልባኒይ የኮሙኒም ሥርዓት ቅስቀሳ ታካሂዳለህ ኮሙኒዝምን ትቃወማለህ ተብለው በግርፋት በጠቅላላ ጸረ ሰብአዊ በደል ሁሉ ደርሶባቸው በዚያኑ ወቅት የአገሪቱ የደህንነት ግቢ ውስጥ በነበረው አንድ ዛፍ ላይ ለስቅላት መዳረጋቸውና ከሳቸውም ጋር ሌሎች 18 ካህናት መገደላቸው የብፁዓኑ ታሪክ የጠቀሱት ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ገልጠው የሰማዕታቱ ደሞ ይኸው በጌታ ጸጋ የቤተ ክርስቲያን ጸደይ ሆኗል። በዚያች አገር ያ ሁሉ የደረሰው ግፍና በደል እምነትን ለማጥፋ አለ መቻሉና  ምእመናን በየቤታቸው በመጸለይ መቁጸሪያ በመድገም በስውር አበይት በዓላት በዓለ ልደትና ፋሲካ በማክበር ካህናት በስውር ሕዝብን በማጽናናት እምነትን በማነቃቃት ይፈጸም የነረው የእርስ በእርስ በጌታ የመጸናናቱ ተግባር በስፋት የታየባት መሆንዋ ዛሬ በሕይወታቸው የተረፉት ካህናት ምእመናን እንደሚመሰክሩትም ብፁዕነታቸው አስታውቋል።

በመጨረሻም ብፁዕ ካርዲናል አማቶ በቅርቡ ቅዱስ አባታችን ከሰየሙዋቸው አዳዲስ ካርዲናሎች ውስጥ አንዱ በቅድሴው ስነ ሥርዓት የተሳፉት በኮሙኒም ሥርዓት ወቅት ለ 28 ዓመት እስራት የተዳረጉት የስኩታኢ ሰበካ ካህን አባ ኤርነስት ሲሞኒ የዚያ ጽኑ እምነት ምስክር ናቸው በማለትም ቅዱስ አባታችን እኚሕ ካህን ካርዲናል እንዲሆኑ እንደሸሙዋቸውም ይከንን የቅዱስ አባታችንን ውሳኔ እንደደረሳቸውም ቅዱስ አባታችን በጌታ ፈቃድ የሰጡኝ ጸጋ ነፍሳትን ለማዳን ዳግም የሰላም መሣሪያ ሆኜ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ያቀኑ ዘንድ ለመደገፍ ለማደርገው አገልግሎ አቢይ ኃይል ነው በማለት ገልጠው እንደነበርም አስታውሰው። መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው ከምን ጊዜም በበለጠ ዓለም የድህነት ብሥራት እጅግ ዛሬ ያስፈልገዋል ሲሉ ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ አድሪያና ማሶቲ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.