2016-11-07 14:02:00

ቅዱስነታቸው “በመላው ዓለም የሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የእስረኛ የአያያዝ ሁኔታን መሻሻል እንዳለባቸው ጥሪ አደረጉ።


በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 27/2009 ከ13 ቀናት ቡኋላ የሚጠናቀቀውን ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ ከተለያዩ 12 ሀገራት የተውጣጡ 1,000 የሚሆኑ ታራሚዎችና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮ ባዚሊካ በስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ ቡኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናንና የሀገር ጎብኚዎች  ከመልዐከ እግዚኣብሔር ጸሎት ቡኋላ ቅዱስነታቸው እንደ ተለመደው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በዓለም የሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ሁሉ “የህግ ታራሚዎች የሰባዊ ሁኔታ ባከበረ መልኩ” የእስረኛ የአያያዝ ሁኔታቸውን መሻሻል እንዳለባቸው ጥሪ ማድረጋቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው እንዳሳሰቡት  የወንጀለኛ መቅጫ የሕግ ሂደት ጥፋተኛውን እንዲቀጣ ማድረግ  ብቻ ላይ ያተኮረ መሆን ሳይሆን የሚጥበቅበት ነገር ግን ታራሚው በተስፋ እንዲማላ በማድረግ ወደ ማኅበረሰቡ ተመልሶ እዲቀላቀል የሚይደርግ ሊሆን እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

“ለየት ባለ ሁኔታ” አሉ ቅዱስነታቸው “ይህንን ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመትን አጋጣሚ በመጠቀም በሁሉም አገሮች ውስጥ ተገቢ የሆኑ የሲቪል ባለሥልጣናት ወደ ማረሚያ ቤት በመሄድ የአመክሮ ጊዜ ይገባቸዋል ብለው ላመኑባቸው ሰዎች ከእዚህ ህጋዊ አሰራር ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም በፈረንሳይ ተካሂዶ በነበረውን  ጉባሄ ከስምምነት ላይ የተደረሰው የአከባቢ ጥበቃ መርሀ ግብር   ከባለፈው አርብ ከጥቅምት 25/2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባር ላይ መዋሉን አስመልክተው እንደ ገለጹት “ይህ ታላቅ እርምጃ የሰው ልጆች በጋራ ፍጥረታትን ሁሉ የመጠበቅ ችሎታ እንዳላቸውና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ በሆነ መልኩ የሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሰላም እና ፍትህን ለመገንባት እንደ ሚታል ያሳየ” ጉባሄ መሆኑን ከገለጹ ቡኋላ በነገው እለት ማለትም በጥቅምት 28/2009 በሞሮኮ በማራኬክ ከተማ የሚጀመረው በአከባቢ ጥበቃ ላይ የሚመክረው ጉባሄ ለጋራ መኖሪያችን እንክብካቤ እንዲደረግ በድጋሚ እንደ ሚያሳብ ተስፋቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 26/2009 በአልባኒያ ለእምነታቸው ሲሉ የተሰው 38 ሰማዕታት የብጽዕና ማዕረግ እንደ ተሰጣቸው አስታውሰው እርሳቸው ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን እስከ መጨረሻ ድረስ ታማኝ ሆነው ለመኖር እንደ ሚፈልጉም ገልጸው ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ካስፈለገም እስራትን፣ ግርፋትን እንዲሁም ሞትን መጋፈጥ” እንደ ሚፈልጉ ገልጸው የእነዚህ ሰማዕታት አብነት በመከራችን ወቅት ሁሉ በጌታ ብርታት እንድናገኝ በመርዳት መልካም ነገሮችን፣ ይቅርታንና ሰላምን ለማምጣት እንደሚያነሳሳን ጠቅሰው መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.