2016-11-07 13:54:00

ቅዱስነታቸው "ታራሚዎች በምንም ዓይነት ሁኔታ ይቅር ልባል አልችልም" የሚለውን አስተሳሰብ ማስወገድ እንደ ሚገባቸው አሳሰቡ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 27/2009 ከ13 ቀናት ቡኋላ የሚጠናቀቀውን የልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በማስመልከት ከተለያዩ ሀገራት ለተውጣጡ የሕግ ታራሚዎች በተገኙበት በቅድስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት  ታራሚዎች ተስፋ እንዳይቆርጡ ወይም ደግሞ በምንም ዓይነት ሁኔታ ይቅር ልባል አልችልም የሚለውን አስተሳሰብ ማስወገድ እንደ ሚገባቸው ማሳሰባቸው ተገለጸ።

ከ12 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው፣ የማረሚያ ቤቶች የነብስ አባቶች፣ የማረሚያ ቤት ሠራተኞች ጋር እና የሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በመሆን መስዋዕተ ቅዳሴን መታደማቸው የታወቀ ሲሆን በእለቱ ቅዱስነታቸው ያሰሙት ስብከት መሠረቱን አድርጎ የነበረው ከሁለተኛው የመጽሐፈ መቃብያን የተወሰደውና ሰባቱ ወንድማማቾች እግዚኣብሔር እንደገና ከሞት እንደ ምያነሳቸው ተስፋ ያደርጉ እንደ ነበር በሚገልጸው ታሪክ ላይ እና ኢየሱስ ለሰዱቃዊያን አማላካችን “የሙታን አምላክ ሳይሆን የሕያዋን አምላክ ነው” ብሎ በሰጠው ምላሽ ላይ ትኩረቱን ባደረገው ስብከታቸው ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠን እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉኋል።

“ተስፋ የእግዚኣብሔር ስጦታ በመሆኑ” ልንከባከበው ይገባል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ማንኛውም ዓይነት ሰው ስህተት በሚፈጽምበት ወቅት ሁሉ፣ የአምላካችን ምሕረት በዝያኑ ልክ በመብዛት ኋጥያተኛውን ሰው ወደ ንስሐ እንዲመለስ ያነቃቃዋል፣ ይቅር ይለዋል፣ እርቅን እንዲፈጥርና ሰላምን እንዲያገኝ ያደርገዋል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት የታሳሪዎች የነፃነት እጦት የወንጀል ቅጣቱን የከፋ እንደ ሚያደርገው ጠቅሰው ይህንን እውነታ ታራሚዎች በተስፋ እስትንፋስ መወጣት እንደ ሚኖርባቸው ገልጸዋል።

እንደ አውሮፓዊያን የሥርዓተ-ሉጢርጊያ አቆጣጠር መሠረት በእለቱ የተነበበው ሁለተኛው ምንባብ የተወሰደው ሐዋሪው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች ከጻፈው መልዕክት የነበረ ሲሆን ሐዋሪያው ጳውሎስ “እግዚኣብሔርም በእኛ ተስፋ እንደ ሚያደርግ ግልጹዋል” የሚለውን በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እርሱ በምሕረት ተግባራት ስለተጠመደ እርፍት የለውም፣ እርሱም በመጻሐፍ ቅዱስ ምሳሌ ውስጥ እንደ ተጠቀሰው እግዚኣብሔር በመንገድ አጠገብ የወደቀ ልጁን መመለስ በተስፋ እንደ ሚጠብቅ አባት ዓይነት መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ስለዚህም “እግዚኣብሔር ተስፋ የሚያደርግ ከሆነ ማንም ሰው ተስፋ ሊቆርጥ አይገባውም፣ ምክንያቱም ተስፋ ወደ ፊት መግፋት የሚያስችልንን ጥንካሬ ስለሚያጎናጽፈን ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስንታቸው “ተስፋ ወደ ፊት እንድንገፋ በማድረግ ሕይወታችንን እንድንቀይር የሚያደርግ ኋይል” መሆኑን አውስተው “በተስፋ ነገን እንድንመለከት በማነሳሳት፣ በፍቅር ግድፈቶቻችንን እንድንመልከት በማድረግ አአዲስ መንገድ እንድንይዝ ይረዳናል” ብለዋል።

ታራሚ እስረኞችን እንደ ጥፋተኞች አድርጎ ሁልጊዜ መቁጠር “ግብዝነት ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው በእርሳቸው አመለካከት ማረሚያ ቤት የማገገሚያ ሥፍራ መሆኑን እንደ ሚያምኑ ከገለጹ ቡኋላ ታራሚዎች ይህንን ተገንዝበው ያለፈው ስዕተቶቻቸው “ምርኮኛ” መሆን እንደ ለለባቸው አውስተው “መቼም ቢሆን ይቅር ልባል አልችልም የሚለውን አስተሳሰብ ማስወገድ እንደ ሚጠበቅባቸው ጠቅሰዋል።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አስተንትኖ በራሳቸው ወይም በሚወዱዋቸው ሰዎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ  ወይም በደል ያደረሱ ሰዎች ይቅርታ ሊደረግላቸው ያስፈልጋል በሚል ጭብጥ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን ቅዱነታቸው በመከልም እንደ ገለጹት በእግዚአብሔር ብቻ ለፈወሱ የሚችሉ አንዳንድ ቁስሎች እንዳሉ ገልጸው በተጨማሪም “ግፍ ከይቅርታ ጋር በተገናኘ ጊዜ ክፉትን የፈጸሙ ሰዎች ልብ  ክፉ ነገርን ሁሉ በሚያሸንፍ ፍቅር ይማረካል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ “ቅድስት እናታችን ማሪያም ልባችሁ በተስፋ ኋይል እንድትሞላ፣ አዲስ ሕይወትን መለማመድ እንድትችሉና በሙሉ ነፃነት በመኖር ጎሬቤቶቻችሁን ማገልገል እድትችሉ ታማልዳችሁ ዘንድ እጸልያለው ካሉ ቡኋል ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.