2016-11-01 12:50:00

ቅዱስነታቸው "አብረን በተስፋ ከጥላቻ ወደ ሕብረት” የሚል ዓላማ ያነገበ 17ኛ ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን በስዊድን ጀመሩ።


ቅዱስ አባታችን ፈራንቸስኮ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ ቡኋላ በይፋ የጎበኙዋቸው 25 ሀገራት ሲሆኑ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 21/2009 የጉብኚታቸው 26 መዳረሻ የሆነችውንና 17ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኚታቸውን ለማድርግ 1,540 ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ በስዊዲን ሀገር የምትገኘውን የማልሞ ከተማን ለመጎብኘት በሮም ከሚገኘው የፉሚቺኖ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 08:20 ላይ ተነስተው የ2:40 በረራን ካደርጉ ቡኋላ በስዊዲን የሰዓት አቆጣጠር በ11:00 ላይ ማልሞ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እንደ ሚደርሱም ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በበረራቸው ወቅት  የአየር በረራ ክልላቸውን ለሚቋርጡባቸው የጣሊያን፣ የኦስትሪያና ለጀርመን እንደ ተለመደው የሚከተለውን የቴለግራም ምልዕክት አስተላልፈዋል።

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለክቡር የኢጣሊያን ሬፑብሊክ ርዕሰ ብሔር ሰርጆ ማታሬላ፣ ሮም

የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ከካቶሊክ የተለየችበትን 500ኛው ዓመት ለመዘከርና በካቶሊክ  እና በሉቴራን አብያተክርስቲያንት መካከል ለአንድነት በሚደረገው የጋራ የጸሎት ሥነ ስርዓት ለመሳተፍ የሚልውን ሐሳብ ማዕከል በማድረግ ወደ ስዊድን 17ኛውን ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ስነሳ ለእርስዎ ለክቡርነትዎና ለመላው የኢጣሊያ ሕዝብ መንፈሳዊ ደኅንነት ይቀዳጅ ዘንድ ጥልቅ በሆነ መንፈሳዊነት ጽሎት እንደማቀርብ እያረጋገጥኩኝ ሐዋርያዊ ቡራኬዬን ሳስተላልፍ ደስታ ይሰማኛል፡፡

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ኦስትሪያ ሬፑብሊክ  ብሔርዊ ምክር ቤት ርዕሰ ብሔር ኦሪስ ብረስ፣ ቪየና።

ወደ ስዊድን በማደርገው 17ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ የኦስትሪያን የአየር በረራ ክልል በማቋርጥበት ወቅት ርዕሰ ብሔር ለሆኑ ለእርስዎና  ለአገሪቱ ሕዝብ በእርስዎ አማካኝነት ልባዊ ሰላምታዮን በማቅረብ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር በሰላሙና በጽናቱ ይባርክዎት ዘንድ ጸሎቴ ነው። በመላው ሀገሪቱ ላይም መለኰታዊ ቡራኬ ይበዛ ዘንድ እማጠናለሁ።

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  ጀርመን ሬፑብሊክ ርዕሰ ብሔር ጆኣኪም ጉዋኽ፣ በርሊን።

ወደ ስዊድን በማደርገው 17ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት እግረ መንገዴን የጀርመን የአየር በረራ ክልል በማቋርበት በአሁኑ ሰዓት ልባዊ ሰላምታዬን ለእርስዎ ለክቡርነትዎና ለመላው የጀርምን ሕዝብ አቀርባለሁኝ። በመላው ሀገሪቱ ሁሉን ቻይ የሆነው የእግዚአብሔርን ቡራኬ ይበዛ ዘንድ እማጸናለሁ። ሰላሙንና ደኅንነቱንም ይሰጣችሁ ዘንድ እጸልያለሁ።

በማለት የአየር በረራ ክልላቸውን ላቋረጡባቸው ሦስት ሀገራት ርዕሰ ብሔራት እና ሕዝቦች ሁሉ ቅዱስነታቸው መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል።

የሉቴራን እና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊ እንድምታ በአጭሩ

የሉቴራን ቤተ ክርስቲያን እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር 1517 ከካቶሊክ በይፋ የተለየችበትን 500ኛ ዓመትን ለመዘከር በማሰብ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በታሪክ የመጀመሪያ የሆነው ጉብኚት ለማድረግ የተዘጋጀው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 17ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኚት አስፈላጊነትን አስመልክተው የሉቴራን ፌደረሽን ዋና ጸሐፊ ክቡር ማርቲን ጃንግ እና በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረውና የክርስቲያን ህብረት እንዲጠናከር የሚሠራው ምክር ቤት ዋና ጸኋፊ የሆኑት ካርዲናል ኩርት ኮክ ጉብኚቱን አስመልክተው በጥቅምት 16/2009 በቅድስት መንበር የህትመት ክፍል ተገኝተው በጋራ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደ ገለጹት ይህ ማለትም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ የሚያደርጉት 17ኛ ታሪካዊ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለስኬት ሊበቃ የቻለው ቀደም ሲል እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ1999 ጽድቅን የተመለከተ የማይለውጥ የነገረ መለኮት አስተምህሮ ላይ የተደረገ ማሻሻያ እና እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ2013 ደግሞ በሁለቱ አባያተ ክርስቲያን መኋከል ተሃድሶን በተመለከተ የነበረውን ሁኔታ የሚያስረዳ ታሪክ በጋራ ስምምነት “ከጥላቻ ወደ ሕብረት” (From Conflict to Communion) በሚል አርዕስት ያሳተሙት ሰንድ ለግንኙነታቸው ፈር የቀደደ እንደ ነበረና ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትን ለማቀራረብ፣  በአንድነት የሚጋሩዋቸውን የክርስትና እሴቶችን በማጎልበት አሁን በምንገኝበት ዓለማችን ሰላምና ብልጽግናን ለማምጣት ይቻል ዘንድ “አብረን በተስፋ ከጥላቻ ወደ ሕብረት” የሚለውን መልዕክት ለዓለም ለማስተጋባት ያሰበና ማረጋገጫ የሚሰጥ ጉብኚት እንደ ሚሆንም መግለጻቸው ይታወሳል።

ካርዲናል ኮክ ኩርት በመግለጫቸው እንዳስታወቁት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጉብኚት በቀዳሚነት “አብረን በተስፋ ከጥላቻ ወደ ሕብረት” የሚል ታላቅ መልዕክት ያነገበ እንደ ሆነ ጠቅሰው ከዚህ ሐሳብ ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ  3 ዋና ዋና ዓላማዎች እንዳሉት በጥቅምት 16/2009 በቅድስት መንበር የሕትመት ቢሮ ተገኝተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ይህ የመታሰቢያ በዓል በጋራ መከበሩ ወይም መዘከሩ በራሱ ታላቅ እምርታን ያስገኘ በመሆኑና የታቀደውን “አብረን በተስፋ ከጥላቻ ወደ ሕብረት” የሚለውን ግብ እንድንመታ ከፍተኛ አስተዋጾ በማድረጉ የተነሳ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ዓላማ መሆኑን ገልጸው በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ለ50 ዓመታት ያህል በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መኋከል በጋራ የሚደርገው ምስክርነት “የመጭው ጊዜ ተስፋ ነው” በሚል ሕሳቤ ስያደርጉ ለነበረው ውይይት መሠረት የጣለና ተፈጻሚ እንዲሆን የረዳ መሆኑ የሚታሰብበት እለት ሲሆን በመጨረሻም በተሃድሶ ምክንያት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መኋከል ተፈጥሮ በነበረው ቅራኔ ምክንያት በ16ኛው እና በ17ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓ አሰቃቂ ወደ ሆነ ግጭት ውስጥ በገባችበት ወቅት በተፈጠረው “የደም መፍሰስ” በመጸጸት እንደ ሚዘከርና ዳግመኛም አላስፈላጊ ወደ ሆነ ግጭት ከመግባት ይልቅ “አብረን በተስፋ ከጥላቻ ወደ ሕብረት” የሚለውን የተስፋ መልዕክት በከፍተኛ ሁኔታ ለማስተጋባት ይቻል ዘንድ ዓላማን ያነገበ ግብኚት መሆኑን ካርዲናል ኮክ ኩርት መግለጻቸውን በጥቅምት 18/2009 ባስተላለፍነው የዜና እወጃችን መዘገባችን ይታወሳል።

የተከበራችሁ አድማጮቻችን በመቀጠል በስዊዲን የምትገኘውንና ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የሚጎበኝዋትን የማልሞ ከተማን በከፊል በረዲዮ እናስቃኛችኋለን።

የማልሞ ከተማ በስዊዲን ከሚገኙ ትላልቅ ከሚባሉ ከተሞች ሦስተኛዋና የኢንዱስትሪ ከተማ ስትሆን 7,176 እስኩዌር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ያላት ከተማ ስትሆን 322,571 ከተለያዩ ከ170 ሀገራት የተውጣጡ ነዋሪዎች እንደ ሚኖሩባት እና ከእነዚህም ውስጥ 32% የሚሆኑት ውልደታቸው ከስዊዲን ሀገር ውጭ የሆነና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ስዊዲን የመጡ ሰዎች ሲሆኑ ከነዋሪዎቿ መካከል 48% የሚሆኑት ደግሞ በ2015 በተደረገው ቆጠራ መሰረት እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸውም ታውቁዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በስዊድን ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ 11 ሰዓት በማልሞ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ እንደደረሱ በስዊድን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልዑካንና የቅዱስነታቸው የሐዋርያዊ ጉዞ ሥነ ስርዓት ሓላፊ ጋር በመሆን ከአይሮፕላኑ እንደወረዱ በስዊድን የባህልና የዴሞክራስ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊቸ ባህ ኩህንከ፣ በየሉተራን ፈደራላዊት ቤተ ክርስትያን አበይት አካላት፣ በስካዲኔቪያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር፣ የስቶኮልም ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ አንደርስ አርቦረሊዩስ፣ በስዊድን የቅድስት መንበር ሐዋያዊ ልዑክ ብፁዕ አቡነ ሄንርይክ ጆሰፍ ኖዋኪ እና ተባባሪዎቻቸውና እንዲሁም   በሀገሪቱ መራሔ መንግሥት ስተፋን ሎፍቨን አቀባበል ከተደረገላቸው ቡኋላ ቫቲካንና የስዊድን ብሔራዊ መዝሙሮች ተደምጥው እንዳበቁም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.  የስዊድን ርእሰ ብሔር በኢገሎሳ ለቅዱስነታቸው ባቀረቡት የምሳ ግብዣ ላይም የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ፒየትሮ ፓሮሊን፣ በክርስቲያኖች ዘንድ አንድነት ይፈጠር ዘንድ የሚሠራው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ፣ የቅድስት መንበር ተተኪ ዋና ጸሓፊ ብፅዕ አቡነ አንጀሎ በቺዩ፣ በስዊድ የቅድስት መንበር ሐውርያዊ ልዑክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አብነ ኖዋኪ እና በስዊድን የቅዱስ አባታችን ርሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት አስተባባሪ አባ ፍረደሪክ ኤማኑአልሶን ታጅበው የምሳ ግብዣን ከተቋደሱ በኋላ  ልክ አንድ ሰዓት ከ 35 ደቂቃ ላይ በስዊድን ከሚገኙ የንጉሣን ቤተሰብ ጋር ለመገናኘት  ወደ ቤተ ንጉሥ ሕንፃ በመሄድ ከንጉሥ  ካርሎ አስራ ስድተኛና ንግሥት ሲልቪያ ጋር ተገናኝተው አጠቃላይ ውይይት አካሂደው እዳበቁም የንግጉሣኑን ቤተሰብ ተሰናብተው ከቀትር ቡኋላ ሁለት ሰዓት ከሩብ በሉተራንና በካቶሊካክ አብያተ ክርስቲያናት በጋራ በተዘጋጀው የጸሎት ሥነ ስርዓት ለመሳተፍ ሉንድ ወደ ሚገኘው ሉተራናዊ ካቴድራል ተዛውረዋል።

ሁለት ሰዕት ተኩል የሁለቱም አቢያተ ክርስቲያን የጋራ የጸሎት ሥነ ስርዓት በመዝሙር ተጀምሮ ቀጥሎም የመሓፍ ቅዱስ ንባባት ከተደምጠ በኋላ የሉተራን ዓለም አቀፍ ፈደራላዊ ማኅበር ሊቀ መንበር ክቡር አቡነ ሙኒብ ዩናን የሚከተለውን ስብከት አስደምጠዋል።

የኢየሱስ ተከታዮች በሆኑት መካከል መንፈስ ቅዱስ በመኋከላችን በዘራው ዘር አማካይነት የተፈጠረውን አንድነት ለመመስከር እዚህ በመገኘቴ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ይሰማኛል። መንፈስ ቅዱስ በማርቲን ሉተር ቃላት አማካይነት “በምድር ላይ የሚገኙ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያንትን ሁሉ በአንዱ በክርስቶስ ላይ የተመሠረተውን አንድ እምነት እንድንከተል ይጠራል፣ የሰበስበናል፣ያሰርጻል፣ ያነጻልም”። ከዛሬ 2,000 አመት በፊት ደቀ መዛሙርት እንደ ነበራቸው ዓይነት ልምድ እኛም ዛሬ በሉንድ ካቴድራልና በማልሞ ከተማ  ወቅታዊ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ተዐምር እኛንም እያጋጠመን ይገኛል።

አንድነታችንን ለመግለጽ በተሰበሰብንበት በዛሬው እለት “ዓለም እንዲያምን. . .ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ” (ዩሐንስ 17.20,21) የሚለውን የክርስቶስ ክህነታዊ ጸሎትን በማሰብ ነው። ከጥላቻ ወደ ሕብረት እየተጓዝን በመሆናችን ሦስትና አንድ የሆነውን አማላክ እናመስገናለን። ይህ ታሪካዊ ግንኙነታችን መንፈሳዊ የሆኑ ማህበራት ሁሉ አሁንም ቢሆን በከፍተኛ ግጭት ውስጥ በምትገኘው ዓለማችን የባሰውኑ ጥላቻን  ከማዛመት ተላቀው ሰላማዊ ወደ ሆነ እርቅ መመለስ እንደሚችሉ ከፍተኛ መልዕክት ያስተላለፈ ግንኙነትም ነው። መንፈሳዊ የሆኑ ሰዎች ለአንድነት እና ለእርቅ በሚሠሩበት ወቅት ሁሉ ሃይማኖት የሰው ልጆች ሁሉ ሰባዊነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረግ ይችላሉ።  እኔ ዛሬ እስካሁን  ለእኛ የቀረበውን ምስክርነት በጥንቃቄ አዳምጫለሁ። ልቤንም ሰብሮታል። ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው በአንደኛ መልዕክቱ የኢየሱስን አካል በተመለከተ እንደ ገለጸው “አንዱ የአካል ክፍል ሲሰቃይ ሌሎችም የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረውት ይሰቃያሉ፣ አንዱ የአካል ክፍል ሲከበር ሌሎችም የአካል ክፍሎች አብረውት ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ” (1ቆሮንጦስ 12.26)። ዛሬ የእያንዳንዳችሁን ምስክርነት የሰማን እኛ ሁላችን  ምንም እንኳን ከእናንተ ጋር ተሰቃይተን የነበርን ብንሆንም ቅሉ ፣እግዚኣብሔር በእናንተ አማካይነት የጎሬቤቶችን ፍላጎት ለሟሟላት ያደርገውን ብዙ መልካም ነገሮች ክብር እንሰጣለን።

እዚህ የተገኘን ካቶሊኮች እና እኛም ሉቴራን በመኋከላችን ብዙ ህብረታችንን የሚያጠናክሩ ምልክቶች ቢታዩም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ወደ ፊት እንድንጓዝ እንበረታታለን። የዛሬው ግንኙነታችን የወይይታችን ማብቂያ ሳይሆን ነገር ግን አዲስ ጅማሮ ነው። የእኛ የገራ ዓላማ በሥነ-መለኮታዊ ውይይት ውስጥ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ነገር ግን ተጨባጭ በሆነ ምስክርነት፣ በሰማዕትነትና በአገልግሎትም ጭምር እንደ ሚገለጽ እርግጠኛ ነኝ። ዓለማቀፋዊ የሉቴራን ፌደሬሽን በተፈጥሮ አደጋ፣ በፖሌቲካዊ ጭቆና፣ ሆን ተብሎ በሚካሄድ ስልታዊ የሆነ ድህነትን ማስፋፍትን ወይም ደግሞ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለመዋጋትና ሰዎችን ከስቃያቸው ለማማቀቅ በሚደርገው ጥረት ላይ ተካፋይ ትሆናለች። ካቶሊኮች እና ሉቴራን የእግዚኣብሔርን ጥሪ ተከትለው እንዴት እንደ ሚዋደዱ ለእግዚአብሔር ጥሪ መልስ በመስጠት ሉተራኖች እና ካቶሊኮች እርስ በርሳችን እንድንዋደድና ጎሬቤቶቻችንን ማገልገል መቻላችንን ይህንንም ዓለም አይቶ ያምን ዘንድ በማድረጋችን ከእርሶ ጋር ኩራት ይሰማኛል። እግዚኣብሔር ይባርኮት፣ በተጨማሪም እርስ በራሳችን ያለን ግንኙነት ሥር የያዘ ይሆን ዘንድ እግዚኣብሔር እንዲረዳን እጸልያለሁ።

በመቀጠል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚከተለውን ስብከት አስደምጠዋል

በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ እኖራለሁ” (ዮሐ. 15,4) ጌታችን ኢየሱስ ይኽንን ያለው እኛ ወደ ክርስቶስ እንቀርብ ዘንድ በመስቀል ላይ በማያዳግም ሁኔታ ገዛ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ከመስጠቱ ጥቅቲ ጊዜያት ቀደም በማድረግ በመጨረሻው የእራት ወቅት ነበር፣ ለእኛ ያለው የፍቅር ትርታና በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ ያለው የአንድነት ፍላጎት የምንሰማበት ሁኔታ ነው። እርሱ እውነተኛ ግንድ እኛ ደግሞ ቅርንጫፎች በመሆን ፍሬ ለማፍራት የምንሻ ከሆን እርሱ ከአባቱ ጋር እንዳለው ውህደት እንዲሁም እኛም በእርሱ እንድ ሆነን መገኘት ይኖርብናል።

በዚህ በሉንድ በምናደርገው ጸሎት በእርሱ ዘንድ አንድ ሆነን እንገኝ ዘንድ ያለውን የጋራው ፍላጎታችንን ለመግለጥ እንፈልጋለን። …. ጌታ ሆይ አንድ እንድንሆንና ሕይወትም እንዲኖረን በአንድ ላይ ሆነን ስኬታማ የእምነት፣ የተስፋና የፍቅር ምስክርነት እናቀርብ ዘንድ ጸጋህን ስጠን። በጌታ የሚያምኑ ወንድሞች ይህንን በወንድሞች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲቀርፍ ካለ መታከት የተለያዩ አብያተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ለአንድነት በሚያደርጉት  ያቀና ጥረት ምክንያትም ጌታን እናመሰግናለን።

ካቶሊካውያንና ሉተራናውያን በጋራ በእርቅ ጎዳና እየተጓዙ ነው። በተለይ በዚህ ... 1517 .. የተጀመረው 500ኛው ዓመት የሉተራን ህዳሴ በምናስብበት ቀን በዓለም አቀፍ ፈደራላዊ ሉተራናዊት ቤተ ክርስቲያንና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ወደ ውህደት የተጀመረው ጎዳና ያቀናው የጋራው ውይይት በላቀ መንፈስ እናበረታታውም ዘንድ ትልቅ አጋጣሚ ነው። በመካከላችን ለተፈጠረው መከፋፈልና ልዩነት እጃችንን ልንሰጥ አይገባንም። በታሪክ ለተከሰተው መስቀለኛ የልዩነት አጋጣሚ ልንሸነፍ አይገባንም። ይህንን ልዩነት ለመጠገን እድሉ አለን

የወይኑ እርሻ ባለቤት የሆነው ኢየሱስ “ቅርንጫፉ ፍሬ እንዲያፈራ የሚያደርገው ጌታ ነው” ይለናንል፡ በኢየሱስ ዘንድ ሁላችን አንድ እንድሆን ዘንድ እግዚአብሔር ይጋብዘናል፣ ይመለከተናል የፍቅር እይታውም ያለፈውን ታሪካችንን እናነጻ ዘንድ በጋራ ያንን የምንጠባበቀው የውህደት ውጤት እንቀዳጅ ዘንድ ያበረታታናል። እኛም በተራችን በፍቅርና በቅንነት መንፈስ ያለፈውን ታሪካዊ ስህተቶቻችን ሁሉን በመቀበል ምህረት ልንጠይቅ ይገባናል። እግዚአብሔር ብቻ ነው ፈራጅ። ልይነቶቻችን ከዚያ አንድ ሕዝበ እግዚአብሔር አርቆ ከተመለከተውና ከሚሻው አንድነት የሚያርቅ የፈጸምነው ስህነትት በትህትናና በቅንነት ታምነን በዚያ በየዋሁ እረኛ ጥበቃና የዋህነት በሚያንጸባርቅ መንፈስ ያንን አንድነትን የሚለው ሕዝበ እግዚአብሔር መምራት ያስፈልጋል።ባንድ በኩል የአንድነቱ ፍላጎት ያለ ቢሆንም ቅሉ በራሳችን ለመዝጋት ፈተና ተጠቂዎች መሆናችን ልናምን ይገባናል። ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ... ጥቅምት 31 ቀን 1983 .. በወቅቱ ለነበሩት የክርስቲያኖች አንድነት ጉዳይ ለሚከታተለው ማኅበር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጆሃነስ ዊለብራንድስ አስተላልፈውት በነበረው መልዕክትየእውነት እረኞች በመሆን ወደ ውህደት ማቅናት ይስፈልጋል” ያሉትን ሐሳብ ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፥ እግዚሔር የማሳው ጌታ ነው። በታላቅ ፍቅሩና ጥበቃውም ይመግባል። በእግዚአብሔር እይታ እንታይ ዘንድ እንፍቀድ።ያለፈው ታሪክ ለመለያየት የዳረጉንን ምክንያቶች ሁሉ ማስታወስ ሳይሆን ስህተቶቻችንን ለማረም በቀና መንፈስ መለስ ብለን እናንብበው።

ኢየሱስያለ እኔ ምንም ነገር ለማድረግ እትችሉም” (ዮሐ.15,5) ይለናል። እርሱ ዘወትር ወደ እንድነት የሚመራ ጥረቶታችንን ሁሉ የሚደግፈና የሚያበረታታ ነው። ልዩነታችን የብዙ ስቃይ ምክንያት ሲሆን በሌላው መልኩም አድነት አለ እርሱ እንደማይከውን አለ እርሱ ምንም ነገር ማድረግ እንደማንችል እርግጠኛነቱን እንድናስተውል አድርጎናል። የሉተር ህዳሴ የመጽሓፍ ቅዱስ ማዐከልነት ቀስቅሷል፡

የማርቲን ሉተር መንፈሳዊነት ዛሬ ለሁላችን ትልቅ ጥያቄ ሲሆን ያለ እግዚአብሔር ምንም ነገር ማድረግ እንደማይቻለን ያስታውሰናል። ሉተር በመደጋገም ያቀርበው የነበር ጥያቄምእንዴት ብየ ነው አንድ መሐሪ እግዚአብሔር እንዲኖረኝ የማደርገው?” የሚለው ሲሆን፡ ይኸንን እግዚአብሔር ምሕረት ሉተር፥  ተወለደ ሞተ ተቀበረ ሞትን አሸንፎ ተነሣ የሚለው ምሕረት ከአዲስ ኪዳን ቃል ጋር አገናኝቶታል። በመለኰታዊ ጸጋ ብቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ማንኛውም የሰው ልጅ ለሚሰጠው ምላሽ እግዚአብሔር በምሕረት እንደሚቀድም ነው የሚያረጋግጥልን።

በጋራ የትብብር መንፈስ ወደ ፊት እንጓዝ ዘንድ አደራ እላለሁ። ስለዚህ የድኅንነት  ትምህርት የሰው ልጅ ህልውና በእግዚብሔር ፊት ያለው አሰፈላጊነት የሚያመለክት ነው።

ኢየሱስ በአባቱ ፊት ስለ እኛ የሚማጸን አስታሪቂያችን ነው። ስለ ደቀ መዛሙርቱ አንድነት ወደ አባቱ ይጸልያል (ዮሐ. 17.21) ይኽ ነው የሚይጽናናን ወደ ውህደት እናቀና ዘንድ የሚደግፈን …. እንደ ክርስቲያኖች ዓለም ከእኛ የሚጠባበቀው የምሕረት ምስክርነት የዚያ የዕለት በዕለት ተመኩሮዎች በማድረግ በመካከላችን የምንኖረው የመማማር፣ የመታደስና ይቅር የመባባል ተግባር የሚለካው ምሕረት ነው። በጋራ በተጨባጭና በሐሴት የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር በማገልገል የእግዚአብሔር ምሕርት አብሳሪዎች እንድንሆን ይጠበቅብናል።

ሉተራናውያንና ካቶሊካውያን በዚህች ሉተራናዊት ካቴድራል በጋራ እንጸልያለን እግዚብሔር ምንም ነገር ለማድረግ እንደማንችል ግንዛቤው አለን። በእርሱ ላይ አንድ የሆነ ሕያውነት እንድንኖር የእርሱ እርዳታን እንጠይቅ። በጋራ ቃሉን ወደዚያ የዋህነትና ምሕረት ወደ ሚሻው ዓለም ሁሉ እንድናደርስ የእርሱ ጸጋ ያስፈልገናል።

ቅዱስነታቸው ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠንቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.