2016-10-26 14:44:00

ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ለእኛ ነጻነትን ስለሰጠንና በገርነት መሐሪዎች እንድንሆን ስለጠራን ግትርነትን ማስወገድ ይገባል አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 14/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት እግዚኣብሔር ለእኛ ነጻነትን ስለሰጠንና በገርነት መሐሪዎች እንድንሆን ስለጠራን ከመጠን ያለፈ ግትርነትን ማስወገድ እንደ ሚገባ ማሳሰባቸው ተገለጸ።

 

በቀኑ ከሉቃስ ወንጌል (13.10-17) በተወሰደው ምንባብ ላይ ኢየሱስ በምኩራብ እያስተማረ በነበረበት ወቅት አንዲት ጎባጣ ሴትን በሰንበት ቀን በፈወሰበት ወቅት የምኩራቡ አለቃ ኢየሱስ  በሰንበት ቀን በመፈወሱ ተቆጥቶ እንደ ነበር በሚያወሳው ምሳሌ ላይ ተመርኩዘው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “የእግዚኣብሔርን ሕግ የሚያመልክተንን ማንግድ መከተል አስቸጋሪ ነው” ማለታቸውም ተግልጹአል።

በማቴዎት ወንጌል የተጠቀሰው ተመሳሳይ ምሳሌ ላይ እንደ ተጠቀሰው ኢየሱስ በሰንበት ቀን ሴቲቷን ፈውሶ ስለነበር” የምኩራብ አለቃ የነበረ ሰው በጣም ተናዶ እንደ ነበረ ከገለጹ ቡኋላ ምክንያቱም ኢየሱስ የእርፈትና የአምልኮ ቀን በሆነው የሰንበት ቀን የእግዚኣብሔርን ህግ ጥሶ በእለቱ ፈውስ በመፈጸሙ በመሆኑ እንደ ነበረ ገልጸዋል።

“ኢየሱስ ለምኩራብ አለቃው ‘እናንተ ፈሪሳዊያን!’ በማለት መልስ ስጥቶ እንደ ነበር” በማውሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ሁሌም ቢሆን ኢየሱስ ህግን ከመጠን በላይ በሆነ ሁኔታ ለሚከተሉ ሰዎች ዘወትር የሚሰጠው ምላሽ እንደ ሆነ አውስተው “ህግ” አሉ ቅዱስነታቸው “ህግ ነጻ አውጥቶን የእግዚኣብሔር ልጆች እንድንሆን ነው የተሰጠን እንጂ ባሪያዎች ልያደርገን አይደልም” ብለዋል።

ከመጠን በላይ በሆነ ሕግ ውስጥ መደበቅ ሌላ ነገር ከጀርባው እንዳለ ያሳያል! ለእዛም ነው ኢየሱስ ‘ፈሪሳዊያን!’ የሚለውን ቃል የተጠቀመው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ከማንኛውም ከመጠን ያለፈ ግትርነት ጀርባ በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ሌላ ተጨማሪ ነገር ይኖራል” ብለው ገርነት፣ መልካምነት፣ ፍቅር፣ ይቅርታ ናቸው እንጂ የእግዚኣብሔር ስጦታዎች ግትርነት አይደልም ብለዋል።

በማንኛውም ሁኔት ግትርነት አደር ባይ የሆነ ሕይወት እንዲኖረን ያደርገናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም እየጎለበተ በሚሄድበት ወቅት ወደ በሽታነት ይቀየራል ብለዋል።

ግትርና መልካም የሆኑ ሰዎችን በሚያጠቅ በሽታ የሚሰቃዩ ሰዎች ይመስላል በማለት አስተያየት በመስጠት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የሚሆንበት ምክንያት የእግዚኣብሔር ልጆች የሚያደርጋቸውን ነጻነት በማጣታቸው መሆኑን ገልጸው “በእግዚኣብሔር የህግ መንገድ መጓዝ አያውቁበትም” ብለዋል።

“በሆነ ነገር ውስጥ ተሸሽገው ህግጋትን ስለሚከተሉ ብቻ ጥሩ ሰዎች መስለው ይታያሉ፣ ፈሪሳዊያን ወይም ደግሞ የታመሙ ሰዎች ናቸው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ግትር በመሆናቸው ብቻ የእግዚኣብሔርን ሕግ የተከተሉ ለሚመስላቸው ወንድሞች እና እህቶች መጸለይ ይገባል” ካሉ ቡኋላ እግዚኣብሔር አባታችን እንደ ሆነ ይሰማቸው ዘንድና ምሕረትን ማድረግ እንደ ሚወድ፣ መልካም፣ የዋህ፣ መሆኑን ተረድተው እግዚኣብሔር ባሳየን እነዚህን ባሕሪያትን በመላበስ መጉዝ ይችሉ ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል ብለው ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.