2016-10-21 16:13:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቡርኪናፋሶ ርእሰ ብሔር ተቀብለው አነጋገሩ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ለይፋዊ ጉብኝት አገረ ቫቲካን የገቡትን የቡርኪና ፋሶ ርእሰ ብሔር ሮክ ማርክ ክርስቲያን ኮብረን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ። በተካሄደው ክሌአዊ ግኑኝነት ይላል የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ፥ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው መልካም ግኑኝነት ተበክሮ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቡርኪና ፋሶ የምትሰጠው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ለየት ባለ መልኩም በጤና ጥብቃና በሕንጸ ዘርፍ በዋነኛነት በመጥቀስ ይክ አገልግሎት የቡርኪና ፋሶ መንግሥትና ሕዝብ የሚያደንቀው መሆኑ ከቡርኪናፋሶ መራሔ መንግሥት ተመስክሯል በማለት በሁለቱ አገሮች መካከል በዓለም አቀፍ ሕግ ላይ የታመነ ክሌአዊ ግኑኝነት እንዳላቸውም በተካሄደው ግኑኝነት መበከሩ አስታውቋል።

በቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ ዕርቅ ያለው አስፈጊነት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት ትብብር ስለ ወጣቶች ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልኩም ሥራ አጥነት የሚያስከትለው ኅብረ ተግዳሮች ቀርቦና በትክክል ለይቶ ለመፍታት የሚያስችል ሂደት ይለይ ዘንድ የተካሄደው ግኑኝነት እንዳሰመረበት የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ከዚህ ብሔራዊ አቀፍ ጉይዳ ውጭ ወቅታዊነት ባላቸው ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ መካሄዱ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.