2016-10-20 09:57:00

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮኋቸው "የተራበን መመገብና የተጠማን ማጠጣት” የወንጌል ትዕዛዝ ነው አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 9/2009 በቅዱስ ጴትሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተሰበሰቡ ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው “የተራበን መመገብና የተጠማን ማጠጣት” በሚል የወንጌል ጭብጥ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ ተገለጸ።

ክቡራን እና ክቡራት አንባቢዎቻችን በመቀጥል ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 9/2009 በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ያስተላለፉትን አስተምህሮ እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድታነቡት እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ! “የጋራ ጥቅም” ተብሎ የሚጠራው አሰተሳሰብ ከሚያስከትለውን መዘዝ አንዱ ለሌሎች ማሳየት የሚገባንን ደግነትን በመተው ሰዎች ራስቸውን በራስቸው ለሌሎች ዝግ እንዲሆኑ አድርጉዋል። እነዚህ ጊዜያዊ ሕይወት ሞዴሎችን በማቅረብ ለማታለል የሚያደርገው ጥረት ከተወሰነ ጊዜ ቡኋላ ፈንድቶ ግልጽ የሚወጣ ጉዳይ ሲሆን ይህም ጉዳይ የሚሆንበት ምክንያት ልክ ሕይወታችን እንደ ፋሽን በየወቅቱ የሚቀያየር በመሆኑ ነው። እንዲህ መሆን ግን የለበትም! እውነታውን መቀበል መቻል አለብን፣ እየሆነ ያለውን ነገር መጋፈጥ አለብን፣ በአብዛኛውም አጣዳፊ የሆኑ ሁኔታዎችን መጋፈጥ ያስፈልጋል። ለእዚህም ነው የምሕረት ሥራዎች ሁሉ እንደ ርሃብ እና ጥማት ላሉ ነገሮች መልስ እንዲሰጥ፣ የተራበን አብላ ይላል የተራቡና የተጠሙ ብዙ ሰዎችም አሉ! የመገናኛ ብዙኋን በምግብና በወሃ እጥረት የሚሰቃዩ ሰዎችን በተለይም ሕጻናት እየደረሰባቸው ያለውን መከራ ብዙን ጊዜ አሳይተውናል።

አንዳንዴ ከምናያቸው ዜናዎችና ጥቂት ምስሎች ላይ ተመርኩዘው ከሕዝብ ከሚቀርበው አስተያየት በመነሳት አልፎ አልፎ አንድነታችንን የሚገልጽ እርዳታ ይደረግ ዘንድ ዘመቻዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። በእዚህም ረገድ በደግነት የሚሰጠው ስጦታ የሰዎችን ሕይወት ከመከራ ለማውጣት አስችልዋል። የእዚህ አይነቱ እገዛ ምንም እንኳን በቀጥታ ተሳታፊዎች ባያደርገንም አስፈላጊነቱ ግን የጎላ ነው።  ነገር ግን በመንገድ ላይ በምንጓዝበት ወቅት በችግር ላይ ያለ አንድ ሰው በምናገኝበት ወቅት ወይም ደግሞ አንድ ድኸ ሰው ቤታችን መጥቶ በራችንን በምያንኳኳበት ወቅት የሚሰማን ስሜት በጣም የተለየ ነው ምክንያቱ በአንድ የተለቪዢን ምስል ፍለፊት ሳይሆን ያለነው ተጨባጭ በሆነ በአንድ ሰው ፊት በመገኘታችን ምክንያት ነው። በእኔና በእርሱ ወይም በእርሷ መኋከል ብዙ ክፍተት የለም፣ በዚህም ምክንያት ጥያቄ ይጭርብናል።

በጥቅሉ ድኽነትን ስናስብ ጥያቄን እንድናነሳና እንዲሁም ቅሬታ እንዲሰማን ያደርጋል ነገር ግን ድኽነትን የአንድን ሰው ወይም ሴት የአንድን ሕጻን ሥጋን ለብሶ በምናይበት ወቅት በጣም ያሳዝነናል! ስለዚህም እኛ የተቸገሩ ሰዎችን እንድንሸሽ የሚያደርገን አባዜ፣ እንዳንቀርባቸውና የችግረኛውን ተጨባጭ ሕይወት እንዳናይ የያዘን ይህ የጊዜው ፋሽን ነው። በእዚህም ምክንያት ከእዚህ እውነታ እንርቃለን።

በእዚህ ረገድ ምን አይነት ስሜት ነው የሚሰማን? መንገዴን ቀይሬ በሌላ በኩል ነው የማልፈው? ወይም ደግሞ ቆም ብዬ ላናግረውና በእርሱ ገጽታው ውስጥ እራሴን ለማስገባት ነው የምሞክረው? ይህንን በምታደርግበት ወቅት “ከአንድ ድኸ ሰው ጋር የሚነጋገር ይህ ሰው እብድ ነው” የሚል ሰው አይጠፋም። ይህንን ሰው በአንድ መንገድ ይሁን በሌላ ልቀበለውና ከእዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ በቶሎ ነፃ ይሆን ዘንድ እረዳዋለው? ምን አልባትም እኮ እርሱ የሚጠይቀን የሚበላ ወይም የሚጠጣ ነገር ሊሆን ይችላል። እስቲ ለተወሰን ጊዜ እናስብ. . .በቀን ስንት ጊዜ ነው “አባታችን ሆይ” ብለን የምንጸልየው ወይም ደግሞ በጸሎቱ ወቅት የምንደግመውን “የእለት እንጀራችንን በእየለቱ ስጠን” የሚሉትን ቃላት በማስተዋል ነው የምንደግመው?

በመዝሙረ 136 “በሕይወት ላለ ሰው ሁሉ ምግብን የሚሰጥ” እግዚኣብሔር ነው ይላል። ርሃብ በጣም አስቸጋር ነገር ነው። በጦርነት ወይም በርሃብ ውስጥ ያለፈ ሰው በይበልጥ ርሃብ ምን መሆኑን ይረዳዋል። ነገር ግን ይህ ልምድ ወይም እውነታ በእየለቱ ከተትረፈረፈ ሕይወትና ከምግብ ብክነት ጋር አብሮ እየኖረ ይገኛል። “ወንድሞቼ ሆይ ሰው እምነት አለኝ ቢል፣ ነገር ግን እምነቱን በሥራ ባይገልጥ ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ለምስሌ የሚለብሱትና የሚመገቡት የሌላቸው ወንድምና እኅቶች ቢኖሩ፣ እናንተ ልኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሳትሰጡአቸው ‘በሰላም ሂዱ! ይሙቃችሁ! ጥገቡ!’ ብትለሉአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?’ (ያዕቆብ 2.14-17) የሚለው የሐዋሪያው የያዕቆብ መልዕክት ሁልጊዜም ቢሆን የማይረሳ ነው ይህንን የሚያደርግ ሰው መልካም ሥራን እየሰራ አይደለም፣ የምሕረትንና የፍቅርን ተጋባርም ልፈጽም አይችልም። መቼም ጊዜ ቢሆን የእኔን እገዛ የሚፈልግ የተራበ ወይም የተጠማ ሰው አለ። በዚህ ሁኔታ ምንንም ልወክል አልችልም። ይህ ድኸ ሰው የእኔን እርዳታ፣ የእኔን ቃል፣ የእኔ ለእርሱ ትኩረት መስጠቴን ማወቅ ነው የሚፈልገው፣ ሁላችንም በእዚህ ጉዳይ ልንሳተፍ ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ይህንን መልካም ተግባር መፈጸም እንድንችል እግዚኣብሔር እንዲያግዘን መጸለይ ይገባል ብለው የእለቱን አስተምህሮ አጠንቀአል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.