2016-10-17 17:05:00

የቅድስና አዋጅ ለሰባት የእምነት ሰማዕታትና ለድኾች ቅርብ በመሆን ሕይወታቸውን እንደ ጌታ ፈቃድ ለኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች


ገና የ 14 ዓመት ዕድሜ ታዳጊ ወጣት እያለ በመክሲኮ እ.ኤ.አ. በ 1928 ዓ.ም. እምነቱን እንዲክድ በሚዘገንን ሁኔታ ሲገረፍና ሲደበደብ እምነቴን አልክድም በማለቱ ምክንያ ለሕልፈ የተዳረገው ሰማዕት ኾሰ ሳንቸስ ደል ሪዮ ከተገደለ በኋላ በኪሱ ውስጥ “ለመንግሥተ ሰማይ ለሁላችህ መልካም ሥፍራ ላዘጋጅላችሁ ቃል እገባለሁኝ። ልጅሽ ኾሴ የካቶሊክ እምነቴንና ለክርስቶስ ንጉሥና ለቅድስት ድንግል ማርያም ዘጓዳሉፐ ያለኝ ፍቅር ላለ መካድ አንገቴን ለካራ ከማለት ወደ ኋላ አልልም” የሚል ለእናቱ የጻፈው መልእክት መገኘቱ የዚህ ቅዱስ የታሪም ማሕደር ውስጥ ተዘግቦ ይገኛል።

አዲሱ ቅዱስ ኾሴ ሳንቸዝ ደል ሪዮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 28 ቀን 1913 ዓ.ም. በሚቾአካን ክልል የተወለዱ እንደነበሩም ከቅዱሳኑ ማኅደር ለማረጋገጥ ተችሏል።

በላሳል ለሚታወቀው የክርስቲያን ወንድሞች ማኅበር አባል ወንድሞ ሳሎሞኔ ለክለርክ እ.ኤ.አ. ህዳር 14 ቀን 1745 ዓም. በፈረንሳይ የተወለደ በ 1792 ዓ.ም. በፈረንሳይ አብዮት ወቅት ጊዜ ባመጣው ለሚቀያየረው የምድር ባለ ሥልጣናት ገዛ እራሱን ሳያንበረክክ የእግዚአብሔር ነኝ በማለት እምነቴን አልክድም ጌታን ከማበሰር ወደ ኋላ አልልም በማለት እምነቱን ወደ ጎብ በማድረግ ምሉ ተአዝዞነት ለፈረንሳይ አብዮት ሕገ መንግሥት ሁሉም ውሉደ ክህነት ግድ የሚለው መንግሥት ለደነገገው ውሳኔ እምቢ ቃለ መሃላዬ ለጌታ ነው በማለቱ ምክንያ የደም ሰማዕትነት የተቀበለው።

ኩራ ቡረቸሮ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው መጋቢት 16 ቀን 1840 ዓ.ም. በአርጀቲና ኮርዶባ ክልል የተወለደው ኾሴ ጋብሬል ደል ሮሳሪዮ ብሮቸሮ አርጀቲናዊ ካህን የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ሊቅነት ያስመሰከረ እ.ኤ.አ.  በ 1800ና 1900 ዓመታት ለድኾች የጌታን መጽናናትን በማድረስ የታመሙትን በደዌ እና በተለያዩ በሽታዎች የተጠቁት ማንም ደራሽ ያልነበራቸውን ዜጎች የጌታ ፍቅር በማካፈል በማገልገል ለጌታ ያለን ፍቅር መመዘኛው የሆነው ለወንድም የሚኖረው ፍቅር ነው ሲል ኢየሱስ የሰጠውን ጥሪ በሙላት እይኖረ፡ የታመሙትን በማገልገል ላይ እያለ በደዌ በሽታ ተጠቅቶ ዓይኑ እስከ መታወር የደረሰ ነገር ግን ድኾችን በማፍቅር እምነትን የመሰከረ እ.ኤ.አ. ጥር 26 ቀን 1914 በሰማይ ቤት የተወለደ።

የስፐይ ተወላጅ ማኑኤል ጎንዛለስ ጋርሲያ እ.ኤ.አ. በ 1940 ዓ.ም በሰማይ ቤት የተወለደው የፈዋሹ አሃድነት ቅዱስ ቁርባን ማኅበርና የቅዱስ ቁርባን ዘናዝራዊ ልኡካን ደናግል ማኅበር መሥራች የቅዱስ ቁርባን አምልኰና ስግደ ባማነቃቃት የተተዉት የተዘነጉት መንበረ ታቦት ጳጳስ” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው።

 የብረሺያ ካህን የቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም ልጆች ማኅበር መሥራች የኢንዳስትሪው አብዮት በተነቃቃበት ወቅት ድኾችንና ለተገፉትን ሁሉ እምነትና ሙያዊ ተግባር በማስተማር እራስ በመቻል አቅም ብቁ ሆነው ከድኽነት ገዛ እራሳቸውን እንዲያላቅቁ በማድረግ ዓላማ በማገልገል ይኸንን አገግሎት የሚኖሩ የካህናትና ወንድሞች ማኅበር የመሠረተ በ 1847 ዓ.ም. በሰማይ ቤት የተወለደ ብፁዕ ሉዶቪኮ ፓቮኒ ( እ.ኤ.አ. 1784-1849)።

በኢጣሊያ የሳሌርኖ ሰበካ ካህን ብፁዕ አልፎንሶ ማሪያ ፉስኮ (እ.ኤ.አ. 1839-1910) የቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ ደናግል ማኅበር መሥራች የኢጣሊያ አንድነት መረጋገጥ ጋር ተያይዞ ተጋብቶ በነበረው ችግር ምክንይት የተረሱት ለብቻቸው የተተዉት የገጠር ነዋሪዎች በግብርና ለሚተዳደሩት ሁሉ ቅርብ በመሆን እንዲሁም በጎዳና ተዳዳሪነት አደጋ ለተጋልሰጡት ሁሉ ቅርብ በመሆን በማነጽና ከወደቁበት ችግር በማትረፍ ምሉእ ሰብአዊና መንፈሳዊ ሕንጸት እንዲያገኙ ያደረገ፡

በመጨረሻም ቅድስና ከታወጀላቸው ውስጥ ሰባተኛይቱ በሰቂለ ኅሊና መንፈሳዊነት የታወዱ የቅርመሌሳውያን ደናግል ማኅበር አባል ገና በ 26 ዓመት እድሜያቸው እ.ኤ.አ. በ 1906 ዓ.ም. በሰማይ ቤት የወተወለደች ስትሆን። የደረሰባት ከባድ ሕመም በተስፋ መቁረጥ ለወደቁትና ስለ ሁሉም ነፍሳት ድህነት መሥዋዕት በማድረግ የኖረች ኤሊዛበታ ዘቅድስት ሥላሴ ይገኙበታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.