2016-10-17 13:55:00

ቅዱስነታቸው ማንኛውም ሰው ድኽነትን ለማጥፋት በሚደረገው የትግል ሂዴት ውስጥ እንዲሳተፍ ጥሪ አደረጉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 6/2009 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ በሕይወታቸው ባከናውኑት ታላቅ የእምነት ጽናት ምንያት ለቅድስና ማዕረግ የበቁትን ሰባት አዳዲስ ቅዱሳን በሾሙበት ወቅት ይህንን ታላቅ የእምነት በዓልን ለማክበር ለተገኙ ከ80,000 በላይ የሚሆን ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚወች ካሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ቡኋላ ካደርጉት የመልዐክ እግዚኣብሔር ጸሎት በመቀጠል ለመላው ዓለም ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ገለጹት ማንኛውም በጎ ፈቃድ ያለው ሰው ድኽነትን ለማጥፋት በሚደረገው የትግል ሂዴት ውስጥ በመሳተፍ ቤተሰብንና በተለያዩ ቦታዎች ተቀጥረው የሚሠሩት ሰዎች የሥራ ዋስትናቸው ይጠበቅ ዘንድ ጠንከር ያለ ፖሌቲካዊ ሕግ ተፈጻሚ እንዲሆን ልያግዙ እንደ ሚገባ ጥሪ ማድረጋቸው ታውቀ።

በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 7/2009 ዓ.ም ታስቦ የሚውለውን “ዓለማቀፍ ድኽነትን የማጥፋት ቀን” ምክንያት በማድረግ መልዕክታቸውን የስተላለፉት ቅዱስነታቸው “ግብረገባዊና ኢኮኖሚያዊ ኋይሎቻችን በማስተባበር የሰውን ሕልውና የሚፈታተነውን፣ ሰዎችን የሚይሰቃየውንና በጣም ብዙ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን የሚገለውን ድኽነትን በጋራ በመዋጋት ለተቀጣሪ ሠራተኞችና ለቤተሰብ ያለንን አጋርነት ልንገልጽ”ታስፈልጋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት ከልብ በመነጨ መልኩ ለሰላም ጸሎት እንዲደርገ ብድጋሜ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በጣም ረጅም የሆነ ጎዞን በማድረገ በእለቱ የቅድስናን ማዕረግ የተቀበሉትን 7 ቅዱሳንን ለመዘከር በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መገኘታቸው አመስግነው በተለይም ደግሞ ይህንን ታላቅ በዓል ለመታደም ኦፊሴላዊ በሆነ መልኩ ሀገሮቻቸውን ወክለው የተገኙ የአርጄንቲና፣ የእስፔን፣ የፈረንሳይ፣ የጣሊያንና የመክሲኮ ተወካዮች ለየት ባለ መልኩ አመስግነው፣ የእነዚህ የ7 አዳዲስ ቅዱሳን የሕይወት ምሳሌና እጹብ ድንቅ የሆነ አማላጅነት እያንዳዳችን በተሰማራንበት የሥራ መስክ ይረዳን ዘንድ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን መልካም አገልግሎትና ለማኅበረስቡም መልካም አገልግሎት የምናውልበት” ይሆን ዘንድ መጸለይ እንደ ሚገባ ገልጸውና ቡራኬን ስጥተው የእለቱን መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.