2016-10-14 14:06:00

ናይጀሪያ፥ በቦኮ ሓራም አሸባሪያን እጅ ታግተው ከነበሩት 270 ሴቶች ውስጥ 21 ነጻ ተለቀቁ


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. በናይጀሪያ ኪቦክ ከተማ ሰርጎ በገባው ቦኮ ሓራም የተባለው አሸባሪው የምስልምና እምነት አክራሪው ኃይል እጅ ታግተው ከነበሩት 270 ሴቶች ተማሪዎች ውስጥ 21 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ነጻ መለቀቃቸው አንሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይኸ አንሳ ያሰራጨው ዜና በማያያዝ ለቫቲካን ረዲዮ ዘገባውን ያጠናቀሩት የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሮበርቶ ፒየርማሪኒ እነዚህ በአሸባሪው ኃይል የተጠለፉት ወጣት ተማሪ ሴቶች ብዙዎቹ በአሸባሪያኑ በደረሰባቸው የወሲብ ዓመጽ ምክንያትም የልጆች እናቶች መሆናቸው ቢቢሲን ጠቀስው ከገለጡ በብኋላ ለእነዚህ ተማሪዎች ነጻ መለቀቅ ምክንያት የናይጀሪያ የደህንነትና ጸጥታ አባላት የስዊዘርላንድ መንግሥትና ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር ተዋሽነት ከአሸባሪያኑ ጋር የተካሄደው ድርድር መሆኑ የናይጀሪያው መንግሥት 21 ነጻ መለቀቃቸው ይፋ ባደርገበት ቀን ማስታውቁ ገልጧል።

የናይጀሪያው መንግሥት ሴቶችን ነጻ ለማስለቀቅ በአቡጃን ወህኒ ቤት ተይዘው ከነበሩት አራት የቦኮ ሐራም አባላትን ነጻ እንዲለቅ ከአሸባሪያኑ ወገን የቀረበውን ጥያቄ ያረካ መሆኑ ጠቅሰው ነጻ የተለቀቁት ሴቶች ወዲያውኑ አቢጃን እንደደረሱም ለህክምናና ከደረሰባቸው የሥነ አእምሮ ጭንቀት ለማላቀቅ የተሟላ የሕክናና የሥነ አእምሮ ድጋፍ ሊያገኙበት ወደ የሚችሉበት ማእከል መዛወራቸው ቢቢሲ ያሰርጨው ዜና ጠቅሰው ከገለጡ በኋላ አክለው ነጻ የተለቀቁ ሴቶች ሕጻናት የታቀፉና አንዳንዶቹም ነፍሰ ጹር እንደነበሩ አስታውቋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.