2016-10-14 13:54:00

ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በዝክረ 500ኛው ዓመተ ቅዋሜ የሉተር የኅዳሴ ቤተ ክርስቲያን መሳተፍ ለአሃድነት አቢይ ድጋፍ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን የገቡትን በማእከላዊ ጀርመን አንሃልት ክልል የመጡትን የሉተራናዊት ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መጋብያንና ምእመናን ተቀብለው የአንሃልት ሉተራናዊት ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ መንበር ዥዋኪም ላይቢግ ነጋድያኑን በመወክል ቅዱስ አባታችን ላደረጉባቸው አቀባበል አመስግነው፡ በጠቅላላ ያንን ማርቲን ሉተር የተወለደበት ክልል በተመለከት ባህሉ አምነቱ መልክኣ ምድራዊ አቀማመጡ ምስ ተመስሎውን አስተዋውቀው እንዳበቁ፡ ቅዱስ አባታችን በመቀጠል ዝክረ 500ኛው ዓመት የተሃድሷዊት ሉተራናዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዋሜ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለአሃድነት ታልሞ በሚደረገው የጋራ ውይይት ያለው አስተዋጽኦ በጥልቀት ተንትኗል።

ስለ ተካሄደው ግኑኝነትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስደመጡት መልእክት ዙሪያ በኢጣሊያ የወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያን ፈደረሽን ሊቀ መንበር መጋቤ ሉካ ማሪያ ነግሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ቅዱስነታቸው ያስደመጡት ቃል በእውነቱ እጅግ አስፈላጊና ተቀባይነት ያለው የአቢያተ ክርስትያን የሚከውኑት አሃድነት ላይ ላተኮረው የጋራው ጉዞ የላቀ ድጋፍ ነው። በእርግጥ የአቢያተ ክርስቲያን የጋራው ውይይት ዛሬ የተጀመረ ባይሆንም ቅሉ አሁን የደረሰበት ደረጃ ስንቃኝ በእውነቱ በጀ የሚያሰኝ ነው።  በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል በቲዮልጊያ መስክ በጋራው ብዙ  ውይይት ተከውኗል። አሁንም ብዙ የሚለያይ ጉዳይ አለ ስለዚህ እስካሁን ድረስ የተጨበጥውው መልካም ውጤት ገና ብዙ መሠራት እንዳለበት የሚያመላክት ነው ብሏል።

አንድ የጋራ ምስክርነት ያለው አስፈላጊነት

እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. የጋራው የካቶሊክና የኢጣሊያ ሉተራናዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል “ካለ መግባባት ወደ ሱታፌ” በሚል ርእስ ሥር በጋራ ያጸደቁት ሰነድ  ዝክረ 500 ዓመት የተኅድሶ ሉተራናዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዋሜ ላይ እይታውን በማኖር በመከናወኑም በእርግጥ በቲዮሎጊያ ዘርፍ እየተደረግ ባለው ውይይት ወደ ፊት መባሉ ያረጋግጣል። ሰነዱ በስሜታዊነት ላይ ሳይሆን በቲዮሎጊያዊ አመክንዮ ላይ  የጸና በመሆኑ ያለው ጠንካራ ልዩነቱን ወደ ጎን ሳያደርግ የሚያገናኛቸው የጋራው ነጥብ በማጤን የሚከናወን የጋራው ውይይት ወጤት እንደሚኖረው አሰምሮበታል። እውነትም ነው። ሉተራናዊ ኅዳሴ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለዳግመ ግኝት አቢይ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ሌላው ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስደመጡት ቃል እንዳሉትም ሃይማኖትና ግብረ ገብ ከማኅብራዊ ሕይወት የሚነጥልና በማኅበራዊ ጉዳይ ሃይማኖትም ግብረ ገብም ረብ የለውም የሚል ባህል እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ለዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የጋራ ክርስቲያናዊ ምስክርነት አጅግ አስፈላጊነቱን አስምረውበታል፡ በምዕራቡ አለም የክርስትያኖች መከፋፈል በኤውሮጳ ልቅ አለማዊነት እንዲስፋፋ እድል የሰጠ ነው የሚመስለው ካሉ በኋላ አያይዘው፥ ዝክረ 500ኛ ዓመት ሉተራናዊ ኅዳሴ እያንዳንዱ አቢያተ ክርስቲያን ህሊናውን የሚመረምርበትና ርእሰ ህየሳ የሚያደርግበት ጥሩ አጋጣሚም ነው፡ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በስዊድን ሉንድ ከተማ ቅዱስነታቸው በተገኙበት ስነ ሥርዓት ዝክረ 500ኛው ዓመት የሉተራናዊት የኅዳሴ ቤተ ክርስቲያን ቅዋሜ ይከበራል። ይኽ አጋጣሚም ሉተራናዊ ኅዳሴ እምነትን በመደገፉና በማስፋፋቱ ዘርፍ የሰጠው አወንታዊ አስተዋጽኦ እውቅና የሚያሰጥም ይሆናል። ለተደረሰው መከፋፈልም ጌታን ይቅርታ የምጠይቅበት ሁኔታ ይፈጥርልናል። በዚህ የተዘክሮ በዓል ቅዱስነታቸው ለመሳተፍ መፍቀዳቸው በካቶሊክና በሉተራናዊት የኅዳሴ ቤተ ክርስቲያን መካከል ለአንድነት ታልሞ ለሚደረገው የጋራው ውይይት አቢይ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ስለዚህ ዝክረ በዓሉ አሃድነትን የሚያነቃቃ ነው ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.