2016-10-12 14:41:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ጌታ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድብን ለሌሎች ሰዎች በምናደርገው ምሕረት ላይ ተመርኩዞ" ነው አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፋርንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 2/2009 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተሰበሰቡ ምዕመናንና የሀገር ጎቢዎች ያሰላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በማቴዎስ ወንጌል ላይ ሲሆን ይህም ጌታ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድብን ለሌሎች ሰዎች በምናደርገው ምሕረት ላይ ተመርኩዞ መሆኑን የገለጸበት ምዕራፍ እንደ ነበር ታወቀ።

የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን በመቀጠል ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያስተላለፉትን አስተምህሮ ጠቅላላ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተከበራችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ።

በእዚህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ልጁ በሆነው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለይም ደግሞ ሥጋን ለብሶ በመገለጡና የኢየሱስ ተከታዮች እንደ ሞሆናችን መጠን በተግባር “እንደ አማላካችን መሐሪዎች እንድንሆን” ያስችለን ዘንድ በእግዚኣብሔር ምሕረት ላይ አስተንትኖን አድርገናል። በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታ በመጨረሻው ቀን የሚዳኜን እርሱ በሚገለጽበት ማለትም ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን በምናሳየው ምሕረት ላይ ተመርኮዞ ነው። የኢየሱስ ቃል ምርኩዝ ያደረገው ልማዳዊ በሆኑ ሰባት “አካላዊ” የምሕረት ተጋባራት ላይ ሲሆን እነዚህም የተራበን ማብላት፣ የተጠማን ማጠጣት፣ የታረዘን ማልበስ፣ የባዕድ ሀገር ሰውን መቀበል፣ የታመመን መጎብኘት፣ የታሰረን መጠየቅና ሙታንን መቅበር ናቸው። ቤተ ክርስቲያን በበኩሏ በማመንታት ላይ የሚገኙትን መምከር፣ ያልተማሩ ሰዎችን ማስተማር፣ ኋጥያተኞችን መገሰጽ፣ የተጎሳቆሉትን ማጽናናት፣ በደልን ይቅር ማለት፣ ክፉ ነገር የሚፈጽሙብንን ሰዎች በትዕግስት ማለፍና በሕይወት ላሉ እና ለሞቱ ሰዎች መጸለይ የሚሉት ደግሞ ሰባቱ “የመንፈስ” የምሕረት ተግባራትን ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች። ሕያው  የሆነ የእምነት መግለጫ ስለ ሆነው እነዚህ ተግባራት ብዙን ጊዜ መፈጸም የሚኖርባቸው በጸጥታ እና ቀላል በሆኑ ምልክቶች ነው። እንደ እማሆይ ትሬዛ ያሉ ቅዱሳን እንደ ሚያሳዩን ምሕረታዊ የሆነውን የክርስቶስን ፊት በመግለጽ በአከባቢያችን የሚታየውን ልማድ ቀይረዋል። እነዚህን ነገሮች ሁልጊዜም በማስታወስ በእየለቱ በተግባር ላይ ለማዋል እንጣር። በማለት ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

ቅዱስነታቸው ካስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ቡኋላ ያስተላለፉት መልዕክት በሶሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ በድጋሚ ጥሪ ማድረጋቸውም የታወቀ ሲሆን በእለቱም ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልዕክታቸው አጉልተው እንደ ገለጹት “እኔ በሶሪያ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሰለባ ከሆኑ ሰዎች ጋር ያለኝን አንድነት ለመግለጽ እፈልጋለሁ” ካሉ ቡኋላ “በጣም አስቸኳይ በሆነ መልኩ፣ በልመናም ቢሆን ያለኝን አቅም ሁሉ ተጠቅሜ በእዚህ ጦርነት ውስጥ የድርሻቸውን የሚጫወቱትን ሁሉ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉና በእዚህ ወጥመድ ውስጥ የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎችን በተለይም ሕጻናትን ከእዚህ አሰቃቂ የቦንብ ድብደባ ማውጣት ይቻል ዘንድ ብያንስ ብያንስ ለተወሰነ ጊዜም እንኳን ቢሆን የተኩስ አቁም በአስቸኳይ ይደረግ ዘንድና ይህም እንዲከበር የሰላም ጥሪዬን በድጋሚ አቀርባለሁ” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.