2016-10-11 13:00:00

ቅዱስነታቸው በመስከረም 29/2009 ለ17 ጳጳሳት የካርዲናልነትን ማዕረገ መስጠታቸውን ገልጹ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመስከረም 29/2009 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ ቡኋላ በተካሄደው የመልዕከ እግዚኣብሔር ጸሎት በመቀጠል ባስተላለፉት መልዕክታቸው ከ11 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ 17 ካርዲናሎችን መሾማቸውን አስታወቀው የእነዚህም 17 ካርዲናሎች ሹመት በመጭው ጥቅምት 9/2009 በእለቱ በይፋ በሚዘጋው ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ጋር መሳ ለምሳ በመሆነ እንደ ሚከበር ገልጸዋል።

ከእነዚህ ከተሾሙ 17 ካርዲናሎች መካከል 13ቱ እድሜያቸው ከሰማንያ ዓመት በታች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ይህም የቅዱሱ ጴጥሮስ ተከታይ የሆነውን ቀጣዩን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ እንዲሁም የመመረጥ መብትን እንደ ሚያጎናጽፋቸው የተገለጸ ሲሆን ቀሪዎቹ 4ቱ ግን እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ በመሆኑ ከላይ የተጠቀስውን ማለትም የመምረጥ እና የመመረጥ መብት እንደ ማይመለከታቸውም ታውቋል። አዲስ የተመረጡ 17 ካርዲናሎች ነባሩን የካርዲናሎች ቁጥር በአጠቃላይ 211 እንደ ሚያደረሰው የታወቀ ሲሆን ከእነዚህ 211 ካርዲናሎች መካከል እድሜያቸው ከ80 በታች የሆኑና ቀጣዩን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ እንዲሁም የመመረጥ መብት ያላቸው 111 ብቻ መሆናቸውም ታውቁኋል።

ቅዱስነታቸው አያይዘውም እንደ ገለጹት እነዚህ አዲስ የተመረጡ ካርዲናሎች ከአምስት አህጉራት መወጣጣታቸውን ገልጸው ከእነዚህም መኋል 3 የአሜሪካ ሊቀ ጳጳሳት፣ 1 የሞሪሼስ እና 1 የባንግላዲሽ ሊቀ ጳጳሳትም እንደ ሚገኙበት ታውቋል።

የእነዚህ አዲስ የተመረጡ ካርድናሎች ስም ዝርዝር እንደ ሚከተለው ነው።

  1. ሊቀ ጳጳስ ማሪዮ ዜናሪ ከጣሊያን

  2. ሊቀ ጳጳስ ዴውዶኔ ዛፓላኢንጋ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ

  3. ሊቀ ጳጳስ ካርሎስ ኦዞሮ ሲዬራ ከእስፔን

  4. ሊቀ ጳጳስ ሴርጆ ዳ ሮካ ከብራዚል

  5. ሊቀ ጳጳስ ብላዝ ጄ. ኩፒክ ከአሜርካ

  6. ሊቀ ጳጳስ ፓትሪክ ዲ ሮዛሪዮ ከባንግላዲሺ

  7. ሊቀ ጳጳስብላታዛር ኤንሪክ ፖራስ ቻርዶዝ ከቬንዙዌላ

  8. ሊቀ ጳጳስ ጆዜፍ ዴ ከዜል ከቤልጄየም

  9. ሊቀ ጳጳስ ማውሪስ ፒያት ከሞሪሽዬስ

  10. ሊቀ ጳጳስ ከቪን ጆሴፍ ፋሬል ከአሜሪካ

  11. ሊቀ ጳጳስ ካርሎስ አጉየር ሬተስ ከሜክሲኮ

  12. ሊቀ ጳጳስ ጆን ሪባት ከፓፗዋ ኒው ጊኒ

  13. ሊቀ ጳጳስ ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን ከአሜርካ

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት 13 ካርዲናሎች የቅዱስ ጴትሮስን ተከታይ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት ያላቸው ሲሆን ከታች የተዘረዘሩት ደግሞ እድሜያቸው 80 በላይ በመሆኑ ቀጣዩን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ ወይም የመመረጥ መብት የሌላቸው መሆኑም ታውቁኋል።

  1. ሊቀ ጳጳስ አንቶኒ ሶቴር ፈርናዴዝ በማለዢያ የሚገኘው የካዋላ ላምፑር ሊቀ ጳጳስ

  2. ሊቀ ጳጳስ ሬናቶ ኮርቲ በጡረታ ላይ የሚገኙ የቀድሞ በጣሊያን የሚገኘው የኖቫራ ሊቀ ጳጳስ

  3. ሊቀ ጳጳስ ሰባስቲያን ኮቶ ኮሀራይ በጡረታ ላይ የሚገኙ በለሴቶ የሚገኘው የሞሃለ ሆኤክ ሊቀ ጳጳስ

  4. ሊቀ ካህናት ኤርነስት ሲሞን በልባኒያ የሚገኘው የሸኮዴር ፑልት ሊቀ ካህን

የዓለም የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ካርዲናሎች ስም ዝርዝር

 

አህጉር

 

እድሜያቸው 80 በታች የሆኑና ቀጣዩን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ ወይም የመመረጥ መብት ያላቸው ካርዲናሎች

 

 

አጠቃላይ የካርዲናሎች ብዛት

 

በዓለም የሚገኙ የካቶሊክ  እምነት ተከታዮች በመቶኛ

ቁጥር

በመቶኛ (%)

ቁጥር

በመቶኛ (%)

አውሮፓ

52

46.8%

107

50.71%

26.37%

ደቡብ አሜሪካ

11

9.91%

25

11.85%

27.87%

ሰሜን አሜሪካ

13

11.71%

23

10.90%

16.11%

እስያ

13

11.71%

22

10.43%

11.49%

አፍሪካ

13

11.71%

21

9.95%

12.63%

መካከለኛው አሜርካ

6

5.41%

8

3.79%

4.79%

ኦሽኒያ

3

2.70%

5

2.37%

0.74%

ቶታል

111

100%

211

100%

100%

 

ሰንጠረዥ 1. የዓለም የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ካርዲናሎች ስም ዝርዝር

ምንጭ: ምብጭ፣ Wikipedia, Cited:  11-10.1016. 11:27. List of Cardinales.

 www. en.wikipedia.org/wiki/List_of_living_cardinals

 

 

ከ80 ዓመት እድሜ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አሀጎር ካርዲናሎች

 

ሥም

 

ሀገር

 

የልደት ቀን እ.አ.አ

 

እድሜ

 

ሀገረ ስብከት

 

ሹመቱን የሰጠው ር..

 

የሹመት ቀን እ.አ.አ.

ካ. አርሊንዶ ጎሜዝ ፉርታንዶ

ካፔ ቬርዴ

15-11-946

66

ሳንዲያጎ ዲ ካፔ ቨርዴ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮ

በየካቲት 14/2015

ካ. ጂን-ፒየር ኩታዋ

አይቬሪኮስት

22/12/1945

70

አብጃን

ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮ

በየካቲት 22/2014

ካ. ላውሬንት ሞንሴንጉዎ ፓሲኒያ

ኮንጎ ዲሞክራቲክ ርፖብሊክ

7/10/1939

77

የኪኒሻሳ ሊቀ ጳጳስ

ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ

ህዳር 20/2010

ካ. አልፍሪድ ናፒር

ደቡብ አፍሪካ

13/04/1941

75

የደርባን

ሊቀ ጳጳስ

ር.ሊ.ጳ ዩሐንስ ሁለተኛ

የካቲት 21/2001

ካ. ጆን ኑጄ

ኬንያ

 31/12/1944

71

የናይሮቢ ሊቀ ጳጳስ

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ

ህዳር 24/2007

ካ. ጆን ኦናዬካን

ናይጄሪያ

29/01/194

72

የአብጃን ሊቀ

 ጳጳስ

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ

ህዳር 24/2012

ካ. ፊሊፔ ናኬሌንቱባ

ቡርኪና ፋሶ

29/01/1945

71

የኦጋደጉ ሊቀ ጳጳስ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ

የካቲት 22/2014

ካ. ፖሊካርፕ ፔንጎ

ታንዛኒያ

5/09/19/44

72

የዳሬሰላም ሊቀ ጳጳስ

ር.ሊ.ጳ. ዩሐንስ ጳውሎስ

የካቲት 21/1998

ካ.ሮበርት ሳራ

ጊኒ

15/08/1945

71

የመለኮታዊ አምልኮ ማህበር አለቃ

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ

ህዳር 20/2010

ካ. ቴዎዶሬ አድሬዬን ሳር

ሴኔጋል

28/11/1936

79

የቀድሞ የዳካር  ሊቀ ጳጳስ

ር.ሊ.ጳጳስ በነዲክቶስ 16ኛ

ህዳር 24/2007

ካ. ብርሃነየሱስ ደምረው ሱራፌል

ኢትዮጲያ

 14/11/1948

68

የአዲስ አበባ ጳጳስ እና የኢት.ካ.ቤተ. ሊቃነ ጳጳሳት

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ

የካቲት 14/2015

ካ. ፒተር ቱርክሰን

ጋና

 11/10/1948

68

የሰላምና የፍትህ ቢሮ ዋና ኋላፊ

ር.ሊ.ጳ. ዩሐንስ ጳውሎስ 2ኛ

ጥቅምት 21/2003

ካ. ጋብሪኤል ዙቤር ዋኮ

ሱዳን

የካቲት 27/02/1941

75

የካሩቱም ሊቀጳጳስ

ር.ሊ.ጳ. ዩሐንስ ጳውሎስ

ጥቅምት 21/2003

 

ምንጭ፣ Wikipedia, Cited: 11-10.1016. 11:27. List of Cardinals.

 www. en.wikipedia.org/wiki/List_of_living_cardinals








All the contents on this site are copyrighted ©.