2016-10-08 09:34:00

ቅዱስነታቸው ቀኖና "በየቀኑ በሙልኋት ለመንፈስ ቅዱስ እራሱን ክፍት ያደረገ የእግዚ/ር ግልጸት ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በመስከረም 27/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ-ቅዳሴን ማሳረጋቸው የታወቀ ሲሆን በእለቱም ባሰሙት ስብከት እውነተኛ ቀኖና ከህግ ጋር እንደ ተቆራኜ ክችች ያለ አስገዳጅ ርዕዮተ ዓለም ማለት አለመሆኑን ገልጸው ነገር ግን እራሱን ሁል ጊዜ ለበለጠ ግልጸት ያመቻቸ እና በየቀኑም በሙልኋት ለመንፈስ ቅዱስ እራሱን ክፍት ያደረገ የእግዚአብሔር ግልጸ ነው ብለዋል።

በእለቱ የተነበበው ምንባብ የሚያወሳው መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስትያንን ወደ ፊት በታላቅ ብርታት እስከ ዓለም ፍጻሜ እንድትጓዝ የሚያደርጋት “ታላቅ የአምላክ ስጦታ” መሆኑን ሲሆን መንፈስ አሉ ቅዱስነታቸው “ ቤተ ክርስትያን ‘ወደ ፊት እንድትጓዝ’ የሚያስችላትን ገፀ-ባሕሪ” የሚጫወተውም እርሱ መሆኑን ገልጸው “ያለ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስትያን እራሷን በእራሷ በፍርሃት ዝግ ታደርጋለች” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በተያያዘ ሊጠቀሱ የሚችሉ ሦስት ዝንባለዎች እንዳሉ ጠቅሰው የመጀምሪያውም ልክ ሐዋሪያው ጳውሎስ የገላቲያን ሰዎች ‘በኢየሱስ ሳይሆን ሕግን ብቻ በመፈጸም እንድናለን’ በማለት “ለሕግ ብቻ እውቅናን መስጠት ይገባል” የሚለውን እምነታቸውን መውቀሱን አውስተው እነርሱም ማለትም የገላቲያ ክርስትያኖች “በጣም ግትሮች” እንደ ነበሩም አስታወሰዋል።

እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች ናቸው ኢየሱስን ስያጠቁት የነበሩ እና ኢየሱስም እናንተ ግብዞች በማለት. . .

“ይህ ከሕግ ጋር ያለን ከፍተኛ ቁርኝት መንፈስ ቅዱስን ችላ ይላል። የኢየሱስ አዳኝነት ከመንፈስ ቅድሱ ጋር  ተቆራኝቶ ወደ ፊት የሚጓዝ መሆኑን አያረጋግጥም። ሕግ ብቻ ጠቃሚ እንደ ሆነም ያሳያሉ። በእርግጥም እወነት ነው ልንከተላቸው የሚገባን ሕግ-ጋቶች አሉ፣ ነገር ግን ሊተገበሩ የሚገባው እግዚአብሔር በሚሰጠን ፀጋ እነዚህም በእርሱ ልጅ እና በመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሆን ያስፈልጋል። በእዚህ ረገድ ሕግን በሚገባ መረዳት ይቻላል። ነገር ግን የልጁን እና መንፈስ ቅድሱን በሕግ እይታ ውስጥ በማስገባት አታሳንሱት። የእነዚህም የገላቲያ ሰዎች ችግር ይህ ነበር፣ መንፈስ ቅዱስን ችላ በማለታቸው ወደ ፊት መጓዝን አላወቁበትም። ይህን እና ያንን መሥራት ያስፈልጋል ቢሚሉ አስተሳሰቦች እራሳቸውን ከርችመው ዘግተዋል። በአብዛኛውም እኛ በእንደነዚህ ዓይነት ፈታና ውስጥ እንገባለን” ብለዋል ቅዱንስታቸው።    

የሕግ አዋቂዎች “በአስማት ሐሳብ ወስጥ ይገኛሉ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው. . .

“ምክንያቱም ርዕዮ-ዓለም እንደ አስማት ነው። ቅድሱ ጳውሎስ የዛሬውን መልዕክቱን የጀመረው ‘እናንተ ሞኞች የገላቲያ ሰዎች! አስማት እንደተደረገበት ሰው ስለ ምን ፈዘዛችሁ?’ በርዕዮተ-ዓለም የሚሰብኩ ሁሉ አስማት እንደ ሚያደርጉ ግልጽ ነው፣ ምንም ጥርጥር የለውም፣ ነገር ግን ተመልከቱ ግለጸት ብሩዕ አይደለም አይደል? የእግዚአብሔር ግልጸት እለት በእለት በተጨማሪነት የምናገኘው ነው፣ ሁል ጊዜም በሂደት ላይ ነው። ገባችሁ? አዎን! እንደ መስታወት ግልጽ ይሆናል! የሚገልጽልንም እርሱ ነው፣ በሂደት የምናገኘው ነገር ነው። ነገር ግን እወነት በእጃቸው መዳፍ ቁጥጥር ሥር ብቻ ነው ብለው የሚያምነ ሰዎች ቸልተኞች ብቻ አይደሉም። ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደሚለው “ምክንያቱም አስማት እንዲደረግባችሁ ስለፈቀዳችሁ እናንተ ሞኞች ናችሁ!” እንዳለቸውም አስታውሰዋል።

ሁለተኛው አመለካከት መንፈስን ከማሳዘን የሚመነጭ መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህም የሚፈጠረው በክርስትና ሕይወታችን ወደ ፊት ይመራን ዘንድ እርሱ እንድያነቃቃን በማንፈቅድበት ወቅት መሆኑን” ገልጸው “በስነ-መልኮት ሕግ ሳይሆን ነገር ግን በመንፈስ ነፃነት እንዲመራን በማንፈቅድበት ወቅት” እንደ ሚከሰት አውስተው በእዚህም ረገድ አሉ ቅዱስነታቸው “ለብ እንዳለ ሰው እንሆናለን” ካሉ ቡኋላ “ያልተገባን ክርስትያኖች” ወደ ሚያደርገን መንገድ እንወድቃልን ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ምንም ዓይነት ተግባር በእኛ ውስጥ ስለማያከናውን መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

በሌላም በኩል ሦስተኛው ምልከታ “እራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት ማድረግንና መንፈስ ቅዱስ ወደ ፊት እንዲመራን ማድረግ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው  ይህም ሐዋሪያት በጴንጤቆስጤ ቀን እንዳገኙት ዓይነት ብርታት ነው፣ እራሳቸውን ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት በማድረጋቸው የተነሳ   ፍርሀታቸው ተወግዶ ነበር” በማለት ገልጸዋል። “የኢየሱስን ቃል ለመረዳት እና ለመቀበል” አሉ ቅዱስነታቸው “እራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ኋይል ክፍት ማድረግ አስፈላጊ ነው” ካሉ ቡኋላ አንድ ሰው ወይም ሴት እራሱን ወይም እራሷን ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት በሚያደርጉበት ወቅት በንፋስ ኋይል እንደ ሚቅዝፍ ጀልባ ወደ ፊት ሳያቆም ይጓዛል” ካሉ ቡኋላ ነገር ግን ይህ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ለመንፈስ ቅዱስ እራሳችንን ክፍት ማድረግ ስንችል ብቻ መሆኑን ገልጸው ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.