2016-10-06 14:03:00

በ2018 የሚካሄደው 15ኛው መደበኛ የጳጳሳት ጉባሄ ምርዕ ሐሳብ “ወጣቱ ትወልድ፣ እምነት እና በጥሪ መጽናት"አንደ ሆኑ ታወቀ


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 2018 በሚካሄደው 15ኛው የጳጳሳት መደባኛ ጉባሄ  መርዕ ሐሳብ “ወጣቱ ትወልድ፣ እምነት፣ ጥሪን ለይቶ ማወቅ” የሚሉ ጭብጦች ሐሳቦች በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ መመረጣቸው ታወቀ። በዛሬው ቀን ከቫቲካን በተገኘው መረጃ መረዳት እንደተቻለው ቅዱስነታቸው እነዚህን መርዕ ሐሳቦችን ከመምረጣቸው በፊት እንደ ተለመደው ከጳጳሳት ጉባሄ፣ ከምስራቃዊ አብያተ ክርስቲያናት ጋር እና የተለያዩ መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አለቆች ጋር ተመካክረው የደረሱበት ውሳኔ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም በአስራ አራተኛው መደባኛ የጳጳሳት ጉባሄን የተካፈሉ አባቶችን እና በዚሁ ጉባሄ ላይ የተሰጡትን ገንቢ ሐሳቦችን ከግምት ያስገባ እንደሆነም ተጠቅሱኋል።

ይህ የተመረጠው መርዕ ሐሳብ “ቤተ ክርስቲያን ለወጣቶች የሚሰጠውን ሐዋሪያዊ አገልግሎትን ለማጠናከር በማሰብ” መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ይህም መርዕ ሐሳብ መሰረቱን በቅርቡ በቤተሰብ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ያለፈውን ጉባሄ ላይ እና ቅዱስነታቸው በጸሐፉት አሞሪስ ላይቲሲያ (የፍቅር ሐሴት) በሚለው ድዕረ- ሲኖዶስ ሐዋሪያዊ ስነ-ምዕዳን ላይም የተመረኮዘ ነው። ከቫቲካን የተሰጠው መግለጫ ጨምሮ እንዳብራራው “ይህ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 2018 የሚካሄደው 15ኛው መደበኛ የጳጳሳት ጉባሄ “ወጣቶችን በእድገት ጎዳናቸው ወደ ተፈለገው የብስለት ደረጃ እንዲደርሱ ለማገዝ እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት የሕይወታቸውን ትክክለኛ አቅጣጫ እንዲያገኙ እና ደስታንም ይጎናጸፉ ዘንድ እርሳቸውንም እግዚአብሔርን እና ሰዎችን ለመገናኘት ክፍት እንዲያደርጉ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያንን እና ሕብረተሰብን ለመገንባት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ለማስቻል በማሰብ መሆኑም ተገልጹኋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.