2016-10-05 16:57:00

የኵላዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. 2016 ዓ.ም. የጥቅምት ወር የጸሎት ሃሳብ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. 2016 ዓ.ም. ጥቅምት ወር የጸሎት ሃሳብ ምን መሆን እንዳለበት ባስተላልፉት ድምጸ ራእይ መልእክት የመገናኛ ብዙኃን ሙያተኞችና ጋዜጠኞች የግኑኝነት ባህል ገንቢዎችና ጋዜጠኝነት የግኑኝነት ባህል አገልግሎት ይሁን በማለት ሙያዊ እውነትን ከማክበርና ከአቢይ የሥነ ምግባራዊ ሃላፊነት የተነቃቃ ይሁን እንዳሉ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው የመገናኛ ብዙኃን የግኑኝነት ባህል ገንቢዎችና የግኑኝነት ባህል አገልግሎት መሆን አለበት የሚል ሃሳብ በተደጋጋሚ የሚያሰላስሉት መሆኑም ገልጠው፡ የመገናኛ ብዙኃን እንዴት ለግኑኝነት ባህል አገልግሎት ማዋል ይቻላል የሚል ጥያቄ በማቅረብ ስለዚህ ለሕዝቦችና ለማህበራዊ ጥቅም የሚያገለግል መሆኑ ታውቆ በዚህ ዓላማ ዙሪያ ሲጠመድ በእውነቱ የግኑኝነት መሣሪያ ይሆናል። የመገናኛ መሣሪያ የሚያጋጭ የሚያጣላ የሚለያይ ከሆነ ሙያው መሠረታዊ ትርጉምን አጥቶ የሚለያይ መሣሪያ ይሆናል ብለው ሁሉም የመገናኛ ብዙኃን ባለ ሙያዎችና ጋዜጠኞች የጥቅምት ወር የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሃሳብ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን እውነትን ከማክበርና ከሥነ ምግባራዊ ኃላፊት የተነቃቃ አገልግሎት ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን ገልጠው። ጋዜጠኞና የመገናኛ ብዙኃን ይኸንን የጸሎት ሃሳብ እንዲያስፋፉ አደራ ካሉ በኋላ አያይዘው የመገናኛ ብዙኃን እያንዳንዱ ሰው ገዛ እራሱን እያንዳንዱ ባህል ገዛ እራሱን ክፍት በማድረግ ሌላውን ለመቀበልና ከሌላው ጋር ለመገናኘት የሚያነቃቃ መሣሪያ ይሁን እንዳሉ ጂሶቲ ገልጠዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.