2016-09-26 16:47:00

የመልአከ እግዚአብሄር ጉባኤ አስተምህሮ ፍጻሜ ያስተላለፉት መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደወትሮው ዕለተ ሰንበት እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከውጭና ከውስጥ የመጡ መንፈሳዊ ነጋዲያን ያሳተፈ የሚያሳርጉት ጸሎተ መልእከ እግዚአብሔር ቀደም በማድረግ የሚለግስቱ የመልአከ እግዚአብሔ ጉባኤ አስተምህሮ እ.ኤ.አ. መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ለግሰው እንዳበቁ እ.ኤ.አ. መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ጀርመን ዊዩርዝቡርግ በዳቻው የናዚው ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ለሞት ይዳረግበት በነበረው የመቅሰፍት ሰፈር በእምነታቸው ምክንያት ለሞት የተዳረጉት የእግዚአብሔር አገልጋይ አባ ኤንገልማር ኢዩዛይቲንግ የማሪያንሂል ልኡካን ማኅበር አባል ቤተ ክርስቲያን በይፋ ብፅዕና እንዳወጀችላቸው አስታውሰው፡ አባ ኢዩዛይቲንግ ጥላቻን በፍቅር ጨካኝነትን በገርነት የተቃወሙ አብነታቸው ፍቅርን እንመስክር ዘንድ ሁካታ ባለበት ሁሉ ተስፋን እንመሰክር ዘንድ ይርዳን ብለው፥

ባለፈው ሰኞ እ.ኤ.አ. መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በመክሲኮ በሚገኘው በቨራክሩዝ ግዛት ተጠልፈው ለሞ የተዳረጉት አባ አለኾ ናኦሪና አባ ኾሴ አልፍረዶ ኺመነዝ እንዲሁም እ.ኤ.አ. መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚቾአካን ግዛት የተገደሉትን አባ ኾሴ አልፍረዶ ሎፐዝ ጉይለን በማሰብ የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን ተልእኮና በዓለም ደረጃ ጭምር ሐዋርያዊ ግብረኖልዎና ባህላዊ ትኩረት በሚጠይቀው የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ለአገሪቱ ኅብረተሰብና ቤተሰብ እንዲሁም የሕይወት ባህል ዙሪያ ለሚሰጡት አገልግሎት በጸሎቴ ቅርብ በሆኔ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ። በአገሪቱ የሚታየው በቅርቡ በተለየ መልኵ የካህናትን ሕይወት ለሞት በመዳረግ ዓመጽ ምክንያት የሚሰቃየው ተወዳጁ የመክሲኮ ሕዝብ የአገሪቱ ውሉደ ክህነት በጸሎቴ ህልው ነው የዚህ ዓይነቱ ዓመጽ ይቆም ዘንድ ጌታን እማጠናለሁ።

እ.ኤ.አ. መስከረም 25 ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የሚውለው የመስማት ሕዋስ ስንኩላን ቀን መሆኑም በማስመልከት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙት በበሽታው ለተጠቁትን ሁሉ ሰላምታቸውን በማቅረብ በዚያች አለ ምንም ልዩነት ሁሉ በእኩል በሚስተናገድባት በሚገለገልባት ቤተ ክርስቲያን የሚሰጡት አገልግሎት እንዲበራታና የሚሰጡት አስተዋጽኦ አስፈላጊ ነውና በዚሁ ጉዳይ አደራ እንዲበራቱ ማሳሰባቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፥ በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ሁሉንም በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ማኅብራትና እንቅስቃሴዎች የታቀፉት እዛው ለጸሎተ መልአከ እግዚኣብሔር  የተገኙትን እንዲሁም በምሕረት ዓመት ምክንያት የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎ ኢዮቤልዩ ቀን ለተሳተፉት ሁሉ ሰላምታ አቅርበው በቤተ ክርስቲያን የአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ተሳታፊያን በመሆን ለምትሰጡት እምነትን የማስተላለፍ አስተዋጽኦ ምክንያት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ቅድስተ ማርያም ትደግፋችሁ በእምነት ጉዞአችሁ በማጽናት በትምህርተ ክርስቶስ አማካኝነት የምታስተላልፉት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሕይወት ትመሰክሩት ዘንድ ትደግፋችሁ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.