2016-09-23 16:27:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃል ለኢጣሊያ ጋዜጠኞች ማኅበር


ጋዜጠኝነትና የመገናኛ ብዙኃን ባለ ሙያነት የሰው ልጅ ክብር በመጠበቅና የክዋኔዎች እውነተኛነትን በማፍቅር የሰው ልጅ ማኅበራዊ ልኬት የሚያንጽና የሚያሳድግ ነው የተሰኘውና ሌሎች አንኳር ነጥቦች አዘል መልእክት እ.ኤ.አ. መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኢጣሊያ ብሔራዊ የጋዜጠኞ ማኅበር ምክር ቤት አባላትን አገረ ቫቲካን በሚገኘው በቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ጥቁርና ነጭ ሁለት በትክክል የሚለዩ ቀለሞች ናቸው ሆኖም ይኸን ዓይነቱ ልዩነት አንድ ጋዜጠኛ ካጠናቀረው ዘገባ ለመለየቱ ያዳግታል። የአንድ ዜና መዋዕል አቢዩ ርእስ ስፍር ቁጥር የለሽ የበስተጀርባ ሃሳቦች አዘል ነው። ይኽ ደግሞ ብዙውን ጊዜ ፖለቲካዊ ሙግትና ባልተናነሰ ደረጃም ለብዙ ግጭቶችና ውጥረቶች አልፎ አልፎ ጠንቅ ሊሆንም ይችላል። ስለዚህ ግልጽ በሆነና በማያሻማ እይታ የተሳሳተውና ባለ አመክንዮ ለመለየት አያዳግትም ያሉት ቅዱስ አባታችን ይኽ ደግሞ፥

ፍቅር ስለ እውነት እርሱም እውነትን ማፍቅር ያለው አስፈላጊነት ያስገነዝበናል።

ምንም’ኳ አንድ ዜና በሰበር ዜናነት ቀርቦ ሲያበቃ ባጭር ጊዜ ውስጥ ሰበርነቱን በመተው ያለፈ ዜና ቢሆንም። ስለዚህ የጊዜው ፈጣኝነቱ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ይኽ ሁነት ቆም ብሎ እየተሰራ ባለውና እንዴትም እየተስራ ነው በማለት ማስተንተን እግጅ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን የማይካድ ክብር መሆን አለበት ከዚህ አንጻር ሲታይ መዋዕለ ዜና የማጠናቀር ሙያ የጋዜጠኝነት ሙያ ያለው ውስጠ እሴቶች የሚክድ መሆን የለበትም።

እውነትን ማፍቀር መሰረታዊ ነገር ነው። ዜና የማጠናቀሩ ሙያ እውነትን ማፍቀር ከሚለው ልኡል ክብር መንደርደር አለበት። አንድ ዜና በተስማሚነት ማረጋገጥ ለብቻው አይበቃም። እውነትን መኖርና በግብረ ተልእኮ ወይንም በሙያው ዘርፍ እውነትን መኖር ያስፈልጋል። እንዲህ ሲባል ጥያቄው አማኝ ወይንም ኢኣማኝ መሆን ማለት አይደለም። ጥያቄው ለገዛ እራስና ከሌሎች ጋር ቅን መሆን የሚለው ይሆናል። ተገናኝነት አገናኝንት የመገናኛ ብዙኃን ማእከል ነው። ስለዚህ በቅንነት ላይ ያልጸና ግኑኝነት የማይዘልቅ እድሜውም አጭር ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታውቋል።

ጋዜጠኝነትንና ማኅበራዊ ልኬት

በሁለተኛ ደረጃ ይላሉ ቅዱስ አባታችን፤ እያንዳንዱ ሞያ በሞያተኝነት ብቃት ሊኖር ይገባዋል። ይኽ ሲባል የአንድ የሙያ ዘርፍ ሥርዓትና ሕግ (ሙያዊ ስርዓተ ደንብ) ማክበር በሚል አጥር ውስጥ ይዘጋ ማለት አይደለም ሙያዊ ደንብ የማክበሩ ግዴታዊ ኃላፊነት እንዳለ ሆኖ አንድ ሙያተኛ ሙያዉን ውስጠ ትርጉሙን መወሰጥ ያለው አስፈላጊነት ለመጠቆም ነው። ይኽ እርግጠኝነት አንዱ ሙያዉን ለየግል አመክንዮ ለአንድ ለተወሰነ አካል ኤኮኖሚያዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲያጎበድድ ወይም ማስገዛት እንደማያስፈልግ ያመለክታል። የጋዜጠኝነት ሞያ ጥሪ ነው፡ እውነትን ለመሻት ትኵረት የሚደረግበት እውነትን ለመንከባከብ የሚገፋፋ የሰው ልጅ ማኅበራዊነቱን ልኬት የሚያሳድግ እውነተኛ ዜጋዊነትን የሚያንጽ ነው።

የሰዎችን ሰብአዊ ክብር ማክበር

ቅዱስ አባታችን በዚህ የጋዜጠኞችና የጋዜጠኝነት ሙያ ህሊና ለሚያነቃቃ ባቀረቡት ምዕዳን ይላሉ ሙያው ከአሉባልታ በመራቅና አሉባተኝነትን በማግለል ዘወትር የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር እንዲጠበቅ ለማድረግ ያለመ ሕንጸት የሚሰጥበት ሙያ ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው፤

አንድ ዜና ዛሬ ይነገራል ለኅትመት ይበቃል ነገ አይኖም፡ ነገ በሌላ ዜና ይተካል ነገር ግን አለ ምንም ተጨባጭ እውነት አንዴ ስሙ እንዲስተነወር የተደረገውና ስም በማጥፋት የሚጠቃው ሰው ስለ ሆነ መረሳት የለበትም። ሰው ሕይወት እንጂ ዜና አይደለም። ገንቢ ህየሳ ተገቢ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊም ነው። ሆኖም ይኽ ተግባር ሌላውንና ሕይወትን በማክበር ጥበባዊ ሆኖ መከወን ይኖርበታል። ጋዜጠኝነት የጅምላዊ ዕልቂት መከሰቻ፡ ፍርሃትና ውዥንብር የሚያስፋፋ መሳሪያ አይደለም። ይኽ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት እንደሚታየው የስደተኞች ጸኣት ዙሪያ የሚሰጡት ዜናዎች ከጦርነና ከእርሃብ የሚያመልጠው ስደተኛው ዙሪያ የሚቀርቡት ዜናዎች የሚፈጥሩት ውዥንብርና ፍርሃት እንደ አብነት ለመጥቀስ ይቻላል ብለው፥

ጋዜጠኝነት ለጋራ ጥቅም ምክንት ነው

ጋዜጦችና የመገናኛ ብዙኃን ስለ እነዛ ከባድ በሽታ በሥራ እጦት በመሳሰሉት መጻኢን ለመገንባት ለሚደረገው ሰብአዊ ጉዞ የሚያሰናክሉ ሁነቶች እያጋጠማቸው ነገር ግን ሕይወትና እለታዊ ኑሮ በመግጠም ክብራቸውንና ሰብአዊነታቸውን ጠብቀው የሚኖሩ ብርቱ ወንዶችና ሴቶች ማእከል በማድረግ ዜና የሚያስተላልፉ ቢሆን እንዴት ደስ ባለ ነበር። ጋዜጠኝነትና ሙያው የመገናኘት ባህል የሚገነባ ከሌላው ጋር ለመገናኘት የሚያበቃ በር ነው፥ በመጨረሻ ጋዜጠኝነት የሕንጸት መሳሪያ ለጋራ ጥቅም ክክንት እርቅ የሚያፋጥን መሳሪያ ግጭትና ጥላቻን የመጠቆሱን ፈተና ለማግለል የሚስችል የመከፋፈል እሳትን የሚያርገበግብ ቃል ከመጠቀም ይልቅ የግኑኝነት ባህል የሚደግፍ ይሁን በማለት ያስደመጡት ምዕዳን ማጠቃለላቸው ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.