2016-09-23 16:33:00

የሐዘን መግለጫ መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ መክሲኮ ቨራክሩዝ አገር ግዛት ምስራቃዊ ክልል በምትገኘው በፖዛ ሪካ ከተማ ክልል ታግተው የነበሩት ኣባ አለኾ ናቦሪና አባ ኾሴ አልፍረዶ ኺመነዝ መገደላቸው እንደ ተሰማ እ.ኤ.አ. መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት የሐዘን መግለቻ መልእክት ለመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የተለግራም መልእክት ማንኛው ዓይነት ሕይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ የሕይወት ክቡርነት የሚጥስ ተግባር አውግዘው ካህናት ደናግል መናንያን ምንም’ኳ በሕይወት ሕይወትን ለአደጋ የሚያጋልጡ ዘርፈ ብዙ መሰናክሎች ስደት መገፋት ቢያጋጥማቸውም አደራ የመልካሙ እረኛ የሆነው የጠራንን የጌታ አብነት በመከተልና በመኖር በጥሪያቸው አንዲጸኑ አደራ ብልው ለመክሲኮ ውሉደ ክህንትና ጳጳሳት ለተገደሉት ካህናት ቤተሰቦች መጽናናትን ከጌታ ለተገደሉት ካህናትም ጌታ በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው መማጠናቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም አሁንም በመክሲኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም. አሞረሊያ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል አልበርቶ ሷረዝ ኢንዳ በአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ድረ ገጽ በኩል አባ ኾሴ አልፍረዶ ሎፐዝ ጉይለን የተባሉት በሚቾአካን ግዛት በሚገኘው አብፑሯንዲሮ ክፍለ ከተማ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቆመስ ባልታወቁ ሰዎች መታገታቸው ገልጠዋል ሲል ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።

የዚህ ዓይነቱ ጸረ ካህናት ድርጊት በመክሲኮ በተደጋጋሚ የሚታይ በመሆኑ እጅግ የሚያሳዝንና የታገቱት ካህን ሕይወታቸው ተርፎ ወደ አገልግሎታቸው እንዲመለሱ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የውሉደ ክህነት በጠቅላላ የምእመናን ሁሉ ጸሎት እደራ ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ሷረዝ ኢንዳ እክለው በዚህ አጋጣሚም የተገደሉትን አባ አለኾ ናቦሪና አባ ኾሴ አልፍረዶ ኺመነዝን አስታውሰው ሁሉም በተለያዩ የዓለማችን ክልል የታገቱት ካህናትና ምእመናን የታገተው ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።
All the contents on this site are copyrighted ©.