2016-09-22 14:29:00

ቅዱንስታቸው ዓለም ያጣችሁን ሰላም መልሳ ትጎናጸፍ ዘንድ ሁሉም ኋላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ።


ቅዱስ አባትችን ፍራንቸስኮ በትላንትነው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 20/2016 በአሲዚ ተካሄዶ በነበረው ዓለማቀፋዊው ፀሎት ስለሰላም የሚደረግበት ቀን ማጠቃለያ ላይ ለዓለም የሰላም ጥሪ ማሰማታቸው የታወቀ ሲሆን “በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ብንመልስ ለእርሱ ምንም የሚሳነው ነገር ስለሌለ ሁላችንም የሰላም ተዋንያን ልያደርገን ይችላል” ማለታቸው ተገለጸ። 

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ለዓለም ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ ሙሉ ቃሉን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል . . .

ከቅዱስ ፍራንቼስኮ አደባባይ፣ አስዚ

እለተ ማክሰኞ መስከረም 20/2016

ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተውጣጣችሁ እና ለመንፈሳዊ ንግደት በቅዱስ ፍራንቸስኮ ከተማ የተገኛችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ።

እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር የዛሬ 30 ዓመት በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ የተለያዩ የሐይማኖት ተቁዋማት ተወካዮችን እዚህ ጋብዞዋቸው ነበር። ይህም ብዙኋኑን በአንድነት ያሰባሰበ እና በመካከላቸውም የማይፋታ የሰላምን መልካምነት እና እውነተኛ የሐይማኖታዊ ባሕሪ ቃል ኪዳን መኖሩን ያሳየው የመጀምሪያ የተቀደሰ ስብሰባ ነበር።

ከእዚያ ታሪካዊ አጋጣሚ ቡኋላ የተለያዩ ረጃጅም መንፈሳዊ ነግደቶች ተጀምረው የተለያዩ የዓለም ከተሞችን በማዳረስ ብዙኋኑን አማኞች እንዲወያዩ እና ስለሰላም ፀሎት እንዲያደርጉ አጋጣሚን ከፈተ። በመካከላቸው ያለውን ልዩነት ሳይካድ ብዙኋኑን አሰባስቦ በሐይማኖት ተቋማት መካከል የወዳጅነት ግንኙነት እንዲጀመር ሕይወት በመዝራት እና ለጥቂት ተጨማሪ ግጭቶች ብዙ መፍቴሔሆችን በማስገኘት ከፍተኛ  አስተዋጾ አድርገዋል።

በመወያየት ግንኙነት ለማምጣት፣ ማንኛውንም ዓይነት ግጭት መቃወም፣ ሃይማኖትን ሰበብ በማድረግ እና ሃይማኖትን አላግባብ በመጠቀም ጦርነት እና ሽብርተኝነትን የሚያከናውኑትን መቃወም እኛን የሚያንቀሳቅሰን መንፈስ ነው። ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት ለቁጥር የምያዳጉቱ ብዙ ሰዎች አሳስዛኝ በሆነ መልኩ በጦርነት ተጎሳቁለዋል። ጦርነት የማይድን የሐዘን እና የጥላቻን ጠባሳ በመጣል ዓለማችንን እንደሚጎዳ ሰዎች ብዙን ጊዜ አይረዱም። በጦርነት ውስጥ አሸንፍያለሁ የሚለውን ጨምሮ  ማንም አሸናፊ ሆኖ የሚወጣ የለም።

ለዓለማችን ሰላምን ይሰጥልን ዘንድ ወደ እግዚኣብሔር ጸልየናል። ቀጣይነት ያለው ለሰላም የሚደረግ ጸሎት አስፈላጊ እንደሆነ እንረዳልን ምክንያቱም ጸሎት ዓለማችንን ስለሚጠብቅ እና ግልጸትን ስለሚሰጣት ነው። የእግዚኣብሔር ሥም ሰላም ነው። የእግዚኣብሔርን ስም ተጠቅሞ የሽብር ተግባራትን፣ ብጥብጥን ጦርነትን ማካሄድ የእግዚኣብሔርን መንገድ እንደ መከተል ሊቆጠር አይገባውም። በሐይማኖት ሥም የሚደረጉ ጦርነቶች ሁሉ ሐይማኖትን የሚቃወሙ ጦርነቶች ናቸው። እንግዲህ ቁርጥ ባለ አገላለጽ ጥቃት እና አሸባሪነት ተአማኒነት የሌላቸው እና ሃይማኖታዊ መንፈስ የሚቃወሙ ናቸው ብለን መግለጽ ይጠበቅብናል።

በጦርነት ምክንያት እየተሰቃዩ የሚገኙትን የድሆችን፣ የሕፃናትን፣ የወጣቱን ትውልድን፣ የብዙ ሴቶችን፣ የወንድሞች እና የእህቶችን ድምጽ እየሰማን እንገኛለን። ከእነርሱ ጋር በአንድነት እና በጽናት ጦርነት ይብቃ! እንበል። የብዙኋኑ ንጹኋን የጨነቀው ጩኸት ስይሰማ እንዳይቀር። ኃይልና ገንዘብን ለማግኘት የሚደረጉትን ምኞቶች፣ የጦር መሣሪያን ለመቸብቸብ የሚደረገውን ጥረት፣ የግል ፍላጎቶችን ለሟሟላት እና ያለፈን በደል ለመበቀል የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ የጦርነት መንስኤዎች በመሆናቸው የዓለማችን መሪዎች እነዚህን ነገሮች እንድያረግቡ እንማጸናለን። ድህነትን፣ የፍትህ መጓደልንና ያልተመጣጠነ እድገትን እንዲሁም የሰው ልጅ ሕይወት ብዝበዛ እና ንቀትን  በተጨማሪም ከላይ የተጠቀሱትን የጦርነት መንሰኤዎች ጨርሶ ለማጥፋት ቁርጠኛነትን ማሳየት ይገባናል።

ዓለማቀፋዊ ትስስር በተጀመረበት በአሁኑ ወቅት ዓለም አንድ ቤተሰብ ሊሆን ይገባል። እውነተኛ ሰላም ይሰፍን ዘንድ፣ ጥላቻን የሚያስወግድ ትብብርን በመፍጠር አለመግባባቶችን ሁሉ ተገናኝተን በመወያየት ግለሰቦች እና ማሕበረሰቡ ጦርነትን የማስወገድ ብቃት ይኖራቸው ዘንድ ኋላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል። ውጤታማ በሆነ መንገድ ወደ ውይይት በምንገባበት ወቅት ይምናጣው ምንም ነገር የለም። በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በምንቀርብበት ወቅት ሁሉ የሚሳነን ነገር አይኖርም። ሁላችንም የሰላም ተዋናይ መሆን እንችላለን። እዚህ በአሲዚ በተሰበሰብንበት ወቅት በእግዚኣብሔር ድጋፍ እና በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ሁሉ ጋር በመሆን የሰላም ተዋንያን ለመሆን የተረከብነውን ኋላፊነት አንዘንጋ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.