2016-09-22 11:18:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በአሲዚ ለሰላም ተደርጎ በነበረው የጸሎት ቀን ያስተላለፉት መልዕክት


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 20/2016 ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮን ጨምሮ የተለያዩ የሐይማኖት ተቋም መሪዎች በተገኙበት በአሲዚ ስለሰላም ፀሎት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በእለቱ የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች እንደእየ ሐይማኖታቸው ወግ እና ሥርዓት በየግላቸው ፀሎት ማድረጋቸው ታውቁዋል።

‘የሰላም ጥማት፣  የሐይማኖት እና የባሕል ውይይት’ የሚለው ሀረግ በእለቱ የተከበረው የሰላሳኛው ዓለማቀፍ ስለሰላም ጸሎት የሚደርግበት ቀን መርዕ ሐሳብ እንዲሆን ተመርጦ የነበረ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህም እለት ከዛሬ ሰላሳ ዓመት በፊት በቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ አነሳሽነት እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1986 መጀመሩም ይታወቃል።

በእለቱም ከተደረገው የጸሎት ፕሮግራም ቡኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ የማጠቃለያ ነግግር ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን ያስተላለፉት መልዕክት እንደ ሚከተለው ነው።

“ወደ አሲዚ የመጣነው መንፈስዊ ነጋዲያን በመሆነ ሰላምን ለመፈለግ ነው። በሐዘን ውስጥ ለሚገኙ በጣም ብዙ ሰዎችን በማሰብ በውስጣችን እናለቅሳለን እንዲሁም ተስፋችንን በእግዚአብሔር ላይ እናኖራለን፣ ሰላምን ተጠምተናል፣ ስለሰላም መመስከርም እንፈልጋለን። ከሁሉም በላይ ስለ ሰላም ልንጸልይ ያስፈልጋል ምክንያቱም ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ እና ሰላምን እንድንቀናጅ እንዲሁም አልፎም ተርፎ በእየቀኑ በእግዚአብሔር ድጋፍ ሰላምን እንድንገነባ ስለሰላም ልንማልድ ይገባል። እኛ ክርስቲያኖች የተጠራነው እንደ ወደድነው እንድናሰላስል ሳይሆን ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊት ‘የእግዚአብሔር ኋይል እና ጥበብን’ (1ቆሮ. 1:24) የፍቅርን ምስጢራዊነት እንድናሰላስል እና ምሕረትን በዓለም ለማሰራጨት ነው። የሕይወት ዛፍ በሆነው መስቀል ላይ ክፋት ወደ መልካምነት ተቀይሮኋል እኛም በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የነበርው ሐዋሪያ እንደ መሆናችን መጠን በግድዬለሽነት የተበከለውን ዓለማችንን እንዲመጥ እና ለዓለም ንፁህ የፍቅር አየር የሚያስገኘውን ‘የሕይወት ዛፍ’ እንድንሆን ተጠርተናል። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈሥ (ዩሐ. 19:34) ተምሳሌት የሆነው ውሃ ከጎኑ እንደወጣ ሁሉ  በእርሱ ከምንታመን ከእኛ ሁላችን ዛሬ ላዘኑት ሁሉ ርኅራኄ ከውስጣችን ሊወጣ ይገባል። የዛሬ 30 ዓመት በፊት የነበረው የአሲዚ መንፈስ በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ የነበሩ ዩሐንስ ጳውሎስ በወቅቱ እንደ ገለጹት ‘ሰላም ለተወሰኑ ጠበብት፣ አዋቂዎች እና ስልት አውጭዎች ቢቻ ክፍት የሆነ ቤተ ሙከራ ሳይሆን ለሁሉም ክፍት የሆነ ነገር ነው። ሰላም ሁለንተናዊ ኃላፊነት ነው’ ማለታቸው ይታወሳል። እኛ ይህን ኃላፊነት በመውሰድ ለብሮነት እንዲሁም የሰው ልጅ የተጠማውን ሰላም እግዚኣብሔር በሚፈልገው መንገድ ለምገንባት እሽታችንን በድጋሜ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.