2016-09-20 10:51:00

ቅ.ር.ሊ. ፍራንቸስኮ የቫቲካን የፖሊስ ኋይል ላለፉት 200 ዓመታት ያህል ላበረከቱት አገልግሎት ምስጋናን አቀረቡ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 18/2016 የቫቲካን ከተማ የፖሊስ ኋይሎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እያበረከቱ ለሚገኘው አገልግሎታቸው ምስጋናን ችረው አጋጣሚውንም ተጠቅመው ከብዝበዛ እና ከሙስና ጋር ከተያያዙ ወንጀሎች ይታቀቡ ዘንድ ማሳሰባቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታችው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ያሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ የቫቲካን ከተማ የፖልስ ኋይል አገልግሎቱን በይፋ የጀመረበትን 200ኛ ዓመትን የዘከረ ሲሆን በእለቱ ያሰሙት ስብከታቸው በዋነኛነት መሠረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በተነበበው እና በትንቢተ አሞጽ 8,4-7 የተጠቀሰው በዝባዦች፣ ሌባ እና ታማኝ የሆኑ 3 የተለያዩ ዓይነት ሰዎች መኖራቸውን በሚያወሳው ምንባብ ላይ መሠረቱ አድርጎ የነበረ መሆኑም ታውቁኋል።

“ሌባ ሰው ተንኮልን ይወዳል ታማኝነትን ግን ይጠላል፣ ክፉ ሰው ደግሞ በስውር የሚፈጸሙትን ስምምነቶች እና ጉቦን ይወዳ፣ ይህንንም እያደርገ እራሱን እንደ መልካማ ሰው መቁጠሩ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ ክፉ  ያደርገዋል” በማለት ስብከታቸውን የቅጠሉት ቅዱስነታቸው ሌባ ሰው በስተመጨረሻ የሚከሰቱበትን ነገር ሳያስብ “በድሆች ላይ ይረማመዳል” ብለዋል ።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት “የሠራተኞቻቸውን ጉልበት የሚበዘብዙ በጣም ብዙ ታላላቅ የሆኑ ኢንዱስትሪዎች” በዛሬው ዓለማችን እንድሚገኙ አስታውሰው “ዛሬ በምንገኝበት ዓለማችን የጉልበት ብዝበዛ ልክ እንደ አንድ የአስተዳደር መመርያ” እየተቆጠረ የመጣ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው አስተንትኖ እንደ ገለጹት እና ታማኝ የሆነው ሰው የተመሰለበትን ምሳሌ ባብራሩበት ወቅት ይህ ታማኝ ሰው ትክክለኛ የኢየሱስ ተከታይ መሆኑን ገልጸው “የዚህ ዓይነቱ ሰው በድርብ ስሜት ለሌሎች የሚጸልይ እና ሌሎችም ለእርሱ እንደ ሚጸልዩ የሚያምን የጸሎት ሰው” መሆኑን ከገለጹ ቡኋላ የስርዓተ-ቅዳሴውን ታዳሚዎች የእነርሱ ዋነኛ ተግባር ወይም ኋላፊነት ሊሆን የሚገባው አጭበርባሪዎችን፣ ሌቦችን እና በዝባዦችን መዋጋት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

የቫቲካን ፖሊስ ዋንኛው ተግባር መሆን የሚገባው ለሐቀኝነት ጥብቅናን መቆም መሆኑን በአጽኖት የገለጹት ቅዱስንታቸው “ለሁለት ምዕተ-ዓመታት ያህል ላበረከታችሁት አገልግሎት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፣ ከትንሽ አንስቶ እስከ ትልቅ ያሉት የቫቲካን ከተማ ማሕበረሰብ እና የቅድስት መንበር አገልግሎታችሁን ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” ብለዋል።

የቫቲካን ፖሊስ ለቫቲካን ከተማ እና ከቫቲካን ውጭ በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙትን የቫቲካን ንብረቶችን የመጠበቅ ኋላፊነት የተሰጠው ሲሆን ይህም  ኋይል በእነዚህ አከባቢዎች ጸጥታን የማስከበር፣ ማሕበራዊ ስርዓቶችን የማስከበር፣ ወንጀሎችን ማስቆም እና መከላከል በአጠቃላይ ፍትህን የማስከበር ኋላፊነት የተጣለበት ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1816 በጊዜው በነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፒዮስ 7ኛ በቪዬና ተካሄዶ በነበረው ጉባሄ ላይ ጳጳሳዊ ግዛቶች እንዲኖሩ ከመውሰኑ ጋር ተያይዞ የተመሰረተ ተቋም መሆኑም ይታወቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.