2016-09-19 16:27:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን፥ ፍርሃት ባለበት ዓለም ያገናኝ ድልድይ መገንባት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 15 ቀን እስከ መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በዚህ እየተኖረ ባለው የምህረት ዓመት ምክንያት በመላ የዓለማችን አህጉራት የሚገኙትን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ለኢዮበልዩ ቀን አገረ ቫቲካን እንዲገኙ በማለት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት በተለያየ ምክንያት ለመገኘት ካልቻሉት ሁለት ሐዋርያዊ ልኡካን በስተቀረ 106 ልኡካን መሳተፋቸውና ሦስቱን ቀናት በዓውደ ጉባኤ ጸሎትና አስተንትኖ እንዲሁም በቅዱስ በር በማለፍ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥልጣናዊ መሪ ቃል በመቀበል ብሎም እ.ኤ.አ. መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው በቅድት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት በሐዋርዊ ልኡካኑ ታጅበው በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባስደመጡት ስብከት የሰጡት መርህ ቃል በመቀበል መጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ፡

በሮችን ክፍት አድርጉ ድልድልዮችን ገንቡ ግኑኝነትና አሃድነትን አነቃቁ ውጣ ውረድ ለሚያበዛው ነዝናዥ የዚህ ዓለም መሥተዳድራዊ ሂደት አመክንዮ ሁሉ ፍርሃትን ያለፈውን ጨለማ ህልው አድርጎ በመኖር መኖርን ጊዚያዊነት ላይ የሚያቆም በመሆኑ እምቢ በማለት ትሁትን በመሆን ጸላያንና፡ መጻኢ ክፍለ ብርሃን በመሆኑም የክርስቶስ ነው  የሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል ያደረገ ሥልጣናዊ ምዕዳን  በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ቀለመንጦስ የጉባኤ አድራሽ ሐዋርያዊ ልኡካኑን ተቀብለው መለገሳቸው ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ገለጡ።

ትሁታን ልኡካን ሆኖ ማገልገል

ሐዋርያዊ ልኡካን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በምትገኝበት አገሮች ሁሉ አረኞች በመሆን ሕዝበ እግዚኣብሔን መሸኘት እንደ ትሁታን ልኡካን በውፉይነት መንፈስ ለማገልገል የተጠሩ ናቸው በሚል ቃል የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል መሆን ምን ማለት መሆኑ በጽማሬ ገልጠዉታል። የር.ሊ.ጳ. የፍቅር ሥራ ተልእኮው በሚያገለግሉበት አገርና በተለያዩ አገሮች ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን  የምታቀርቡና ካንተ የተለየ አስተሳሰብና አመለካከት ባለው ሰው ላይ ለመፍረድ ጣት ከመቀሰርና የበላይነት ለሚያሳይ ለአራሚነት ተግባር ከመሮጥ ይልቅ ለመደገፍ የፈጠኑ በቅርበት  በዝግጁነትና በወንድማማችነት መንፈስ ለእርቅና ለምኅህረት የፈጠኑ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ለሚስደደዱትና ለተገፉት ማኅበረ ክርስቲያን በማሰብ

ተኩላ የሚነዛው ያደፈጠው ስጋት ሁሌ ይኖራል፡ እውነትን ለማግለል የጥላቻ ባህል ስደትና መከራ ለማስፋፋት ዘወትር የነቃ ነው። በመካከለኛ ምስራቅ ያለው ማኅበረ ክርስቲያን አገራቸውንና ክልላቸውን ለቀው እንዲሰደዱ የሚጣልባቸው አስገዳጁ ጥቃትና አመጽ ብዙዎች በምን አገባኝነትና ችላ ባይነት ተግባር በመመልከት በተዘዋዋሪ ተባባሪ እየሆኑበት ያለውን ጸረ ሰብአዊ ተግባር ዘክረው ይኸንን የስጋት ሁነት የሚኖር ማኅበረ ክርስትያንን በማሰብ የዚያንች በደስታ የምታገለግሉዋት ቤተ ክርስቲያንና የኢየሱስ የተራራው ስብከት ያለው የእምቁ ኃይል መንፈስ በሁሉም ይደመጥ ዘንድ ለማድረግ ትጉ ከማጉረምረምና በሚሰነዘር ችትች ምክንያት እራስ ተገፊ በማድረግ ከማንባትና ከመወላወል መንፈስ መራቅ ያስፈልጋል።

አላፊ ለሆነው ለዚህ ዓለም ሥልጣን ከማጎብደድ መቆጠብ፥ ርእዮተ ዓለምና ፖለቲካን ማእተብ አለማድረግ

ሐዋርያዊ ልኡካን በዚያ የእውነት ድምጽ እንዳይሰማና እውነትን ዝም ለማሰኘት ከሚሻው ከማንኛውም የሥልጣን ስልፍ ፊት የቤተ ክርስቲያን ነጻነት ዋስ በመሆን ለመስዋዕት ዝግጁ እንዲሆኑ ቅዱስ አባታችን በማሳሰብ ነጽነት በስምምነቶችና በዲፕሎማሲያዊ የውይይት መድረክ ብቻ የሚረጋገጥ ነው ብሎ እራስን ማታለል የዋህነት ነው። ቤተ ክርስቲያን ነጻ የምትሆነው የውስጧ ተቋማትና ቅርጾች ብዙዉን ጊዜ በመጋብያንም በምእመናንም ላይ ሳይቀር የሚዛመተው ዝውትር የሆኑት ልምዶችና ስልቶች አለ ምንም ፍርሃት ለሁሉም ወንጌልን ማበሰር እንደ ክርስቶስ የተቃርኖ ምልክት ሆኖ መገኘት እንጂ አድር ባይነትን ለመኖር አልተጠሩም።  

የዚያ ከማንኛውም ዓይነት ርእዮተ ዓለም ዘመምነት  ነጻ የሆነው ቃለ እግዚኣብሔርን ለእራስ ጥቅም በማዋል ተግባር ለማንቋሸሽ ለሚራወጠው ላላፊው የዓለም ሥልጣናት አጎብዳጅነትን ያልበገረው ዓለት ለሆነው የቅዱስ ጴጥሮስ ልኡካን መሆናችሁ አስታውሱ። የቤተ ክርስቲያን ህልውና በእንግዳ መቀበያና ባደባባይ በሚከወኑት ስምምነቶች ላይ የጸና ሳይሆን ከተኵላ ከበራሪያን እንስሳት ለየት የሚያደርገው ማረፊያና ጎጆ ለሌለው ለጌታ ታማኝ በመሆን ላይ የጸና ነው።

የውጣ ውረድ የዓለም እሰራር አመክንዮ ማሸነፍ፡ ብፁዓን ጳጳሳት መጋብያን እንጂ መሳፍንት አይደሉም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ደጋግመው ልኡካን የውጣ ውረድ ከሚያበዛ ማለትም ከቢሮክራሲያዊ አመክንዮ ተቆጥበው ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን የዚያች ወደ የከቶሞችና የህልውና ጥጋ ጥግ ለምትወጣው በጦርነት አውድማ ውስጥ እንዳለው የሕክምና መስጫ ድንኳን ለሆነቸው ቤተ ክርስትያን መግለጫዎች እንዲሆኑ በማሳሰብ፡ ስለዚህ የቅድስት መንበር የሐዋርያዊ ልኡክ ሕንፃ የወዳጆችና ጓደኞች መጠጊያ ሳይሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቤት ነው። የሁሉም ቤት እንጂ የወዳጅ ጓደኞች መገልገያ ቤት አይደለም ብለው፡ ልኡካን በሚገኙበት አገር በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለሚሾሙት ብፁዓን ጳጳሳት ብቃት ጠቋሚያን በመሆናቸው ከዚህ አንጻር ሲታይ ያለባቸው ኃላፊነት እጅግ ከባድ ነው፡ ስለዚህ መሳፍንት ሳይሆን የተነሳው ጌታ መስካሪ የሆኑት እረኛ ጳጳሳት በመምረጡ የቅድስቱ ጴጥሮስ ተከታይ ተግባር ያለባቸው የተሳታፊነት ኃላፊነት አደራ በጥንቃቄና በማስተዋል በጸሎት እንዲወጡት በማሳሰብ፡ በእግዚአብሔር ልብ ተመርተው የጌታ ልብ ደስ የሚሰኝበትን ለይቶ ለመጠቆም መውጣት እንጂ ወዳጆችና ጓደኞች በሚሰበሰቡበት መዋኛ ሳይሆን በዚያ ከሁሉም ጋር በመገናኘት የተገባውን ለማጥመድ የሚችሉ እንዲሆኑ በማስገንዘብ፥

ምሕረት የሐዋያዊ ልኡክ ተልእኮ ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ሲያጠቃልሉ የእግዚአብሔር የደግነት ኃይል የማይመለከተው አካል ሥልጣንና ስፍራ የለም ለሁሉም ነው።ለቆሰለው አካልና ዓለም የእግዚአብሔ ምሕረት ማወጅ። ጠፍቶ የሚቀር ከመዳን ውጭ የሆነ ማንም የለም። ቢያውቅም ባያውቅም ለእግዚአብሔር ቦታየይሌለው ማንም ሰብአዊ ፍጡር የለም። ስለዚህ ያንን የእውነት ውበትና ኃይል ከሚያምታታውና ዝቅ ከሚያደርገው ፍርሃት ነጻ ሆናችሁ ከሁሉም ጋር ተወያዩ ። እውነት በሙላት የሚገለጠውና የሚፈጸመው በምህረት ነው። በመሆኑም የታሪክና የሕይወት ኦሜጋ አመጽ ግጭት ሳይሆን ያ የሁሉም ሰብአዊ ፍጡር ልብ የሚጸናበት አሃድነት ነው እንዳሉ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ኦንዳርዛ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.