2016-09-19 16:36:00

ሐዋርያዊ ልኡካን ከዓለም ጋር የሚወያዩ ወደ ውጭ የሚወጡ ልኡካን ናቸው


በሁሉም የዓለም ማእዝን ወንጌል ለማበሰር ከገዛ እራስ መውጣት ወሳኝ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ ባለው ቤተ ጸሎት ለልዩ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን የምሕረት ዓመት ኢዮቢልዩ ቀን እ.ኤ.አ. ከመስከረም 15 ቀን እስከ መስከረም 17 ቅን 2016 ዓ.ም. ለማክበር አገረ ቫቲካን በገቡት የቅድስት መንበር ሐርዋያዊ ልኡካን ታጅበው ባሳረጉብት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከ አስገንዝበው፥ የዘሪው ምሳሌ ጠቅሰው ሐዋርያዊ ልኡክ መልካም ዜና የሚያበስር ነው። ይኽ ደግም ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር የሚቀየርና ወደ ተላከበት አገር የሚንቀሳቀስ በመሆኑም ሐዋርያዊ ልኡክ ዘላንና በቋሚነት የሚኖበት አገር የለውም። የቅዱስ ጴጥሮ ተከታይ ጥሪና ትእዛዝ በመጠባበቅ የሚኖር፡ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር የሚንቀሳቀስ ልኡክ ነው።

ሁሌ ወደ ተላክበት ለመሄድ ዝግጁ፡ በአንድ አገር ተልእኮ የዚያ አካባቢ ባህል ቋንቋ ሃይማኖታዊ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ሂደቱ ጋር ተዋውቆ መኖር ከገዛ እራስ ወጥቶ አዲስ ዜና የማበሰር ተልእኮ ያመመልክታል። ሌላው መውጣት ደግሞ ከተላክበት አገርና ከተዋወቅከውና በማገልገል ላይ ከምትገኝበት አገር ለመቀየር ዝግጁ ሆኖ መገኘት ማለት ነው፡ በዓለማዊነት መስህብ ካለ መማረክና የዓለም ሳይኮን ቃለ እግዚአብሔር ለመዝራት የሚወጣበት ተልእኮ ነው። በዓለም የሚኮነው ሰውን ለማጥመድ እንጂ በዓለም ለመጠመድ አይደለም። ሌላውን ለመረዳት ከሌላው ጋር ለመወያየት መውጣት። ዘሪው ለመዝራት ይወጣል ፍርያማ በማድረግ የሚለመልመውና የሚያሳድገውም እግዚአብሔር ነው። ከዚህ ፍርያማ የሚያደርገውና የሚያሳድገው ጌታ ጋር ለመገናኘት ከገዛ እራስ መውጣት፤ ይኽ ማለት ደግሞ ጸሎት በቅዱስ ቁርባን ፊት አስተንትኖ በመንበረ ታቦት ፊት ጉልበትን አጠፍ ማድረግ ማለት ነው፡ እንዳሉ የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ፡

በምትላክበት አገር ለመኖር ዝጅጉ መሆን። ሐዋርይዊ ልኡክ መሆን ሁሌ ሻንጣህ ዝግጁ አድርገህ መኖርን ይጠይቃል። ሌላው መውጣት ደግሞ ለመማር ዝግጁ መሆና በመጨረሻም ሶስተኛው መውጣ ጾሎትና አስተንትኖ በቅዱስ ቁርባን ፍት ፊት ለመኖር ከእራስ ውጥቶ ወደ ጌታ መውጣት ማለት መሆኑ አብራርተው፡ ልኡካኑ ለሚሰጡት አገልግሎት ቅዱስነታቸው ካመሰገኑ በኋላ በማያያዝም እዚያ በቅድሴው ከተሳተፉት ውጭ በተጨማሪ ሌሎች በቅድሴው ሥነ ስርዓት የተገኙት 40 በተለያዩ አገሮች የቅድስት መንበር ልኡካን በመሆን ያገለገሉት ልኂቅ ሐዋርያዊ ልኡካንን በማሰብ አሁኑም የጸሎት ልኡካን ናችሁ ብለው በመግለጥ። ስለ አገሮች ወንድሞች ሁሉ ወደ አብ ጸሎታቸውን የሚቀርቡ ናቸው። ከኃላፊነት ልኂቅ ወይንም ጡረተኛ ይኰናል ነገር ግን ከጸሎትና ካስተንትኖ ጡረተኛ አይኰንም። በማለት ሁሉንም ልኡካን በዚህ ከገዛ እራስ መጣት በሚጠይቀው አገልግሎታቸው የሚሰጡ ምስክርነት አመስግነው፡ እነዚያ ሦስት ዓይነት መውጣት ዕለት በዕለት ይኖሩ ዘንድ ጌታ እንዲደግፋቸውም ተማጽነው ያስደመጡት ስብከት እንዳጠለሉ ጂሶቲ አስታወቁ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን እ.ኤ.አ. ከመስከረም 15 ቀን እስከ  መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም. የኖሩት ኢዮቤዩ ቀን ያጠናቀቁት የቅድስት መንበር ልኡካን በዓለማችን ክልል የሚታዩት ግጭቶች እንዲገቱና በሰላማዊ መንገድ አመጽና ውጥረት ሁሉ መፍትሄ እንዲያገኝ የውይይት ባህል በማነቃቃትና የሚሰጡት አገልግሎት በማጠናከር እንደሚቀጥሉብትና ግጭት በሚታይባቸው ክልሎች ሰላም እንዲረጋገጥ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርግ የሚያሳስብ የጋራ መግለጫ ማስተላለፋቸው ጂሶቲ አስታወቁ።   








All the contents on this site are copyrighted ©.