2016-09-17 09:47:00

ቅዱስነታቸው የአንድ ክርስቲያን ስነ-አመክንዮ እለታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ያተኮረ ሳይሆን ከሞት ቡኋላ ሕይወት እንዳለ ማመን ነው


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 16/2016 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የአንድ ክርስቲያን ስነ-አመክንዮ (Logic) እለታዊ ነገሮችን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን በእምነት ከሞት ቡኋላ ትንሣኤ እንዳለ የሚያሳየውን የወደፊት ስነ-አመክንዮ መሆን ይገባዋል ማለታቸው ተገለጸ።

 “ክርስቶስ ከሞት ካልተነሳ እኛም ከሞት መነሳት አንችልም” በማለት በመጨረሻው ጊዜ መቤዠት የሚለውን  የስነ-አመክንዮ አስተሳሰባቸውን ለማጽናት በማሰብ በእለቱ ከ1ቆሮ 15, 12-20 በተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጸሎተ ሃይማኖትን በምንደግምበት ወቅት ‘ከሙታን መነሳት እንዳለ አምናለሁ’ የሚለውን የመጨረሻ ሀረግ የወደፊቱ ነገር ስለምያስፈራን በችኮላ ነው የምንደግመው በማለት ጸጸት በተሞላበት መልኩ ገልጸዋል።

“የወደፊቱ ስነ-አመክንዮ የክርስቶስን ከሙታን መነሳት የሚያሳይ ስነ-አመክንዮ ነው” በማለት ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ለእኛ ለሁላችን ባለፈው ጊዜ ስነ-አመክንዮ ውስጥ መግባት በጣም ቀላል ነው ምክንያቱ በተጨባጭ ሁኔታ ያሳለፍነው እውነታ በመሆኑ ነው እንደዚሁም በአሁኑ ጊዜ ስን-አመክንዮ ውስጥ መግባት ለእኛ ቀላል ነገር ነው ምክንያቱም የምናየው እውነታ በመሆኑ ነው ነገር መጭውን ነገር በምናስብበት ወቅት “ቀላል ነገር ባለመሆኑ እና ሙሉ በሙሉ በወደፊቱ ስነ-አምክንዮ ውስጥ መግባቱ ስለሚያስፈራን አለማሰቡን እንመርጣለን” በለዋል።

ቅዱስነታቸው ስበካታቸውን በቀጠሉበት ወቅት “ባለፈው ጊዜ ስነ-አመክንዮ ውስጥ መግባት ቀላል ነው፣ በዛሬው ቀን ስነ- አመክንዮ ውስጥ መግባትም ቀላል ነው፣ በነገው እለት ስነ-አመክንዮ ውስጥ መግባትም ቀላል ነው ምክንያቱም ሁላችንም መሞታችን ስለሚታወቅ፣ ነገር ግን ከእዚያን ቡኋላ ባለው ስነ-አመክንዮ ውስጥ መግባት ግን ቀላል ነገር አይደለም” በማለት በተመስጦ ሰብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ከሙታን መነሳት እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴትስ ይከሰታል? ክርስቶስ ከሙታን መነሳቱ ግልጽ ነገር ነው። አነሳሱም እንደ እንድ መንፈስ አይደለም ምክንያቱም በሉቃስ ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው እየሱስ ከሙታን ከተነሳ ቡኋላ ‘ንኩኝ፣ የሚበላ ነገርም ስጡኝ’ ብሎ ነበር አንድ ምንፈስ ሥጋ እና አጥንት ሊኖረው አይችልም የወደፊት ጊዜ ስነ-አመክንዮ ውስጥ መግባት ማለት በሥጋ መነሳት እንዳለ ማመን ነው ብለዋል።

ሐዋሪያው ዩሐንስ “የእግዚአብሔር ቃል ሥጋን ለብሶ መምጣቱን  የማያምን ሰው ሁሉ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው” ማለቱን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የክርስቶስ ሥጋ የመጨረሻ ሁኔታን ለማሰብ እና ለመቀበል ያስፈራናል፣ ይህም የሆነበት ምክንያት እራሳችንን በክርስቶስ ሥጋ ስነ-አመክንዮ ውስጥ መስገባት ስለሚከብድ ነው” ብለው “ክርስቶስ ከነሥጋው ከሙታን እንደተነሣ ሁሉ እኛም ከእነሥጋችን ከሙታን እንነሳለን” ብለው የእለቱን ስብከታቸውን አጠናቀዋል።  

 








All the contents on this site are copyrighted ©.