2016-09-16 16:10:00

የቅድስት መንበርና የተባበሩት የኤሚራት አረብ አገሮች ክሌአዊ ስምምነት ፍርርም


እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ሎ’ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ሕትመቱ በቅድስት መንበርና በተባበሩት የኤሚራት አረብ አገሮች መንግሥት መካከል በአገረ ቫቲካን በሚግኘው ሐዋርያዊ ሕንፃ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊንና ልኡልነታቸው የዱባይ ዘውደ ወራሽ የተባበሩት የኤሚራት አረብ አገሮች የመከላከያ ኃይል ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሸክ አቡ ሞሃመድ ቢን ዛየድ ቢን ሱልታን አል ናህያን እንዲሁም የቅድስት መንበር የውጭ ጉኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፖውል ሪቻርድ ጋላገርና አቻቸው የተባበሩት የኤሚራት አረብ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአገሪት ዓለም አቀፋዊ ትብብሮች ጉዳይ ኃላፊ ልኡልነታቸው ሸክ አብዱላህ ቢን ዛየድ አል ናህያን  የክሌአዊ ስምምነት ፍርርም መከናወኑ ዘግቦ ባስነበበው ዜና እንዳመለከተው፡ ስምምነቱ በሁለቱ አገሮች መካከል በሚደረገው የጉዞ ግኑኝነት አለ የመግቢያ ፈቃድ የሚከወን የነጻ መግቢያ ፈቃድ ለዲፕሎማቶችና የሁለቱ አገሮች በተለያየ መንግሥታዊ አገልግሎ ምክንያት የሚላኩት የሚመለከት ሆኖ ለኡካንና ልዩ ፓስፖርት ለሚኖራቸው የሁለቱ አገር ዜጎች ነጻ የመግቢያ ፈቃድ የሚል ሲሆን፡ ፍርርሙ ከተከናወነበት እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ስምምነቱ በግብር ላይ እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.