2016-09-15 11:10:00

ር.ሊ.ጳ ፍራነቸስኮ የቤተ ክርስቲያን እረኞች ከምዕመናን መራቅ አይገባቸውም አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 14/2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሳምንታዊው የጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙ መዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ባስተላለፉት አስተምህሮዋቸው የቤተ ክርስቲያን እረኞች ከምዕመናን መራቅ እንደ ማይጠበቅባቸው ገልጸው ነገር ግን በድሆች መካከክል በመመላለስ የእግዚአብሔርን የማዳን ፀጋ ለሕዝቡ ይሰጣቸው የነበረውን የክርስቶስን ምስሌ መከተል እንደ ሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

በትላንትናው እለት የተከበረውን የመስቀል በዓል ዋቢ በማድረግ አስተምህሮዋቸን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ለሁሉም በተለይም ደግሞ ለድሆች ቅርብ እንደ ነበረ ገልጸው “ኢየሱስ በሕዝቦች መካከለ የሚቆም እረኛ ነበር፣ ቀኑን በሙሉ ከእነርሱ ጋር ይሰራ ነበር፣ ኢየሱስ እንደ አንድ አለቃ ሰው አይነት አልነበረም” ብለው “ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት እረኞች ኋላፊ መስለው ስታዩ እና ከሕዝቡ መራቅ ሲጀመሩ በተለይም ከድሆች መራቅ ሲጀምሩ መመልከት በጣም አጸያፊ ነገር ነው፣ ይህም ተግባር የኢየሱስን መንፈስ የማያጸባርቅበት ነው፣ እንደ እነዚህ አይነት እረኞችን  ኢየሱስ ‘እነሩሱ የሚያደርጉትን ሳይሆን የሚልዋችሁን አድርጉ` በማለት መገሰጹን አስታውሰዋል።

በማቴዋስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተለይም በእዚህ በያዝነው ቅዱስ የምሕረት ዓመት “በካቴድራሎች፣ በጸሎት ሥፍራዎች፣ በማረሚያ ቤቶች እና በተለያዩ የዓለም ክፍል በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ ነጋዲያን የእግዚአብሔርን ምሕረት የሚገልጽ ተግባራትን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው በተለይም ደግሞ “ኢየሱስን ለማግኘት፣ የኢየሱስን ጉደኝነት ለመጎናጸፍና ኢየሱስ የሚሰጠውን ልዩ የሆነ እረፍትን” መሻት እንደሚጠበቅብን ገልጸው “ይህም ተግባር ኢየሱስ ወደ ሚፈልገው ዓይነት ሐዋሪያ መቀየራችንን ስለሚያሳይ፣ እንዲሁም ምህረት ሁል ጊዜ የሚገኘው ምሕረትን የሚገልጽ ተግባራትን በምናከናውንበት ወቅት በመሆኑ ይህንን የማያልቀውን እና ዘላለማዊ የሆነውን እንዲሁም ታላቅ የሆነውን የእግዚአብሔር ምሕረትን መሻት ያስፈልጋል” ብለዋል።

የኢየሱስን ቀንበር ተሸክመን እርሱን በምንከተልበት ወቅት እያንዳንዱ  ሰው ከእርሱ ጋር ኅብረትን ይፈጥራላ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ እርሱ እራሱ የማይሸከመውን ሸኽም ለሰዎች አሸክሞ ለብቻቸው የሚለቃቸው መምህር ሳይሆን የዋህ የሆኑትን፣ አቅመ ደካሞችን፣ ድሆችን፣ እገዛ የሚፈልጉትን ሰዎች ሁሉ ሸኽማቸውን በማገዝ ሰዎችን ለማዳን ባደርገው የደኅንነት ጉዞ ሁሉ ድህንነትን በመላበስ በትክሻው ላይ የሰው ልጆችን ሁሉ ሐዘን እና ኋጥያት ተሸክሞ እንደ ነበረ ገልጸዋል።

ከእዚህ መረዳት ያለብን ነገር አሉ ቅዱስነታቸው “ከእዚህ መረዳት ያለብን እና እራሳችንን መጠየቅ የሚገባን ጉዳይ በአደራ የተሰጠንን ኋላፊነት ለሌሎች መልካምነት እያዋልነው እንገኛለን ወይስ አይደልም? የሚለውን መጠየቅ እንደ ሚገባ ገልጸው “አንድ አንድ ጊዜ የእዚህ ዓይነት ድከመት የሚመጣው በአገልግሎታችን ውስጥ ዋና ዋና የሚበላትን ተግባራትን ዘንግተን እና በጣም አስፈላጊ ባልሆኑ ተጋባርት በምንወጠርበት ወቅት ከሕዝቡ እንርቃለን ይህ ደግሞ ተግቢ አይደለም፣ ኢየሱስ የሚያስተምረን “የምሕረት ተግባራት ውስጥ መኖር እና የምሕረት መሳሪያዎች መሆን እንደ ሚጠበቅብን ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.