2016-09-14 17:17:00

ቅዱስነታቸው የግዴለሽነትን ባሕል ማሸነፍ የሚስችለንን እውነታኛ ባሕል ለማምጣት መሥራት ይጠበቅብናል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 13/2016 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት የግደለሽነትን ባሕል ማሸነፍ የሚስችለንን እውነታኛ ባሕል ለማምጣት መሥራት ይጠበቅብናል ማለታቸው ተገለጸ።

የዛሬው የእግዚኣብሔር ቃል ግንኙነታችንን እንድናሰላስል ይጋብዘናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ብዙን ጊዜ ሰዎች ይተላለፋሉ ነገር ግን አይነጋገሩም” ብለው አንድ ሰው በኅዘን ለምንድነው ሰው “እያየ የማይመለክተው እየሰማ የማያድምጠው” ብለን እያንዳዳችን  እራሳችንን መጠየቅ ይገባናል ብለዋል።

“ልክ በዛሬው ወንጌል እንደ ተጠቀሰው መገናኘት የእራሱ የሆን ሌላ ትርጉም አለው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ አንዲያ ልጇን በሞት በማጣቱዋ ምክንያት በማልቀስ ላይ ከነበረች መበለት ጋር በተገኛኘበት ወቅት በጣም እንደ ራራላት ሁሉ የእዚህ ዓይነቱ ርኅራኄ ልያስረዳን የሚሞክረው “እኛ በመንገድ ላይ በምንጓዝበት ወቅት ለምሳሌውም አንድ የምያሳዝን ነገር ስናይ ‘ውይ ያሳዝናል` ብቻ ብለን እንደ ምናልፈው ዓይነት ግንኙነትን አይደልም፣ ኢየሱስ ያሳዝናል ብሎ ብቻ አላለፈም ራራላት፣ መበለቲቱን ቀረበ፣ አገኛትም ከእዚያም ቡኋላ ታምራትን እንደ ፈጸመ” ገልጸዋል።

ከእዚህ ሁኔታ የምንገነዘበው አሉ ቅዱስነታቸው ርኅራኄን ማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን “ፍሬያማ የሆነ ግንኙነት መደረጉ አስፈላጊ መሆኑን ጭምር ነው” ብለው “ማንኛውም ግንኙነት ፍሬያማ ሊሆን ይገባል፣ እያንዳንዱ ግንኙነት ሰዎችን እና ነገሮችን መልሰን እንድናገኝ ይረዳናል ብለዋል።

“እኛ እራሳችን ቸልተኝነትን የተላበሰ ባሕል ተላምደናል፣ ይህንን ለማስወገድ ጠንክረን መሥራት እና ፍሬያማ የሆነ ግንኙነት ማድረግ የሚያስችለንን የእግዚኣብሔርን ፀጋ መጠየቅ ይኖርብናል፣ ይህም ፀጋ ፍሬያማ ያደርገናል፣ ከእዚህም ፍሬያማ ግንኙነት የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚብሔር ልጆች መሆናቸውን የሚያጎናጽፍ መብት እንድንለግሳቸው ያግዘናል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው “እኛ በአለም ውስጥ የሚፈጸሙትን ትልቅ ይሁን ትንሽ መከራዎችን በምንመልከትበት ወቅት ሁሉ “ ውይ በጣም ያሳዝናል፣ እነዚህ ሰዎች እንዴት እየተሰቃዩ ነው፣ እነዚህ ሚስክን የሆኑ ሰዎች. . . ብለን ብቻ እንድናልፍ በሚያደርገን የቸልተኝነት ባሕል ውስጥ እየኖርን እንገኛለን” ብለው ማንኛውንም ግንኙነት በማየት ማለፍ ብቻ ዋጋ የለውም፣ ካልቆሙኩኝ፣ ካልነካሁኝ፣ ካላዋራሁኝ. . . በማየት ብቻ ትክክለኛ የሆነ ግንኙነት አድርግያለሁ ማለት አልችልም፣ መርዳትም አልችልም፣ ይህንን የመሰለ ተግባራትን በምንፈጽምበት ወቅት የግንኙነትን ባሕል ዘንግተናል ማለት ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት በኢየሱስ እና በመበለቲቱ መካከል ግንኙነት በተደርገ ወቅት በእዚያ የነበሩ ሰዎች “ታላቅ ፍርሃት ያዛቸው፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር ምክንያቱም ኢየሱስ እግዚኣብሔርን እና ሰውን በድርጊቱ አገናኝቶ ስለነበረ ነው” ብለው ለእኔ አሉ ቅዱስነታቸው አክለው “በኢየሱስ እና የእርሱን ዳግም መምጣት በምትጠባበቀው ሙሽራው በሆነችው ቤተ ክርስቲያን መካከከል በእየለቱ የሚደረገው ግንኙነት ያስደስተኛል” ብለዋል።

የዛሬ የወንጌል ቃል መልዕክት በድጋሚ የሚያሳስበን ኢየሱስ ከሕዝቦቹ ጋር መገኛኘቱን ነው፣ ሁላችንም ብንሆን የኢየሱስ ቃል ከእርሱ ጋር መገናኘት ያስፈልገናል በማለት ስብከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው “ስንት ጊዜ ነው ከቤተሰብ ጋር በገበታ በአንድነት ቁጭ ብለን የተመገብነው? ነግር ግን የምናዘወትረው ቴለቪዥን ማየት ወይም በእጅ ስልኮቻችን አማክይነት መልዕክቶችን መለዋወጥ ነው የምንመርጠው” ብለው ሁላችንም ለግኝኙነቶች ችልተኝነትን እያሳየን ነው፣ በምሕበረሰብ ውስጥ ይሁን በቤተሰብ ውስጥ ትክክለኛ የሆነ ግንኙነት እየተንጸባረቀ አይደለም ለዚህም ነው በቀላሉ ኢየሱስ ስያደርግ እንደ ሰማነው ይህንን ባሕል ለመለወጥ መሥራት ይኖርብናል የምለው ብለዋል ።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “ማየት ብቻ በቂ አይደለም መመልከት ያስፈልጋል ፣ መስማት ብቻ በቂ አይደለም ማዳመጥ ያስፈልጋል፣ መተላለፍ ብቻ በቂ አይደለም ቆም ብለን ማናገር ያስፈልጋል፣ ያሳዝናል ውውውይ ምሲክን ሰዎች ማለት ብቻ አይበቃም  መቅረብ፣ መንካት እንዲሁም ከልብ በመነጨ መልኩ በአንደበታችን ‘አታልቅሽ ወይም አታልቅስ’ በማለት ተጨባጭ በሆነ መልኩ ርኅራኄን ማሳየት ያስፈልጋ ብለው የእለቱ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.