2016-09-14 17:35:00

ቅዱስነታቸው አንገታቸውን ታርደው የተገደሉትን አባ ጃኩዊስ "ሰማዕት ናቸው” ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 14/2016 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት ስርዓተ ቅዳሴ ወቅት ያሰሙት ስብከት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በሐምሌ 26/2016 በፈረንሳይ ሀገር ቅድስት ኤቲያን ዱ ሩቭሬይ በሚባለው ቤተክርስቲያን ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴን በማሳረግ ላይ በነበሩበት ወቅት በአክራሪ አሸባሪዎች አንገታቸውን ታርደው የተገደሉትን አባ ጃኩዊስ ሀሜል ላይ ትኩረቱን አድርጎ የነበረ ሲሆን በእለቱ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ-ሉጥርጊያ ደንብ መሰረት የተከበረውን የመስቀል በዓልን ዋቢ አድርገው “እኝህ ካህን ሰማዕት ናቸው፣ ሰማዕታት ደግሞ ብጹዕን ናቸው” ማለታቸው ተገለጸ።

በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይም በሁለት ወጣት አሸባሪዎች አንገታቸውን ታርደው ሕይወታቸውን ያጡትን አባ ጃኩዊስ ሀሜል ለመዘከር እርሳቸው በሕይወት በነበሩበት ወቅት ያገለግሉበት የነበረው ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ ዶሜንክ ሌብሩን እና ተጨማሪ 80 ያህል ከሀገረ ስብከቱ የተውጣጡ ነጋዲያን መገኘታቸውም ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው “ሁሉም የሐያማኖት ተቁዋማት በአንድነት ‘በእግዚአብሔር ሥም መግደል’ ሰይጣናዊ ተግባር መሆኑን  ብያወግዙ እንደ ሚደሰቱ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ልብን በሚነካ ሁኔታ “የአባ ጃኩዊስ ሀሜል ሕይወት እና ሞት በክርስቲያን ስማዕታት የሕይወት ታሪክ ውስጥ ተጽፎ እንደ ሚቀመጥ ገልጸው ይህንንም ታላቅ ተግባራቸውን ዛሬ ከፍ ተደርጎ በሚከበረው የመስቀል በዓል ምልከታ ማየት እንደ ሚገባም ጨምረው ገልጸዋል።

ኢየሱስ “በባሕሪው አምላክ ቢሆንም” የባሪያን መልክ ይዞ ሰው ሆነ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እስከ መሞት ድረስም ታዛዥ ሆነ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ የመጀመሪያው ሰማዕት ነው” ከእዚህም ታላቅ የክርስቶስ ምስጢር ውስጥ ከመጀመሪያ ምዕተ አመት እስከ ዛሬ ድረስ የክርስቲያኖች የሰማዕትነት ሕይወት ጅማሬውን አገኜ” ብለዋል።

“የክርስቶስን ሰማዕትነትን በመንበረ ታቦት ላይ እየገለጹ በነበሩበት ወቅት መሰዋታቸውን በጥልቀት ሳስብ በእዚህ ሰው ሕይወት ውስጥ አንድ ነገር እንዳለ ያስታውሰኛል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ እኝህ ረጋ ያሉ፣ መልካም እና ከሁሉም ጋር በወንድማማችነት መንፈስ ይኖሩ የነበሩ ሰው ይጠቁ በነበረበት ወቅት “ሰይጣኖች ከእዚህ ሂዱ!” ብለው ለማውገዝ እና የእዚህን ጸያፍ ግድያን ዓላማ ከመግልጽ አልተቆጠቡም ነበር ብለዋል።

ከእዚህ የምንረዳው አሉ ቅዱስነታቸው “የእዚህ ጸያፍ ተግባር ዋንኛው ተዋናይ ስይጣን መሆኑን ነው” ብለው ይህ የሰማዕትነት ተግባር የኢየሱስን ሕይወት መመስከር ማለት ነው፣ ምክንያቱም እኝህ ፈረንሳዊ ካህን መስዋዕተ ቅዳሴን በሚያከናውኑበት ወቅት እንደ አንድ ወንጄለኛ መታረዳቸው የሚያሳየው ቀደም ሲል የነበሩ ክርስቲያናች ሕይወታቸውን መስዋዕት በማድረግ ክርስቶስን እንደ መሰከሩት አይነት መሆኑን እና እንዲሁም መስዋዕት በሚሆኑበት ወቅት ሁሉ “የእኛ እግዚኣብሔር ከእናንተ ጣዎት ይበልጣል፣ እውነተኛውም እርሱ ነው” በለው ይመሰክሩ እንደነበር በድጋሜ ያስታውሰናል ብለዋል።

“ዛሬም ቢሆን ክርስቶስን ለመካድ ባለ መፈለጋቸው የሚገደሉ፣ የሚደበደቡ፣ የሚታሰሩ የሚታረዱ ክርስቲያንች አሉ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የአባ ጃኩዊስ ሀሜል ታሪክም የእነዚህ ሰማዕታት ታሪክ አንድ ክፍል መሆኑን ገልጸው ዛሬም ቢሆን በእስር ቤት ሆነው ክርስቶስን መካድ ባለመፈለጋቸው ብቻ  የሚገረፉና  የሚሰቃዩ ሰዎች እንዳሉ አስታውሰው ይህ የማሰቃየት ተግባር “የሰይጣን ተጋብር ነው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማብቂያ ላይ “አባ ጃኩዊስ ሀሜል ስማዕት በመሆናቸው እና የየዋህነትን ፣ የወንድማማችነትን፣ የሰላምን፣ እንዲሁም እውነትን የመነናገር ወኔን ያሰጡን ዘንድ ልንጸልይ ይገባል፣ በእግዚአብሔር ስም መግደል ሰይጣናዊ ተግባር መሆኑን በድጋሚ አስታውሰው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.