2016-09-14 16:27:00

ሊቀ ጳጳሳስት ብፁዕ አቡነ ፖውል ሪቻርድ ጋላገር በአንዶራ


የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፖውል ሪቻርድ ገላገር በአንዶራ የኡርገል ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ዦኣን ኤንሪክ ቪቨስ ሲሲሊያና የአንዶራ መንግሥት ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 7 ቀን እስከ መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በዚያች በልኡል በምትመራው አገረ ይፋዊ ጉባኝት ማካሄዳቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ሕትመቱ አስነብቧል።

ብፁዕ አቡነ ገላገር በላ ሱአ ዱርገል ደርሰው ከተደረገላቸው የእንኳንድ ደህና መጡ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት በኋላ እዛው በአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባቅረቡላቸው የምሳ ማዕድ ተቋድሰው እንዳበቁ ከእገሪቱ መራሄ መንግስት አኖኒ ማራቲ ጋርና ከአግሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ጂልበርት ሳቦያ ሱንየ ጋር መገናኘታቸው የገለጠው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አያይዞ ከርእሰ ብሔር ቪሰንክ ማተኡ ጋር በቤተ መግሥት ተገኝተው እንዳበቁም ካሳ ደ ቫለ በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕንጻ ጎብኝት ማካሄዳቸውን ይጠቁማል።

ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጋላገር እ.ኤ.አ መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገሪቱ ጠባቂ ቅድስት እመቤት ዘመሪቲክሰል ቤተ መቅደስ በአገሪቱ ብሔራዊ በዓል ምክንያት ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው እንዳበቁም አዲሱን የቅድስት ማርያም ዘመሪትክሰል ቅዱስ ሐውልት ባርከው  እዛው ከተሳተፉት የአገሪቱ መንግስት የበላይ አካላትንና ምእመናንን ሁሉ ጋር ተገናኝተው ለክብራቸው የቀረበላቸውን የአገሪቱ ባህላዊ ትርኢት ተከታትለው እንዳበቁም በሆቴል ካኒሎ ከአገሪቱ ውሉደ ክህነትና ብፁዓን ጳጳሳት ጋር ተገናኘው ወደ መንበረ ጳጳስ ተመልሰው በአገሪቱ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በአገሪቱ መንግሥት የበላይ አካላት አሸኛኘት ተድርጎላቸው ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው በዚያኑ እ.ኤ.አ. መስክረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ አገረ ቫቲካን ተመልሰዋል ሲል ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.