2016-09-13 11:31:00

ቅዱስነታቸው "“በእግዚአብሔር ፀጋ ተደግፎ በኋጥያት ምክንያት ከወደቀበት ሥፍራ የማይነሳ ሰው የለም" ማለታቸው ተገለጸ።


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 11, 2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሳምንታዊ የጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት አስተምህሮ በእለቱ በተነበበው ወንጌል ላይ የተመስርተና “በእግዚአብሔር ፀጋ ተደግፎ በኋጥያት ምክንያት ከወደቀበት ሥፍራ የማይነሳ እና የማይለወጥ ሰው የለም፣ ኋጥያትን እየፈጸምን ብንሆንም እንኳን እግዚአብሔር ለእኛ መልካም ነገርን ከመመኘት ታቅቦ አያውቅም” ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ በተነበበው እና ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 15 ላይ በተወሰደው ምንባብ ላይ ተመስርተው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህ የምህረት ተግባራትን በሚገልጸው ምዕራፍ ውስጥ ኢየሱስ  በማጉረምረም ላይ ለነበሩ ፈሪሳዊያንና ጸሐፍት  ሦስት ምሳሌዎችን ተጠቅሞ መልስ መስጠቱን አስታውሰው በመጀምሪያ ምሳሌውም እግዚአብሔር 99 በጎችን ጥሎ “የጠፋውን 1 በግ ለመፈለግ እንደ ሄደ” እረኛ ተመስሎ እንደነበር አስታውሰዋል። 

በሁለተኛው ምሳሌ ደግሞ  አሉ ቅዱስነታቸው “ አንድ ሳንቲም የጠፋባት ሴት የጠፋባትን ሳንቲም እስከ ምታገኘው ድረስ አጥብቃ እንደ ምትፈልግ ዓይነት ሴት” ጋር የተነጻጸረ መሆኑን ገልጸው በሦስተኛም ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር “ርቆ ሄዶ የነበረ ልጁ በተመለሰ ጊዜ በደስታ ሊቀበለው እንደ ወጣ አባት” የተመሰለ መሆኑን ገልጸው ተጸጽተው ወደ እርሱ የሚመለሱትን ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር በታላቅ ደስታ እንደ ሚቀበል የሚያመለክቱ ምሳሌዎች እንደ ሆኑ ገልጸዋል።  

“በእነዚህ ሦስት ምሳሌዎች አማከይነት ኢየሱስ ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ህልውና መገለጫ የሆኑትን የተዘረጋ እጅ፣ ኋጥያተኞችን በርኅራኄ እና በፍቅር የሚቀበል መሆኑን አሳይቶናል፣ ይህም ምሳሌ ሁላችንን ይነካል ምክንያቱም ፍጻሜ የሌለውን የእግዚአብሔር ፍቅር የሚገልጽ በመሆኑ እና የጠፋውን ልጅ በሚያገኝበት ወቅት ወደ እራሱ ስቦ የሚያቅፈን አባት በመሆኑ” ነው ብለዋል።

ጠፍቶ በተገኘው ወጣት ልጅ አሳዛኝ ታሪክ ውስጥ በተለይም ደግሞ በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 15, 18 ላይ  የተጠቀሱት “ተነስቼ ወደ አባቴ ሊሂድ” የሚሉት ወሳኝ ቃላት መሆናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው ወደ ቤት የመመለሻው መንገድ የተስፋ እና የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ መንገድ ነው ብለው እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ወደ ትክክለኛው መንገድ እስክንመለስ ድረስ በትዕግስት ይጠባበቀናል፣ ገና በርቀት በምያየን ጊዜ እንኳን በፍጥነት ሊቀበለን ይወጣል፣ ያቅፈናል፣ ይስመናል፣ ይቅር ይለናል” በለዋል።

“እንዲህ ነው እግዚአብሔር እንዲህ ነው አባታችን፣ የእርሱ ምሕረት የቀድሞ ጥፋታችንን ይቅር ብሎ አዲስ ፍጥረት እንድንሆን ያደረገናል፣ የቀድሞ በደላችንን ይረሳል፣ እኛ ኋጥያተኞች በምንለወጥበት ወቅትና ወደ እግዚአብሔር በምንመለስበት ጊዜ አይረግመንም፣ አይጨክንም ምክንያቱም እግዚአብሔር አዳኝ በመሆኑ የተነሳ ወደ ቤቱ በደስታ ይቀበለናል” ብለዋል።

“ንስኋን በምናደርግበት ወቅት ሁሉ በሰማይ ሐሴት እና ፍስዐ ይሆናል ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ ወይ?” ይህንን ጥያቄ ማንሳት በጣም አስደሳች ነገር ነው” ካሉ ቡኋላ የመልዕከ እግዚአብሔርን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ደግመው እና በእለቱ በካዛኪስታን ለአቅመ ደካሞች፣ ለተቸገሩት እንዲሁም በሕይወት ዘመኑ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባሮችን በመፈጸም እግዚአብሔርን በሕይወቱ በመመስከሩ የብጽዕና ማዕረግ የተገኖናጸፈውን አባ ላዲስላዎ ቡኮዊንስኪ መጸለይ እንደ ሚገባ አሳስበው እና ቡራኬን ሰጥተው የእለቱ ዝግጅት ተጠናቁዋል።   

 








All the contents on this site are copyrighted ©.