2016-09-12 16:37:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ እውነተኛው ነጻነት የሚሰጠው እግዚአብሔር ብቻ ነው


እ.ኤ.አ. መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምሕረት ዓመት ምክንያት ዘወትር በዕለተ ቅዳሜ  የሚሰጡት ምሕረት ላይ ያተኮረ ይፋዊ  የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህ በመቀጠል ሐሰተኛው አታላይነትን ሁሉ እምቢ፡ እውነተኛ ነጻነት ከእግዚኣብሔር ነው በሚል ቀዉም ሃሳብ ላይ በማነጣጠር ከውጭና ከውስጥ በመጡት በጠቅላላ ከ 30 ሺሕ በላይ የሚገመቱት ምእመናን በተገኘበት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ገለጡ።

ቅዱነታቸው በዚህ ምሕረትና ድሕነት በተሰኘው ክሌስም ላይ ባተኮረው የዕለቱ አስተምህሮአቸው የአሁኑ ዘመን ሰው ነጻ መሆኑን በእግዚአብሔር ገብነት የዳነ መሆኑ የሚያፈቅር የሚያስተውል አይመስልም፥

በነፃነት ስም ባሮች የሚያደርጉ እንደ አደንዛዥ እጸዋት ሐሰተኛ እታላዮችን እምቢ

ሰው ይላሉ ቅዱስ አባታችን ነጻነቱ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠርና ለመጨበጥ የሚያስችለው ኃይል አድርጎ ይመለከተዋል። በዚህ ብቻ ሳይገታ ነፃነቱን እንዲህ ባለ መልኩ የሚመለከተውም በመሆኑ ኩራትና ርእሰ ብቃት ይሰማዋል። በአሁኑ ወቅት ነጻነት በሚል ስምና በነጻነት ስም ብዙ አታላይ ነገሮች ይቸረቸሩለታል። በሐሰተኛው ነጻነት መሳይ ስም ብዙ አዳዲስ የባርነት ቀንበሮች ያቀርቡለታል። ይኸንን ያንን ደስ ስላለኝ አደርጋለሁ። አደንዛዥ እጸዋት ለመውሰዱም ነጻ ነኝ፡ እንዳሻኝ ለማድረግ ነጻ ነኝ። ነጻነት እንዳሻኝ በሚለ ቃለ ተግባር ሲተረጎምና ሲኖር እናያለን። ይኽ ባርነት ነው። በነጻነት ስም ባርያ ሆኖ መኖር። ይኸንን የሚኖሩ ብዙ አይተናል። ተዘርረው ሲወድቁም ታይተዋል ይታያሉም፡ ከማንኛውም ዓይነት የሐሰት ነጻነና ከግድየለሽነት ከስግብግብነትና ማንም አያስፈልገኝም ከሚለው ከትዕቢተኛ ርእሰ ብቃት እግዚአብሔር ያድነን።

እግዚአብሔር በምሕረት በፍቅርና በሐሴት የታነጸ ሕይወት ለእኛ በመጸገው መስዋዕት በመሆን አድኖናል።

በስቃይና በመከራ ከወደቅንበት ሁነት ሁሉ የእግዚብሔር መሐርያን እጆች ያነሱናል።

የምንፈተንበት ሁነትና ጊዜ አለ። እንሰቃያለንም ሆኖም በዚህ በስቃይና ፈተና ወቅት እይታቸውን ስለ እኛ ብሎ ከእኛ ጋር እግዚአብሔር ፈጽሞ እንደማተወን ወደ ሚያረጋግጥልን ወደ ተሰቀለው ኢየሱስ እናደርግ ዘንድ እንጠራለን። መቼም ቢሆን በስቃይና በመከራ በስደትና በዕለታዊ ስቃይ ሁሌ ወደ እርሱ ቀና በሚያደርጉን በእግዚአብሔር መሐሪያን እጆቹ ነጻ እንደምንወጣ መርሳት የለብንም።

እግዚአብሔር ለተናናሾችና ለተናቁት አቢይ ርህራሄ አለ

የእግዚአብሔር ፍቅር ወሰን አልቦ ነውና ዕለት በዕለት እርሱ ለእኛ ያለው አሳቢነት የምንለይበት አዳዲስ ምልክቶችን ለይተን ማወቅት ያስፈልገና። መላ ሕይወታችን በሐጢአት ተነቃፊዎች ብንሆንም በእነዚያ በሚያፈቅሩን የእግዚአብሔር አይኖች ሥር ነን። ለሁሉም በተለይ ደግሞ ለእነዚያ በከፋ ስቃይና ድኽነት ለሚገኙት ሁሉ ቅርብና ርህሩህ ነው።

ለተናናሽና እራሳችውን ለመከላከል ለማይችሉት እቅመ ደካሞችና በሕብረሰብ ለተናቁት ሁሉ  እግዚአብሔር በምህረቱና በቸርነቱ ትልቅ ነው። በበለጠ ድኾችና ምንም ነገር የሌለን መሆናችን ስንገነዘብ የእርሱ እይታ ለእኛነታችን በምሕረቱ በበለጠ ቅርብ ይሆልናል። ድካማችንን ሁሉ የሚያወቅ በመሆኑም በአዛኙ ምሕረቱና በርህራሄው ቅርባችን ይሆናል። ሓጢአታችንን ሁሉ ያውቃልና ይምረናል። ዘወትር ይምራል! አባታችን እርሱ እጅግ ደግና መሓሪ ነው።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሉንም ከተያየ የዓለማችን ክልል የመጡትን ምእመናን አመስግነውና በወጣቶች ዓውደ በዓል በመሳተፍል ላይ ለሚገኙ ለካቶሊክ ተግባር ማኅበር አባላትና በዚህ በምሕረት ዓመት በመናብርተ ጥበብ ኢዮቤል በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ ሁሉ ሰላታቸውን አቅርበው እንዳበቁም እ.ኤ.አ. ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢጣሊያ ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት ምክንያት ወደ ክልሉ በመሄድ በፈጥኖ ደራሽ አገልግሎ በመሰማራት ያገለገሉትና እያገለገሉ ያሉት የፈጥኖ ደራሽ የበጎ ፈቃድ ማኅበር አባላት የኢጣሊያ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ አደጋ መከላከያ አገልግሎት አባላትን ሁሉ ሰላምታን አቅርበው  ውፉይነታቸውና የሚኖሩት ግብረ ደግነት የሚደነቅ ነው ብለው አመስግነው ለሁሉም ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ወደ መጡበት መሸኘታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.