2016-09-09 16:22:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ ተግባር ፊት ሃይማኖቶች አልቦ ልሳን ከመሆን ይቆጠቡ


አማኝ ሕይወትና ተፈጥሮን የሚከላከልና ከማንኛውም ዓይነት ቅጣት ነጻ እየሆነ ያለው  የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ ፊት እጁን አጣምሮ ሊቀመጥ አይገባውም፥ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ኃይለኛ ጥሪ እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በጳጳሳዊ አጎስጥቲኒያኑም መንበረ ጥበብ ባለው የጉባኤ አዳራሽ “አመሪካ በውይይት፡ የጋራ ቤታችን” በሚል ርእስ ሥር በጠቅላላ የአመሪካ አገሮችና የቦኖስ አይረስ የውስጠ ሃማኖቶች የውይይት ተቋም ከጳጳሳዊ የውስጠ ሃይማኖቶች (የተለያዩ ሃይማኖቶች) የጋራ ውይይት የሚነቃቃው ምክር ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ዓውደ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የሚገኙትን 200 ተጋባእያንን እ.ኤ.አ. መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን  በሚገኘው በብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ።

ይኽ በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጉባኤ ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸክሶ ምህዳር ዙሪያ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ማእከል ያደገ ሲሆን ቅዱስነታቸው በዓዋዲ መልእክት ብቻ ሳይሆን  እ.ኤ.አ. በ2015 ዓም. በሳቸው ውሳኔና አሳቢነት የተነቃቃው የተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች በጋራ የሚያከብሩት ባለፈው ሳምንት እ.ኤ.አ. መስከረም 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከበረው ሁለተኛው የዘፍጥረት ቀን ዓላማውን የሚያበክር ዓውደ ጉባኤም ጭምር መሆኑ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ በማያያዝ ቅዱስነታቸው በለገሱት ምዕዳን፥ ይኽ አመሪካ በውይይት በሚል ርእስ ሥር የተጠራውና በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጉባኤ ጅማሬው ለአመሪካውያን አገሮች ብቻ ሳይሆን ለመላ ዓለም ጭምር አስፈላጊነት ያለው ነው። በእውነቱ ተፈጥሮንና ፍጥረት ሁሉ የሚያከብር ሰው የፍጥረት ሁሉ አናት መሆኑ እውቅና የሚሰጥ ምሉእ ምህድር መከወን እንዳለበት ተገንዝበን ይኸንን ዓላማ በማድረግ መሰራት እንዳለበት መታመን ያስፈልጋል። በዚህ ተኪዶ ሁሉም ሃይማኖቶች በተፈጥሮና በፍጥረት ዘንድ ያለው ውበትና ውህበት አማካኝነት ህልወተ እግዚአብሔ የሚያስተውሉ በመሆናቸውም የሚስጡት አስተዋጽኦና ያለባቸው ኃላፊነት መሰረታዊ ነው እንዳሉ ገልጠዋል።

ሕይወትንና የሰብአዊ መብትና ክብር ለመከላከል ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች መተባበር ግድ ነው

መከባበርና ማንነት አቅቦና የእያንዳንዱ ማንነት በማክበር ላይ የጸና የጋራው ውይይት አማካኝነት የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ትብብር ተፈጥሮና ፍጥረትን ለመንከባከብ ለሚደረገው ጉዞ ወሳኝ ነው። ይኸንን ያስቀደመ የግኑኝነት ዘር  በፍሬ እጅግ ሃብታም ወደ ሚሆን ዛፍ ይለወጣል። የእርስ በእርስ መከባበር ከሌለ የውስጠ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት አንደ ማይኖር ነው፡ አማኝ የተፈጥሮና የሕይወት ጠበቃና ተከላካይ ነው። ስለዚህ የሰብአዊ መብትና ክብር ግብረ ረገጣ ባለበት ሁሉ እጆቹን አጣምሮ መኖር አይችልም አይገባውም።

አማኝ ወንድና ሴት ካለ ምንም ማመንታ ሕይወት በሁሉም ደረጃዎቹ የሚከላከሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ከአካላዊ ምሉእነት እስከ መሰረታዊ ነጻነት እርሱም የሕሊና የሃይማኖት ሃሳብህን የመግለጥ ነጻነት ተማጓች መሆን ይገባዋል። እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው። ዘፍጥረትና ሰው ሥሪቱ ናቸው፡ ዘፍጥረትና ሰው ለእግዚአብሔር እጆች መሣሪያ ናቸው። የሁሉም ፍጥረት ክብርና ክዋኔነታቸው እንዲረጋገጥ ዘፍጥረትና ፍጥረት ለእግዚአብሔር እጅ መሣሪያ ናቸው እንዳሉ ዶኒኒ አስታውቀዋል።

ከኢአማኒያን ጋር ጭምር መተባበር

ዓለም የአማኞችን አግባብ አካሄድ አመልና እንዴትና ምን መሆኑ ለማወቅ ለማየት ትኵረቱ በአማኝ ላይ ያደርጋል። ይኽ ደግሞ በመካከላችን መልካም ፈቃድ ካላቸው ኢአማኒያን ሰዎች ጋር የምንተባበር መሆን እንዳለብን ያስገነዝበናል። በዓለም ለሚታየው ስቃይ በተስፋ እጦት ለሚሰቃየው ሰው ልጅ፡ እርሃብ ጦርነት ምህዳራዊ ቀውስ የመሳሰሉትን ሁሉ ለመቅረፍ የሚደረግ ትብብር ነው።

ዓለም በስቃይ ላይ ይገኛል፡ የተለያዩ ሃይማኖቶች የሚሰጡት ጣምራዊ ትብብርና ድጋፍ ያሻዋል። ይኽ ጣምራዊ ትብብር ዓለም ሳይቀር የሚጠይቀው ተግባር ሲሆን። ነገር ግን ሌላውን ሃይማኖቱን እንዲቀይር ከሚያደርግ ወትዋች ግብረ ስብከት ነጻ ነው፡  የሚያሳዝነው በእግዚአብሔር ስም እኵይ ዘግናኝ ተግባር ለምሳሌ ግብረ ሽበራ የመሳሰሉት ጸረ ሰባአዊ ተግብር ሲፈጸም ማየቱ ነው፡ የዚህ አይነቱ አሰቃቂ ግብረ ሽበራ መቃወም ማውገዝ ከዚህ ዓይነቱ የሰውን ልጅ መንፈስ ወደ የክፋት መንገድ ከመምራቱ ድርጊት እራስን ማግለል ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻርም ሲታይም የሁሉም አይማኖቶች የጋራ የውይይት መርሃ ግብር አስፈላጊ መሆኑ የማያጠያይቅ ይሆናል፡ በጋራ አንዱ ሌላውን በመንከባከብ ለመጓዝ ስቃይና ተስፋ ማጋራት ይኖርብናል ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አያይዘው፥ የበለጠው ዓለም ለመጻኢ ትውልድ ጥሎ ማለፍ በእውነት አስፈላጊና ተገቢም ነው፡ ብለው በዓለም እየተስፋፋ ያለው እራስ ወዳድነት ለእኔና ባይነት የሚል ሕይወትን የሚይገል ባህል ጠቅሰው፥ ነገር ግን የበለጠው ዓለም የሚረከብ መጻኢ ትውልድ ይኖራልን ወይ? የሚል ጥያቄ ለተገባእያኑ ማቅረባቸው የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታወቁ።

ይኽ አመሪካ በውይይት በሚል መርሕ ቃል ሥር በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጉባኤ በዚህ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምሕረት ዓመት ወቅት የሚከናወን በመሆኑም ኵላዊ ክብር አለው። ሁሉንም አማኙም ኢኣማኙንም የሚያጠቃልል ነው።  ምክንያቱም የእግዚአብሔር መሐሪው ፍቅሩ ወሰን የለውም። የባህልም የዘግወም የቋንቋ የሃማኖትም ወሰን የለውም። ሁሉንም በሥጋና በነፍስ የሚሰቃዩትን የሚያቅፍ ነው፡ የእግዚአብሔር ፍቅር መላ የእርሱ ሥሪት የሆነውን ፍጥረት ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ ይላሉ ቅዱስ አባታችን አማኞች ያለባቸውን አቢይ ኃላፊነት ማስተዋል ይገባል። ይኽ የምሕረት ቅዱስ ዓመት ወደ ሚሰቃየው ወንድም እንድንልና እንዲሁም ዘፍጥረትን ለመከላከል የሚያነቃቃን ሁነት ይሁንልን፡ እያንዳንዱ ሰው እግዚኣብሔር ከሚሰጠው ጸጋዎች ሁሉ የላቀ ነው ብለው እያንዳንዱ ተጋባኢ ሁሉም አስፈላጊ የሆነበት ሰብአዊነት የተካነው ዓለም እንዲገነባ የሚያነቃቁ እንዲሆኑ አደራ ብለው የለገሱት መሪ ቃል ማጠቃለላቸው ዶኒኒ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.