2016-09-07 16:42:00

እ.ኤ.አ. የወርሃ መስከረም 2016 ዓ.ም. የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሐሳብ


በዓለማችን ለሚታዩት ቀውስ መልሱ መደጋገፍና መተባበር የሚል መሆን አለበት። ምክንያቱም እያንዳንዱ ስለ የጋራ ጥቅምና ሰብአዊነትን ማእከል ያደረገ ኅብረተሰብ እንዲጸና የሚገባውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ለቡ የሚል በመሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በስፓንሽ ቋንቋ ባስተላለፉት ከዛም አረብኛና ቻይንኛ ቋንቋዎች በሚያጠቃልሉ በሌሎች 8 ቋንቋዎች የተተረጐመው የድምጸ ራእይ መልእክት አማካኝነት በማበከር እ.ኤ.አ. መስከረም ወር 2016 ዓ.ም. የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሐሳብ ምን መሆን እንዳለበት ማሳወቃቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታወቁ።

በዚህ በመንፈስና በማኅበራዊና አካላዊ ስቃይ እየተጥለቀለቀ ባለው ዓለም እያንዳንዱ እንቅስቃሴና የሕይወት እክሎችን ሊያገል የሚችለው ሰብአዊነት ማእክለ ሲያደርግ ነው። ሰብአዊ ፍጡር እጅግ አሳሳቢ በሆነው በኤኮኖሚያዊና በቁጠባዊ ብቻ ሳይሆን ምኅዳራዊ በስነ ትምህርት በግብረ ገባዊና በሰብአዊ ቀውስ ጭምር እየተነካ ነው። እንዲህ ያለ አዳጋችና ጠጣራማው ሁነት የሚፈጥረው ምስቅልቅልና መደናገር እንዲሁም ስቃይ ለመተባበርና ለመደጋገፍ የሚገፋፋ አጋጣሚ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት የድምጸ ራእይ መልእክት በማብራራት ከዚ በመንደርደር ሁሉም ለጋራ ጥቅምና ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ ኅብረተሰብ ለማነጽ በሚደረገው ጥረት የሚጠበቅበት አስተዋጽኦ እንዲያበረክት፥ እግዚአብሔር ሆይ ናና እርዳን ብለው የወርሃ መስከረም 2016 ዓ.ም. የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሐሳብ ምን መሆን እንዳለበት ማስገንዘባቸው ጂሶቲ ያመልክታሉ።
All the contents on this site are copyrighted ©.