2016-09-05 15:09:00

በመሰከረም 4,2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ብጽዕት እማሆይ ቴሬዛ ወደ ቅድስና ማዕረግ ከፍ ማለታቸው ታወቀ።


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመሰከረም 4,2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከመቶ ሃያ ሺ በላይ የሚቆጠሩ የብጽዕት እማሆይ ቴሬዛ ወዳጅ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ለሰው ልጆች ዘር ሁሉ ሐይማኖት ሳይለዩ ሌት ተቀን በተለይም ደግሞ በአስከፊ ድህነት ምክንያት በየመንገዱ ወድቀው የሚገኙ ሰዎችን በመሰብሰብ ይነከባከቡ የነበሩ ብጽዕት እማሆይ ቴሬዛ ከብጽዕና ወደ ቅድስና ማዕረግ  በእርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ ከፍ ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ ቅዱስነታቸው ባሰሙት የወንጌል ስብከታቸው እንደ ገለጹት ይህንን ታላቅ በዓል ለመታደም በመምጣታችው እጅግ በጣም አመሰግናለሁኝ በማለት ስብከታቸውን  ጀምረው በተለይም ደግሞ በስፍራው ለተገኙ በእማሆይ ቴረዛ በተመሰረተው የፍቅር ሥራ ልዑካን ማህበር ወይም missionaries of charity ለየት ባለ መልኩ ባስተላለፉት መልዕክታቸው እኝህ የእናንተ ማህበረ መሰራች የሆኑት እና በዛሬ እለት ወደ ቅድስና ማዕረግ ከፍ ያሉት ቅድስት ቴሬዛን አብነት በመከተል ሁል ጊዜም ቢሆን በአደራ ለተሰጣችሁ እግዚአብሄርን፣ ቤተ ክርስቲያን እና ድሆችን የማገልገል ኋላፊነታችሁን በትጋት መቀጠል ይኖርባችኋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ይህንን ታላቅ በዓል ለመታደም ለተገኛችሁ ከአዲስቷ ቅድስት ጋር የቀጥታ ግንኙነት የነበራችሁ ባለ ሥለጣናት እዚህ በመገኘታችሁ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለው በተለይም ደግሞ የቅድስት ቴሬዛን ማሕበር ሥራ የተመለከታችሁ እንዲሁም በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የእርሳቸው ሥራ ተካፋይ የሆናችህ ነጋድያን  የእዚህ ታላቅ ደስታ ተካፍይ ለመሆን እዚህ በመገኘታችሁ በድጋሜ አመሰግናለሁኝ እግዚአብሔር እናንተን እና ሀገራችሁን ይባርክ ዘንድ እጸልያለሁ ብለዋል።

በተጨማሪም እዚህ የተገኛችሁትን የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች ሁሉ ይህ ታላቅ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ለምታደርጉት ተግባራት የቅድስት ቴሬዛ መንፈሳዊ ጥበቃ ይበዛላችሁ ዘንድ እማጸናለሁ ብለው ቅድስት ቴሬዛ ኢየሱስን በእየ እለቱ እንድናሰላስለው እና እንድናመልከው እንዲሁም ለእኛ ሲል የተሰቀለውን ኢየሱስ  ወንድሞቻችንን እና በተለይም በችግር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ በማገልገል ልናከብረው እና ልናውቀው ይገባል ብለዋል።

በእዚህ አጋጣሚ በአስቸጋሪ እና አደገኛ በሁኔታ ውስጥ በመሆን ወንድሞቻቸውን እና እህቶቻቸውን እያገለገሉ የሚገኙ ሰዎች እንዳሉ ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁኝ ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ብዙ ገዳማዊያን ደናግላን ለሕይወታቸው ሳይሳሱ በቅንነት እያገለገሉ የገኛሉ ካሉ ቡኋላ በተለይም ደግሞ ከሁለት ቀናት በፊት በድህነት በምትጎሳቆለው በሀይቲ ህይወታቸውን ያጡት እስፔናዊ ሚስዮናዊ ደናግልን ማስታወስ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው እንዲህ አይነቱ የብጥብጥ ድርጊት ተወግዶ ሰላም እንዲሰፍን እና በተለያዩ ሀገራት በተመሳስይ ሁኔታ የሚገኙ ደናግላን እና የበጎ ፈቃድ ሰራታኞችን የእግዚኣብሔር ጥበቃ ይበዛላቸው ዘንድ እናታችን እና ንግሥት በሆነችሁ በእመቤታችን ቅድስት ድንጋል ማሪያም አማልጅነት መማጸን ያስፈልጋል ብለው መልዕከ እግዚኣብሔር የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ደግመው እና ቡራኬን ስጥተው የእለቱ ዝግጅት ተጠናቁዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.