2016-09-04 11:25:00

የብጹዕ ገብረ ሚካኤል አጭር የሕይወት ታሪክ


ብጹዕ ገብረ ሚካኤል እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1790 አከባቢ በቀድሞ የጎጃም ክፍለ ሀገር የተወለዱ ስሆን በልጅነታቸውም ግራ ዓይናቸውን በአደጋ በማጣታቸው ምክንያት በጊዜው በነበረው የሀገሩ ባሕል ለተለያዩ የሥራ መስኮች ተግቢ ሰው እንዳልሆኑ ይቆጠሩ ነበር። በእዚህም ምክንያት የተነሳ እስከ ተወሰነ ደረጃ ድረስ መሰረታዊ እውቀትን ከጨበቱ ቡኋላ ወደ ገዳም በመግባት ታታሪ ተማሪ መሆናቸውን አስመስክረዋል።

ብጹዕ ገብረ ሚካሄል የምንኩስና ሕይወት ታሪክን የማጥናት ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት የነበራቸው ስሆን በጊዜው የነበረው የገዳም ሕይወት የአኗኗር ዘይቤ ከአጠቃላይ የምንኩስና ሕይወት የአኗኗር ዘይቤ በደረጃው ዝቅ ያለ ሁኖ ስለተሰማቸው ከአለቆቻቸው ፈቃድ በመጠየቅ የእዚህን ችግር መንስሄ ለማጥናት ተነሱ። ይህም በተለያዩ በሀገሪቷ ውስጥ የሚገኙትን ገዳማት የመጎብኘትን እድልን እና በገዳማቱ ውስጥ የሚገኙትን ጥንታዊ የሆን መጽሐፍትን የማንበብ እድልን ከፈተላቸው።

በሚጎበኙባቸው ገዳማት ውስጥ ሁሉ በእዚያ ከሚገኙ ገዳማዊያን መካከል የተወሰኑትን መርጠው እና እንዴት ጥናት ማካሄድ እንደ ሚኖርባቸው መመሪያ በመስጠት በገዳም ሕይወት ውስጥ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረከቱ ስሆን ባካሄዱት ከፍተኛ ጥናትም ደረጃውን ያልጠበቀ የገዳም ሕይወት የተንሰራፋበት ዋንኛው ምክንያት ገዳማዊያን በቂ የሆነ የነገረ መለኮት ትምህርት ስላልነበራቸው መሆኑን ደርሰውበታል።

ይህንንም መሠረታዊ ችግር ለመቅረፍ ያስችላቸው ዘንድ መፍትሄን ለመፈለግ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደው በቂ የሆነ ጥናት ማድረግ እንደ ሚኖርባቸው በመረዳታቸው የእርሳቸውን ሐሳብ የሚጋራ እና ተመሳሳይ የሆነ ጥናት ለማድረግ የሚፈልግ ሰው ባለማግኘታቸው ብቻቸውን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ተነሱ።

በጊዜው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አንድ ብቻ የነበረ እና ይሾም የነበረውም በግብጽ ሀገር በአሌክሳንዴሪያ ከሚገኘው የኮፕቲካ ፓትርያርክ የነበረ በመሆኑ፣ እንዲሁም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ከ1840-1841 የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ስላልነበራት ይህንን ጉዳይ በአሌክሳንደሪያ ለሚገኙት የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ለማቅረብ በተቋቋመው ቡድን ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደረጎ የነበረ ስሆን  ልዩ በሆነ ሁኔታም ይህንን ቡድን አቡነ ያይቆብ እንዲቀላቀሉ  ተደርጎ የነበረ ስሆን በወቅቱ ይህ ቅዱስ አቡነ ያዕቆብ ይህ የተቋቋመው ቡድን የሮም ጳጳስን እንዲጎበኝ መንገድ በማመቻቸት በሁለቱ እህት አብያተ ክርስቲያናት መኋል መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር የበኩላቸውን አስተዋጾ አበርክተዋል። የተላከውም ቡድን በቅድሚያ ወደ አሌክሳንደሪያ ከእዚያም ወደ ሮም ከሮም ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ በመጨረሻም ወደ ኢትዮጲያ ተመልሰዋል።

ይህ የተደረገው ረዢም ጉዞ ቅዱስ አቡነ ያዕቆብ እና ብጹዕ ገብረ-ሚካኤልን በሚገባ እንዲተዋወቁ እድል ከፍቶላቸው የነበረ ስሆን ወደ መጀመሪያ አከባቢ አቡነ ያዕቆብን የካቶሊክ ካህን በመሆናቸው የተነሳ ብቻ ብጹዕ ገብረ ሚካኤል ብዙ ምቾት ተሰምቱዋቸው ያልነበረ ስሆን ቀስ በቀስ ግን እየተግባቡ በመምጣታቸውና በጉዞ ሂዴት ውስጥ አቡነ ያዕቆብ ለሰዎች ያሳዩ በነበረው መልካምነት የተነሳ ቅን ሰው መሆናቸውን እየተረዱ መጡ።

በጹዕ ገብረ ሚካኤል በእውነት ላይ የተመሰረት የነገረ መልኮት ትምህርት ፈላጊ በመሆናቸው የተነሳ ከብዙ ሰዎች ከጓደኞቻቸውም ስይቀር ውግዘት ይወርድባቸው እንደ ነበር እና በእዚህም የተነሳ ብዙ ባለ አንጣ ተንስቶባቸው እንደ ነበር ታሪካቸው ያወሳል።

የነገረ መለኮት እውነተኛ ገጽታን ለሁሉም ለማስተማር በማሰባቸው አዲስ ወደ ተሾሙ የኦርቶዶክስ ጳጳስ ሄደው ጉዳዩን አማክሮዋቸው የነበረ ስሆን ነገር ግን ጳጳሱ በከፍተኛ ሁኔታ ሐሳቡን በመቃወማቸው የተነሳ ብጽዕ ገብረሚካሄል ተስፋ ስይቆርጡ ከአቡነ ያዕቆብ ጋር በድጋሚ ውይይት ለማድረግ ፍሎጎታቸውን በማሳየታቸው እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም ወር 1843 ተገናኝተው ቀደምት የነበረውን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የሆነውን የነገረ መልኮት አስተምህሮ ተመልሶ ይሰፍን ዘንድ ጥረት ማድረጋቸውን ቀጠሉ። ይህ በተደጋጋሚ ያቀረቡት የእውነትን ፍለጋ ተማጽኖ ስላልተሳካላቸው በመስከረም ወር 1843 ብጹዕ ገብረ ሚካኤልን ጨምሮ 37 ኢትዮጲያዊያን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባላት ሆኑ።

ቅዱስ አባነ ያዕቆብ ኢትዮጲያ ከገቡ 5 ዓመታትን ብያስቆጥሩም ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ ግን ስላልነበራቸው አንድ ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ ለማቋቋም ወሰኑ። በእዚህም የተነሳ ጓላ በተባለው ሥፍራ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1844 አንድ የመኖሪያ ቤት አቋቋሙ። ነገር ግን ከ1 አመት ቡኋላ በካቶሊኮች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስደት ደረሰባቸው ብጹዕ ገብረ ሚካኤልም ለተወሰኑ ወራት በእስር ቤት እንዲቆዩ ተገደዱ።

እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1850 ብጹዕ ገብረ ሚካኤል የካቶሊክ እምነትን ከተቀላቀሉ ከስድስት ዓመት ቡኋላ ቅዱስ አቡነ ያዕቆብ ብጹዕ ገብረ ሚካኤልን እንዴት ከምንኩስና ወደ ካህነት መሻገር እንደ ሚችሉ ማሰቡን ተያያዙት (በጊዜው ብዙ ካህን ያልሆኑ መነኩሴዎች ነበሩ) ቅዱስ አቡነ ያዕቆብ ጉዳዩን በጥልቀት ካሰቡበት ቡኋላ ብጹዕ ገብረ ሚካኤል የክህነትን ማዕረግ ሊቀበሉ ፋላጎት እንዳላቸው ጠየቁዋቸው እሳቸውም በሐሳቡ ተስማሙ በእዚህም መሰረት እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 1-1851 የካቶሊክ ካህን ሆነው ተቀቡ።

በተመሳስይ አመት በሰኔ ወር ላይ ቅዱስ አቡነ ያዕቆብ እና ብጹዕ ገብረ ሚካኤል፣ እንዲሁም በተጨማሪም  ሌሎች 4 የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑ ሰዎች ለእስር ተዳረጉ። ኢትዮጲያዊያን እስረኞች በመሬት ላይ በተጋደመ ግንድ ላይ በተቦረቦረ ቀዳዳ ውስጥ እግራቸውን እንድያስገቡ ተገደው የነበረ ስሆን የእዚህም ስደት ዋነኛ ምክንያት የነበረው በጊዜው የነበሩ ጳጳስ የካቶሊክ እምነት እንዳይስፋፋ በመፈለጋቸው እና በተለይም ደግሞ ቅዱስ አቡነ ያዕቆብ ላይ ጫናን በመፍጠር ከሀገር እንዲወጡ ለማድረግ ስለፈለጉ ነው።

እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1855 በጊዜው ንጉሥ ሆነው የተሾሙት አጼ ተውድሮስ አንድ ሀገር አንድ እምነት የሚል መመሪያ ይከተሉ ስለነበር በእስር ላይ የሚገኙ ብጹዕ ገብረ ሚካኤልን እና ሌሎች እስረኞችን ካሀዲዎች እንደ ሆኑ እንድያምኑ እና ከእዚያም ከእስር እንደ ሚፈቱዋቸው ጠይቀዋቸው የነበረ ስሆን እነርሱ ግን ይህንን ማመን ስላልፈለጉ በእስር እንዲቆዩ ተገደዱ።

እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1855 የእንግሊዝ ሀገር ቆንሲል አባል የሆኑ ተወካዮች ንጉሡን ለመጎብኘት በመጡበት ወቅት ብጹዕ ገብረ ሚካኤል እና ጓደኞቻቸው በጊዜው ለፍርድ ቀርበው የነበረ ስሆን ካሀዲዎች እንደ ሆኑ በድጋሚ እንድያምኑ ተጠይቀው አሻፈረኝ በማለታቸው የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸዋል። በወቅቱ የነበሩ የእንግሊዝ ሀገር ቆንሲል አባላት ብጹዕ ገብረ ሚካኤል እንዳይገደሉ ተማጽነው የነበረ ስሆን ከንጉሡ አጃቢ ወታድሮች ጋር በሰንሰለት ታስረው በሚጓዙበት ወቅት በደረሰባቸው መከራ እና እንግልት ምክንያት እንደጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 28-1955 ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ በሞቱበትም ሥፍራ በነበረ ዛፍ ሥር ተቀበሩ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የተቀበሩበትን ትክክለኛ ሥፍራ ማወቅ ግን አልተቻለም።

እውነትን ፍለጋ ባደረጉት ጥረት እና በሐይማኖታቸው ጸንተው በመቆየታቸው ምክንያት ብቻ በደረሰባቸው መከራ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1926 በጊዜው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ በነበሩት በፒዮ 11ኛ የብጽዕና ማዕረግ ተሰጣቸው።

ብጹዕ ገብረ ሚካኤል ቅዱስ ቪንሰንት ዲ ፖል የመሰረተው  የላዛሪስት ማህበር ተከታይ የሆኑት የቅዱስ አቡነ ያዕቆብ ተከታይ የነበሩ ቢሆንም ቅሉ በላዛሪስት ማህበር ታሪክ ጎልተው እንድታዩ ያበቁዋቸው ሦስት ዋና ዋና ነገሮች አላቸው። እነዚህም

  1. የመጀምሪያው ጥቁር አፍሪካዊ መሆናቸው

  2. ከቆያታ ቡኋል የካቶሊክን እምነት መቀበላቸው እና

  3. በመጨረሻም የላዛሪስት ማሕበር አባል ሳይሆኑ ማለፋቸው ይጠቀሳል።

 

 

 
All the contents on this site are copyrighted ©.