2016-08-30 14:42:00

ቅዱስነታቸው የፌስቡክ ተባባሪ መስራች ከሆነው ማርክ ዙከንበርግ እና ከባለቤቱ ፒሪሴላ ቻን ጋር በቫቲካን ተገናኙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በነሐሴ 29-2016 የFacebook ተባባሪ መስራች፣ ባሌበት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆነው ማርክ ዙከንበርግ እና ከባሌበቱ ፒሪሴላ ቻን ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው ታወቀ።

የቅድስ መንበረ የሕትመት ቢሮ ግንኙነቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ መረደታ እንደ ተቻለው ቅዱስነታቸው ከማርክ ዙከንበርግ እና ከባለበቱ ቻን ጋር በተገናኙበት ወቅት ትኩረት አድርገው የተወያዩት ፣ “ድህነትን ለመቅረፍ፣ የሰዎችን የውይይት ባሕል ለማዳበር፣ የተስፋን መልዕክት ለማስተላለፍ በተለይም ደግሞ በአስከፊ ችግር ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን እንዴት መጠቀም እንደ ሚቻል” መወያየታቸው ተገልጹዋል።

Philanthropy የተሰኘው መጽሄት በ2013 “A look at the 50 most generous Donors of 2013” በሚል አርዕስት ሥር ባሳተመው ጹሑፍ ላይ ማርክ ዙከንበርግን እና ባለበቱን ቻን የጠቀሰ ሲሆን በ2013 ብቻ 18 ሚልዮን የአሜርካን ዶላር ለበጎ ሥራ ይሆን ዘንድ ማበርከታቸው በዓለም ውስጥ ከሚገኙ ጥቂት ሀብታም ደጋግ ሰዎች መኋል እንዲመደቡ አድርጎዋቸኋል።

Faccbook የዛሬ 12 ዓመት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 4-2004 የሀርቫርድ ዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች በነበሩት በማርክ ዙከንበርግ እና በጓደኛው ኤድዋርዶ ሳቬሪን ተመስርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ማህበራዊ ድህረ ገጽን መቀላቀሉ የሚታወቅ ሲሆን Statista የተሰኘው ድህረ ገጽ እንዳሰፈረው እስከ ያዝነው የ2016 አጋማሽ ድረስ በዓለም ላይ 1.71 ቢሊዮን የእለት ተእለት ተጠቃሚዎች እንዳሉትም ለመረዳት ተችሉኋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.