2016-08-30 11:11:00

ቅዱስነታቸው በርዕደ መሬት አደጋ የተጎዱ አከባቢዎችን ለመጎብኘት ማሰባቸውን ገለጹ


አንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 23-2016 በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 9,36 ደቂቃ አከባቢ ከሮም ከተማ በስተ-ሰሜን ምስራቅ በሚገኙ አከባቢዎች በሬክተር እስኬል ወይም በመሬት መንቅጥቀጥ መለኪያ መሳሪያ 6.2 ያስመዘገበው ርህደ መሬት መከሰቱን በወቅቱ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረበት እለት ሕጻናት የሚበዙበት የ391 ሰዎችን ነብስ የቀጠፈና  በተለይም ከሮም ከተማ በመቶ ሃያ ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በአማትሪቼ እና በአኩሙሊ  እንዲሁም መጠነኛ ጉዳት በደረሰባቸው በላዚዮ፣ ሁብሪያ እና በማርኬ በተከሰተው ርህደ መሬት የተሰማቸውን ከፍተኛ ሐዘን  ቅዱስ አባታችን ፍራቼስኮ በእለቱ መግለጻቸው መዘገባችን ይታወሳል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙት ምዕመናን እና የሀገር ጎቢኝዎች ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልዕክት በእዚህ የተፈጥሮ አደጋ ሰለባ ለሆኑ ሰዎች የማበረታቻ መልዕክታቸውን የላኩ ሲሆን ቀደም ሲል ባስተላለፉት መልዕክታቸው በጸሎት እና ተጨባጭ የሆነ አጋርነትን ለማሳየት የገቡትን ቃል በማደስ በተቻለ መጠን በፍጥነት የአደጋው ሰለባ የሆኑ ቦታዎችን ለመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸውም በእለቱ ገልጸዋል።

ልማዳዊ በሆነው እና ዘወትር ሮዕቡ እና እሑድ እለት እንዲሁም ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ በእለተ ቅዳሜ በቅዱስ ጴትሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 28-2016 ካሳረጉት የመላዕከ እግዚአብሔር ጸሎት ቡኋላ ባስተላለፉት መልዕክታቸው በእዚህ እርዕደ መሬት አደጋ የተጉዱ ሰዎችን ትኩረት ባደረገው መልዕክታቸው እንደ ገለጹት “በከፍተኛ የርህደ መሬት አደጋ በተጠቁ በላዚዮ፣ በማርኬ እና በሁንብሪያ አከባቢ ለምትገኙ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በችግራችሁ ወቅት መንፈሳዊ አጋርነት በማሳየት ከእናንተ ጋር ለመሆን  የገባሁትን ቃሌን በድጋሜ በማድስ እፈልጋለሁ” ማለታቸው ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ በእዚህ የርህደ መሬት አደጋ ከፍተኛ የሆነ አደገ የደረሰባቸውን በተለይም ደግሞ ከፍተኛ ጉዳትን ያስተናገዱትን ከተሞች አስምልክተው እንደ ገለጹት “በአማትሪቼ፣ በኩሙሊ፣ አርኩዋታ ደል ቶሮንቶ እንዲሁም በኖርቺያ ለምትገኙ ውድ ወንድሞቼ፣ ቤተ ክርስቲያን የእናንተን ሥቃይ እና ጭንቀት እንደ ምትካፈል ላሳውቃችሁ እፈልጋለሁ” ማለታቸውም ተገልጽዋል።

“ቤተ ክርስቲያን ሕይወታቸውን በአደጋው ላጡ እና ከአደጋው ለተረፉ ሰዎች ሁሉ ጸሎት ታደርጋለች” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም “ በአሁኑ ጊዜ የሚመለከታቸው ባለሥልጣኖች፣ የፖሊስ ሐይል አባላት፣ የሲቪል ጥበቃ አባላት እና በጎ ፈቃደኞች እያከናወኑት የሚገኘው ተግባር፣  እንደ እዚህ ዓይነት አሳዛኝ ፈተናዎች በሚፈጠሩበት ወቅት ኅብረትን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳየው ተግባር ነው” ማለታቸውም ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ እንዳሳሰቡት “ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በእምነት የሚገኘውን መጽናናትን ላመጣላችሁ፣ አንደ አባት እና አንደ ወንድማችሁ በመሆን ላቅፋችሁ፣ እንዲሁም በክርስቲያን ተስፋ ተታገዙ ዘንድ ለማስቻል በቅርብ ጊዜ  በአካል ተገኚቼ እንደ ምጎበኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለው በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ፣ ለተጎዱ፣ እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው ሁሉ መጽናናት ይወርድ ዘንድ በማሰብ “ፀጋ የሞላሽ” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከደገሙ ቡኋላ ለእለቱ የነበረው ዝግጅት ተጠናቁኋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.