2016-08-30 11:19:00

ቅዱስነታቸው በመስከረም 1-2016 በሚከበረው ዓለማቀፋዊ የስነ-ሕይወት ቀን ሁሉም ጋር ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 6/2015 በጻፉት ደብዳቤ ላይ ካርዲናል ፒተር ቱርክሰንን እና ካርዲናል ኩርት ኮክን በቅደም ተከተል በቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤት የፍቅር እና የፍትህ አማካሪ ቢሮ ፕሬዚዳንት እና  በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው ክርስቲያናዊ አንድነት ለማምጣት በሚሠራው የጳጳሳት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አድርገው መሾማቸው የሚታወስ ነው።

ቅዱስነታቸው በቅርቡ ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደ ገለጹት “ ስለ ስነ-ሕይወት የሚደርገው ዓለማቀፋዊው የጸሎት ቀን ግለሰቦች እና ማኅበረሰቡ ስነ-ሕይወትን የመንከባከብ እና የመጠበቅ ሞራላዊ ግዴታቸውን እንዲሁም ይህንን አስገራሚ የሆነውን የስነ-ሕይወት ፈጣሪና እንድንከባከበው በአደራ የሰጠንን እግዚአብሔርን እንድናመሰግን  በድጋሜ የሚያስታውሰንን እድል ይፈጥራል፣” ብለው “ስነ-ሕይወትን ለመንከባከብ እንድንችል ያግዘን ዘንድ እና እንዲሁም በምንኖርባት ዓለም ላይ ላደርስነው ጉዳት ይቅርታን እንዲሰጠን ጭምር የእድል በር የሚከፍት አጋጣሚ መሆኑን” ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 28/2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት “መልዕከ ሰላም”  ፀሎት ቡኋላ እንዳሳሰቡት “በሚቀጥለው ሐሙስ እለት ማለትም በመስከረም 1/2016 የዓለም የስነ-ሕይወት ቀን እንደ ሚከበር አስታውሰው ለስነ-ሕይወት ጥበቃ ይደረግ ዘንድ የጸሎት ስነ-ሥርዓት የሚፈጸም በመሆኑ ከኦርቶዶክስ እና ከሌሎች አብያተ ክርስቲያን ምዕመናን ጋር በጋራ መጸለይ እንደ ሚገባ ጥሪ አድርገው ይህም ሁላችንም ሕይወትን የመጠበቅ እና የመንከባከብ ግዴታ እንዲሁም አከባቢያችን እና ተፈጥሮን ከብክለት በመጠበቅ በጋር መንከባከብ እንደ ሚገባን እድል የሚፈጥርልን አጋጣሚ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.