2016-08-18 11:07:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በፖርቹጋል በተነሳው የሰደድ እሳት ለተጎዱ ሰዎች የማጽናኛ መልዕክት አስተላለፉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በፖርቹጋ በአንድ አንድ አከባቢዎች በተነሳው የሰደድ እሳት እየደረሰ በሚገኘው ከፍተኛ ውድመት እና በእዚህ አስከፊ አደጋ ሰላባ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ የሐዘን መግለጫ መልዕክት እና በእዚህ የእሳት አደጋ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን በጸሎታቸው እንደ ሚያስቡዋቸው መግለጻቸው በነሔሴ 10-2008 በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክታቸው ማሳወቃቸው ተገለጸ።

“አይዙዋችሁ! በርቱ! የክርስትያን መጽናኛ የሚመነጨው ከተሰፋ ነው!” በማለት መልዕክታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ተራራማ በሆነ ቦታ እና 900 ያህል ሰዎች በሚኖሩበት አከባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ እስካሁን የሦስት ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ብዙ መኖሪያ ቤቶችን ማውደሙ እና በ100 የሚቆጠር ሄክታር ደን ማውደሙን ለመረዳት ተችሉኋል።

በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ይህንን ሰደድ እሳት በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከፍተኛ ጥረት እያደርገ መሆናቸው የታወቀ ስሆን ይህ በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የተነሳው ሰደድ እሳት ተፈጥሮዋዊው የአየር ሁኔታ እስካልተሻሻለ ድረስ በቁጥጥር ሥር ለማዋል በጣም አስቸጋሪ እንደ ሚሆንባቸው በሥፍራው የሚገኙ የእሳት አደጋ መከላከያ ባለሙያዎች ማስታወቃቸውም ተዘግቡኋል።

ቅዱስነታቸው በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክታቸው በእዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ያላቸውን “አጋርነት እና በጸሎት አብሮዋቸው እንደ ሚሆኑ ገልጸው ይህንን የሰደድ እሳት እይተጋፈጡ የሚገኙትን የእሳት አደጋ ሰራተኞችን አይዝዋችሁ በርቱ አስቸጋሪ ሥራ መሆኑን እረዳለሁ፣ ሰዎችን እና ንብረትን ለማትረፍ መስዋዕት እየከፈላችሁ በመሆናችሁ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጣችሁ ማለታቸውን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት እና መልዕክቱን በውክልና ያስተላለፉት ካርዲናል ጲየትሮ ጳሮሊን በትላንትናው እለት ይፋ ማድረጋቸው ታውቁዋል።

በተያያዘ ዜናም “ሜድትራኒያን ባሕር የመሸጋገሪያ ድልድይ ነው!” በሚል አርዕስት ሥር በሌቼ ጠቅላይ ግዛት ሥር በምትገኘው “በሳንታ ማሪያ ዲ ሉካ” ከነሔሴ 8-2008 ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው ና ወጣቶችን ስለ ስደተኞች አያያዝ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ታስቦ በተዘጋጀው አውደሪይ ማገባደጃ ላይ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ጲየትሮ ጳሮሊን በኩል ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንዳሳሰቡት “ተቀብሎ የማስተናገድ ና አንድነትን የመፍጠር ባህል” በተለይም ደግሞ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እየትሰደዱ የሚገኙትን ስደተኞችን ዋቢ በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክታቸው በተለይም ወጣቱ ትውልድ  ማለትም “ተቀብሎ የማስተናገድ ና አንድነትን የመፍጠር ባህል” እነዚህን ባህላዊ እሴቶች ጠብቆ ማደግ እንድሚገባው አሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው በዋና ጸሐፊያቸው አማካይነት ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደ ገለጹት “የብዙ ወንድ እና ሴት ስደተኞች መኖር እና በተለያዩ ባሕሎች እና እምነቶችን የያዙ ሰዎች ተገናኝተው በሚወያዩበት ወቅት ይህ ግንኙነት ማሕበረሰብን ለማዳበር ከፍተኛ እድል ይፈጥራል፣ ይህም ቅዱስ ወንጌል በሚያዘን መሰረት ለባልንጀራችን መልካምን እንደ ማድረግ ይቆጠራል” ማለታቸውም ተጠቅስኋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.