2016-08-10 16:48:00

ብፁዕ ካርዲናል ማርክስ በኦስትሪያ በሳሊስበርግ የመናብርተ ጥበብ ሳምንት


ማንም ክርስቶስን ያወቀ ሰው አክራሪ ሊሆን አይችልም። ይኽ ደግሞ ወንጌል ይመሰክረዋል። እንደ አብነትም መልካም ሳምራዊው፡ የተራራ ስብከት የመሳሰሉት በወንጌል የሚወሱ ታሪኮችን ማስታወስ ይበቃል። እነዚህ የወንጌል ታሪኮች በኤውሮጳ ለክርስትና ተከታይ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ለኤውሮጳው ባህል ሥልጣኔ ቅርጽ ያስያዙ  ናቸው፡ በወቅታዊው ዓለም የሚሰበከው ነጻነት ለህልውና የተረጋገጠ ዋስትና አይደለም የሚል ሃሳብ ማእከል ያደረገ አስተምህሮ በኦስትሪያ እ.ኤ.አ. እሁድ ነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የሙዩኒክና ፍራይሲንግ ሊቀ ጳጳስ የጀርመን ብፁዓን ጳጳኣት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ኣቢያተ ምክር ኅብረት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ራይንሃርድ ማርክስ የሳሊቡርግ አሳቢነት በሚል ርእስ ዙሪያ በተካሄደው የመናብርተ ጥበብ ሳምንት መዝጊያ ቀን መስጠታችው ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ሕትመቱ አስነብቧል።

የሰው ልጅ ክርስቲያናዊ ራእይ አለ መካድ

የሰብአዊ ነጻነት ክፍለ አካል የሆነው የሰው ልጅ ክርስቲያናዊ ራእይ እርሱም ሰውን በክርስቲያናዊ እይታ ውስጥ የመመልከቱ አስተዋይነት መካድ አያስፈልግም፡ ክርስቲያናዊ ሥነ ሰብእ ይኽ ደግሞ ፍቅርና ሰቂለ ህሊና ያለው የላቀውን ክብር ዳግም በመጐናጸፍ የሚከወን ነው ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ማርክስ በአሁኑ ወቅት በኤውሮጳ እየተከሰተ ያለው አበይት ለውጦች ለዘመኑ ፍልቀት ወይንም ሂደት አንዱ ክፍል ነው፡ እውነቱ ይኽ ሆኖ እያለ በቤተሰቦቻችን ስለ ወቅታዊው ፖሊቲካ ጉዳይ ስንነጋገር ግጭት ውስጥ ካለ መግባት እይካሄድም ይኽ ደሞግ እጅግ የሚያስጨንቅ ጉዳይ ነው፡ ስለዚህ ባንድ በኩል ቁጡነት በሌላው ረገድ ደግሞ ስለ ሌላው በራዳማ አሳቢነት በተሰኙት አጥሮች ውስጥ የተወጠረ ኅብረተሰብ የታነጸ ነው። ይኽ ጉዳይ እንደምናየውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉትም ዓለለማዊ ትስስሮሽ ለበስ ለሆነ ግድ የለሽነት አደጋ እያጋለጠ ነው።

ኤውሮጳዊ እቅድ ተአማኒ ስሜተ ራሮት የዘነጋ ሆነዋል

ብፁዕ ካርዲናል ማርክስ ባስደመጡት ንግግር ወቅታዊው የኤውሮጳ እቅድ በፍቅር በራሮትና የአባልነት መንፈስ የጎደለው መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ምክር ቤት ጉብኝት በማካሄድ አሰምተዉት በነበረው ንግግር ያሉትን ሃሳብ አስታውሰው፡ ኅበረት ሲባል ፍቅር ራሮትና የአባልነት መንፈስ የማይጎላበት ከሆነ ኅብረቱ ስብስብነት ብቻ ሆኖ ይቀራል እንዳሉ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ሕትመቱ ያመለክታል።

እኩልነት ኣልቦ ፍርሃትና ጥለኛ፡ ጠብ ጫሪነት እና ፍርሃት የማዛመት ተግባር በኤውሮጳ

የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ኣቢያተ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማርክስ ባስደመጡት ንግግር፥ በአሁኑ ሰዓት በኤውሮጳ ፍርሃት ኢእኵልነት ጠብ ጫሪነት የመሳሰሉ ተግባሮች በስሜተኝነት እየተዛመቱ ናቸው።  ስለዚህ ስሜት ለአሉታዊ ወይንም ለአወንታዊ ተግባር ማዋል ይቻላል። ለአሉታዊ ተግባር ማዋሉ እጅግ የሚያሰጋና የሰው ልጅ ነጻነት ክብርና ሰብአዊ መብት ለአደጋ የሚያጋልጥ ፍርሃት ብሔርተኝነት የሚያስከትል መንገድ ነው፡ እንዲህ በመሆኑ የኃላፊነት ሥልጣኔ ማነቃቃት ያስፈልጋል። በጣም በአሉታዊ ጎዳና ብዙ ሳይኬድ ከወዲሁ የኃላፊነት ሥልጣኔ በማነቃቃት ኤውሮጳን እንፈውስ ራእይ ያለው መጻኢ ለመገንባት የሚያግዝ መንገድ እናቅና እንዳሉ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ በትላንትናው ኅትመቱ ያመላክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.