2016-08-08 17:02:00

ዝክረ 71ኛው ዓመት አቶሚክ ቦምብ በሂሮሺማ


በሂሮሺማ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ዝክረ 71ኛው ዓመት ምክንያት የፍትና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱርክሶን ባስተላለፉት መልእክት፥ የጦርነትና የአሸባሪያን ሰለባ ለሆኑት ቅርብ እንሁን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታውቀዋል።

ይኽ የዛሬ 71 ዓመት በፊት በሂሮሺማ ልክ ከጠዋቱ ስምንት ሰዓት ከ 15 ደቂቃ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 ዓ.ም. በተጣለው የአቶሚክ ቦምብ 140 ሺሕ ለሞት መዳረጋቸውና ወደ ዘጠኛ ሺሕ የሚገመተው ሕዝብ ቦምቡ በተጣለበት ወቅት በቅጽበት እንደ አቧራ በነዋል። የሂሮሺማ ከተማ 90 መቶኛውን የሚሸፍነው ክልል ለውድመት ዳርጓል።

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ቀጥሎም በሦስት ቀናት ልዩነት ውስጥ በናጋሳኪ ዳግም የተጣለው አቶሚክ ቦምብ ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት እልባት ያሰጠ ከመሆኑም ባሻገር በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታና በቀድሞ ሶቪየት ኅብረት የአቶሞክ ጦር መሣሪያ ምርት እሽቅድድም ያስጀመረ መሆኑ ታሪክ የሚያረጋግጠው እውነት ሲሆን፡ በሂሮሺማ በተካሄደው ዝክረ 71ኛው ዓመት የሂሮሺማ ከንቲባ ካዙሚ ማትዚይ በዝክረ ስነ ሥነ ስርዓት በተገኙት 50ሺሕ ሕዝብ ከ 91 አገሮች የተወጣጡ ልኡካን በተገኙበት በሰላም የተዘክሮ አደባባይ ከጠዋቱ ልክ 8 ሰዓት ከ 15 ደቂቃ በየዓመቱ በሚካኤደው የተዘክሮ ስነ ሥርዓት የተሳታፊያን አገሮች ቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ምርት እገዳ ስምምነት ታልሞ ለሚደረገው ጥረት አቢይ ድጋፍ መሆኑ ያላቸው ተስፋ መግለጣቸው ደካሮሊስ ገልጠው፥

ቱርክሶን፥ የጦርነትና የአሸባሪያን ሰለባ ለሆኑት ቅርብ እንሁን

ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን ለዝክረ ስነ ሥርዓቱ ያስተላለፉት መልእክት በዚህ በሳቸው ለሚመራው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ሚካኤል ቺዘርንይ በተካሄደው ስነ ሥርዓት ተገኝተው መነባቡንም አስታውሰው፡ አባ ቺዘርንይ በሂሮሺማ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በመሳተፍ መልእክቱን ዳግም ሲያነቡ፥ ጳውሎስ ድስተኛ ጥቅምት 1965 ዓ.ም. ለተባበሩት መንግሥታት ባስደመጡት መልእክት፥ ለእርስ በእርስ ጸበኝነት እምቢ። መቼም ቢሆን የእርስ በእርስ ጥላቻ ያብቃ” ያሉትን ቃል ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት እነዚያ የአቶሚክ ቦምብ ሰለባ ለሆኑት በመጸለይ በዚህ ብቻ ሳይታጠርም የግብረ ሽበራ ሰለባ የሆኑትን በማሰብና በመጸለይ የሰላም መሣሪያ እንሁን እንዳሉ አስታውቀዋል።

በዚህ የምሕረት ቅዱስ አመት ወቅት የመማማርና ይቅር የመባባል ተግባር ዳግም ማስተዋልና መኖር

በዚህ ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር ዓመታዊ በዓል በምታከብርበት ዕለት የእግዚአብሔር ቅዱስ ምሕረት አስተንፍሶ መሪና መርህ እንዲሆን እንጸይ  ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን የምሕረት የእርቅ የትብብና ጸጋውን በዚህ በቅዱስ የምሕረት ዓመት ያብዛልን፡ የሰውን ልጅ ልብ የሁሉም ሃይማኖት ተከታታዮች ልብ የሚነካ ጸጋ ይሁንልን እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.