2016-08-08 19:59:00

በሶርያ ሕጻናትና ራስን መከላከል የማይችሉ የግጭቱ ዋጋ እንዲከፍሉ የማይገባ ነው! ር.ሊ.ጳ


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናንትና በቅዱስ ጰጥሮስ ከተገኙ በብዙ ሺ ከሚገመቱ ምእመናን ጋር የመልእከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል። ቅድስነታቸው በአደባባዩ ለተሰበሰበው ህዝበ እግዚአብሔር  የዕለቱ ቃለ ወንጌል ጠቅሰው ባሰሙት ስብከት፡ ኢየሱስ  ክርስቶስ  ለሐዋርያቱ   ከጌታ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻው ግንኙነት መከናወን ስላለበት ሁኔታ እንዳስታወሳቸው አስታውሰዋል። ከጌታ የሚደረገውን ግንኙነት በመልካም ተግባር የተሸኘ መሆን እንደሚገባም  ቅድስነታቸው  በማያያዝ  በቅዱስ ጰጥሮስ ለተገኙ ምእምናን እና ሀገር ጐብኝዎች አስገንዝበዋል። ሰዎች ሁሉ የፈለጉትን ያህል አንጡራ ሀብት ሊኖራቸው ይችላል ሲያልፉ ግን ምንም የሚወስዱት የለም እና እዚህ ምድር ላይ ሩህሩኅን ደጎች መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል።

የምህረት ድርጊት ማድረግ  ክርስትያዊ  ሕይወት ማዘውተር አለብን ብለው ያሉት ቅድስነታቸው መድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን በእምነት መጠባበቅ አለብን  ለመንፈሳዊ  አገልግሎት  ዝግጁ መሆነ   አለብን ብለዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ በየዕለቱ ከኛ ጋር ይገኛል ልባችን ያንኳኳል እና ልባችን ከፍተን እንቀበለው ብለዋል ቅድስነታቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአገልጋዮቹ አገልጋይ መሆኑም ቅድስነታቸውበማያያዝ በቅዱስ ጰጥሮስ   አደባባይ ለተገኙ ምእምናን አክለው ተናግረዋል። 

በመጨረሻም በሶርያ የተከሰተው ህውከት እና ግጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ህጻናትን ጨምሮ ሲቪል ህዝብ የዚሁ ግጭት ሰለባ መሆናቸው ጠቅሰው የሚሰማቸውን ሐዘን ገልጠዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንት በሰሜናዊ ሶርያ በአለፖ እና አከባቢ ወደ700 የሚጠጋ ህዝብ  ለሕልፈት መዳረጉ  የሶርያ ህዝብ መብቶች ታዛቢ ቡድን የሰጠው መግለጫ ያመለክታል።

የሶርያ ህዝብ ለዚሁ አስከፊ ሁኔታ መጋለጡ የሚያሳዝን እንደሆነ ዓለም  አቀፍ ማህበረ ሰብ  ሰላማዊ መፍትሔ  እንድያፈላልግ ቅድስነታቸው አደራ ብለዋል። ይሁን እና ከአምስት  ዓመታት  በፊት  የተጀመረው  የሶርያ  የርስ በርስ ጦርነት  ባለበት እየቀጠለ መሆኑ  ህዝቡ  የጦርነቱ  ሰላባ  መሆኑ  በየዕለቱ  እየተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ሁለቱ  ኅያላን  መንግስታት ማለትም አመሪካ እና ሩስያ የሶርያ ሰላማዊ መፍትሔ  በተመለከተ  የተለያየ አመለካከት እና ራእይ እንዳላቸው እና የጦርነቱ  ሰላማዊ መፍትሔ  በየግዜው  እየራቀ  እና እየተመሰቃቀለ መሄዱ  ታዛቢዎች  ያወሳሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.