2016-08-08 17:04:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአባልነት ሢመት ሰጡ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ኖትረ ዳመ መንበረ ጥበብ የሕግና የስነ ፒሊቲካ ጥናት መምህር ፕሮፈሰር ፖውል ኮራዛ የጳጳሳዊ የሥነ ማኅበራዊ ተቋም አባል በማድረግ እንደ ሸሟቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ፕሮፈሰር ኮራዛ እ.ኤ.አ. በ 1963 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የተወለዱ በሃርቫርድ መንበረ ጥበብ በሥነ ማሕበራዊ ጥናት ሊቅነት ቀጠለውም በሥነ ሕግ ጥናት ጭምር ሊቅነት ያስመሰከሩ በአሁኑ ወቅት በተባበሩት የአመሪካ መንግስታት ኢንዲያንስ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የሥነ ጥናት ተቋም ዋና አስተዳዳሪ፡ በሰብአዊ ሕግ ዙሪያ ብዙ መጻሕፍት የደረሱና የኤውሮጳ የሕግ መሠረተ ባህል ለይተው እንዲሁም የላቲን አመሪካ የሕግ መሠረተ ባህል ዙሪያ ልዩ ጥልቅ ጥናት ያካሄዱ ከ 2006 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. የመላ አመሪካዎች የሰብአዊ መብትና ክብር ድርገት አባል የነበሩና ይኸንን ድርገት እ.ኤ.አ. ከ 2008 እስከ 2009 ዓ.ም. በሊቀ መንበርነት ጭምር የመሩ ሚላኖ በሚገኘው በካቶሊካዊ የቅዱስ ልበ ኢየሱስ መንበረ ጥበብ ያካተተ በኤውሮጳና በላቲን አመሪካ ጎብኝ መምህርነት በማገልገል ላይ የሚገኙ በቺለ በሃርቫርድ የሕግ መምህር መሆናቸውም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጥቁማል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.