2016-08-03 16:41:00

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሂደቱና የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክቶች ጽማሬ


እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 27 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በአገረ ፖላንድ ክራኩፍ ከተማ ተካሂዷል በመከታተልም የበዓሉ ዕለታዊ ውሎዎች ስናቀርብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን መለስ ብለን የሂደቱና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እዛው በመገኘት ያካሄዷቸው ግኑኝነቶች ለወጣቶቹ ያስተላለፉት ምዕዳን የሰጡት አስተምህሮና ስብከት ጽማሬው ከዚያ ቅዱስነታቸው ከተለያዩ የዓለማችን ክልል ለተወጣጣው ከሁለት ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱት ወጣቶች በመደጋገም ለያይ ግንቦችን ማቆም ሳይሆን አገናንኝ ድልድይ ገንቢዎች ሁኑ፡ የታሪክ ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ዋና ተወናያን በመሆን ዓለምን ለመለወጥ እንዲተጉ የአደራ ጥሪ አስተላልፈዋል። በዚህ እየተኖረ ባለው የምሕረት ቅዱስ ዓመት ውስጥ ይኽ “ምህረትን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው ምኅረትን ያገኛሉና” በሚል ቃለ ወንጌል ሥር ተመርቶ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዓቢይ ሁነት ተብሎ የሚነገርለት ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እነዚያ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰገወው የእግዚአብሔር ምሕረት በቃልና በሕይወት የመሰከሩ የፖላንድ ተወጆች ቅዱሳን ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ቅድስት ፋውስቲና ላይ በማተኮር ቅዱስ አባታችን ምሕረትን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው ምሕረትን ያገኛሉና የሚለውን ቃለ ወንጌል በተለያየ መልኩ ተንትነዉታል።

ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዳሜ ሌሊት የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መዝጊያ እሁድ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ጧት ቅዱስነታቸው ለሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ዋዜማ ክራኩፍ በሚገኘው በምሕረት አደባባይ ከአንድ ሚሊዮን 600 ሺህ በላይ ለሚገመቱ ወጣቶች በሰጡት አስተምህሮ፥ “ለያይ የግንብ አጥር ከመገንባት ይልቅ አገናኝ ድልድይ መገንባት እጅግ ቀላል መሆኑ እኛን ለማስተማር ድፍረቱን ብርታቱ ይኑራችሁ”፥ አቢይ የወንድማማችነት ድልድይ የገነቡት ከአምስቱ ክፍለ ዓለም ለተወጣጡ ወጣቶች ንቃት አልቦ የሆነው ተክለኛ ሕይወት ለመኖር ከሚዳርጋቸው የመገናኛ አሳግርትና በመገናኛ አሳግርት ጭውውት ከመሳሰሉት አደንዛዥ መሣሪያዎች ተቆጥበው ለዚያ አልቦ ሕይወትና የማይንቀሳቀሱ ሆነው እንዲቀሩ ለሚፈልጉዋቸው ነጻነታቸው በከፍተኛ ድምጽ እንዲያሰሙ አደራ ያሉት ቅዱስነታቸው ጥላቻን በጥላቻ ማሸነፍ ለሚለው አመለካከት እምቢ በሉ፡ ለጦርነት የሚሰጠው መልስ ወድማማችነት ነው  ብለዋል።

ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፥ በሕዝቦች መካከል ጥላቻ እምቢ ማለት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመሥዋዕተ ቅዳሴው ለተሳተፉት ሁለት ሚሊዮን ወጣቶች ዓለም ለውጡ እግዚአብሔር ደጋፊያችሁ ነው። ምን ለብሳችኋል ምን ዓይነት የእጅ ተሌፎን አላችሁ ለእርሱ ይክ ግድ አይሰጠውም ትካዜነትን እምቢ በሉ። በአግባብና አለ አግባብም ስኬታማነት ብቻ ለሚለው ለሚያደነዝዘው የስግብግብ መንፈስ የሚፈጥረው አደንዛዥ ጽንሰ ሓሳብ እምቢ በሉ። በሕዝቦች መካከል ጥላቻን እምቢ የሚል፡ የአሁጉራቱን ክልል ወይንም ድንበር ለያይ ግንብ አድርጎ የማይመለከት ባህሉን ቋንቋዉን መለያውን በራስ ወዳድነት መንፈስና ሌላው ላይ የመበቀያ መሳሪያ ለማያደርግ የታደሰ ሰብአዊነት ላይ እማኔ ያላችሁ በመሆናችሁ አላሚያን ናችሁ ብለው ሊፈርዱባችሁ ይችላሉ፡ ፍርዱን ተቃወሙት፡፡ ባላችሁ ደስታና በተዘረጉት እጆቻችሁ ተስፋን ታበስራላችሁ፡ ለዚያ ለምትወክሉት ለአንዲያው ሰብአዊነት ቡራኬ ናችሁ ስለዚህ ተስፋ አትቍረጡ ብለዋል።

ቤተ መቅደስና ያቀባበል ስነ ሥርዓት

ወደ ኋላ መለስ ስንል፡ በዚያ የመለኮታዊ ምሕረት ቤተ መቅደስና በዚያ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቤተ መቅደስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በወጣቶች አቀባበል ተድርጎላቸው በለገሱት አስተንትኖ፥ ወንጌል ያልተቀለመ ባዶ ገጽ አለው እርሱም በሕይወታችን በምንፈጽመው ግብረ ምሕረት የሚጻፍ ነው ብለዋል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ገና ከዚያ ለኢጣሊያ የክራኩፍ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊያን ሓምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስተላለፉት የድምጸ ርእየት መልእክት በተለይ ደግሞ ሓሙስ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በ 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በተደረገው ይፋዊ ያቀባበል ስነ ሥርዓት፥ ምሕረት ምን ማለት መሆኑ በቃልና በተግባር በመመስከር አገናኝ ድልድይ መገንባትና ለያይ የግንብ አጥር ማፍረስ ምን ማለት መሆኑ አስተጋቡ እንዳሉም ይታወሳል።

አንድ ልብ ክፍትና የማለም ብቃት ያለው ከሆነ ለምሕረት ቦታ ይኖረዋል፡ ሌላውን ለማጽናናትና የሌላውን ስቃይ ለማበስ የሚበቁ እጆቻችን ለመዘርጋት የሚያችለው ቦታ ይኖረዋል። በልባቸው ሰላም ለተነፈጋቸው በድኽነት ለሚሰቃዩት ያ ወብ የሆነው እምነት ለሌላቸው ሁሉ ቅርብ ለመሆን ያበረታታል። ዓለም ይሰማንም ዘንድ ድምጻችንን ከፍ በማድረግ ምሕረት የሚለውን ቃል ሦስቴ አብረን እንድገም ብለዋል።

ዓርብ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በአውሽዊዝ የመቅሰፍት ሰፈር፡ በሕጻናት ማከሚያ ቤት በመረሻም የፍኖተ መስቀል ጸሎት

 

ቅዱስ አባታችን ወጣቶች ዓለም ለውጡ። ዓለም እንዲለውጡ አደራ በማለት ገና በለጋ እድሚያችሁ ጡረተኞች አትሁኑ ብለዋል። የወጣትነት እድሜ የጋለው ሕይውትና ትኩስ ኃይል የሚደነቅ ነው፡ ዓለምና ቤተ ክርስቲያንም ይኽ የእናንተው ትኩስ ኃይል ያስፈልጋቸዋል ያሉት ቅዱስ አባትችን ገና ወደ ክራኩፍ በተነሱበት አይሮፕላን ውስጥ ሆነው ለሚሸኙዋቸው ጋዜጠኞች የሰጡት ቃለ ምልልስና እንዲሁም በመመለስ ላይ እያሉም በተመሳሳይ መልኩ ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እኚያ በሚዘገንን ድርጊት በሁለት ወጣቶች በፈረንሳይ ለሞት የተዳረጉት የ86 ዓመት እድሜ ካህንና ተመሳሳይ አሰቃቂ ድርጊቶችና አመጾችን ሁሉ አስታውሰው፡ በዓለም የሚታዩት ጦርነቶች በሃይማኖት መካከል አይደለም። የምስልምና ሃይማኖት ከዓመጽ ጋር ማመሳሰል የተገባ አይደለም በማለት ገልጠው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን። በአውሽዊዝ ቅዱስነታቸው በጽሞና በሕሊና ጸሎት ተሸኝተው ባካሄዱት ንግደት ከቃላት በላይ ሰላምና ወንድማማችነት አደራ የሚል ቃል አስተጋብተዋል።

በሕፃናት ማከሚያ ቤት ባካሄዱት ሐዋርያዊ ንግደት እንዲሁም በፍኖተ መስቀል የጸሎት ስነ ሥርዓት በመስቀል ፊት የሰው ልጅ መሠረታዊ ጥያቄ እርሱም “እግዚኣብሔር የት ነበር፡ እግዚአብሔር አለ ወይ?” ንፁሐን ዜጎች ለሞት ይዳረጋሉ። በግብረ ዓመጽና ባሸባሪነት ሕይወታቸው የሚያጡ ሕፃናት ንፁሐን ዜጎች ለሞት ተላልፈው ይሰጣሉ። ስለዚህ ለምን ለሚለው ጥያቄ መልስ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ነው። እርሱ ገዛ እራሱን ከሚሰቃዩት ጋር አመሳሰለ ስቃያቸው የገዛ እራሱን አደረገ። የክርስትና ታማኝነት በተቀባይነትና ባስተናጋጅነት እንጂ ጽንሰ ሓሳብ አይደለም። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይኸንን መሰረት በማድረግ ወጣቱ ትውልድ የመስቀል መንገድ ያለው ክብር በማስተዋል ያገልግሎት ተወናያን እንዲሆን አደራ ብለዋል።

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በክራኩፍ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በተካሄደው የፍኖተ መስቀል ጸሎት ባሰሙት ስብከት “ፍኖተ መስቀል የተስፋና የመጻኢ መንገድ ነው። በለጋስነትና በእምንት የፍኖተ መስቀልን የሚከተል ለመጻኢና ለሰብአዊ ተስፋን ያሰጣል። እናንተ የተስፋ ዘሪዎች ትሆኑ ዘንድ ምኞቴ ነው” እንዳሉ የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.